Get Mystery Box with random crypto!

ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️

የቴሌግራም ቻናል አርማ barnabasism — ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️
የቴሌግራም ቻናል አርማ barnabasism — ትዝብተ-በርናባስ🔎✍️
የሰርጥ አድራሻ: @barnabasism
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.62K
የሰርጥ መግለጫ

ምድር እጅግ ሰፊ ናት፤ እኔ ወንድማችሁ በርናባስ ደግሞ ያሉኝ ሁለት ዐይኖች ብቻ! አባካችሁን ኑ...ና አጋጭተን (ዐይኖች አዋጥተን) እንይ!✍️
አሳብ አስተያየት ቢኖራችሁ፦ @barnica የግላችሁ ነው።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-11 20:37:09 አንተነትህ እኔነቴን!
(ከበርናባስ በቀለ)

አዲሱ ዓመት አዲስነቱ ለእኔ ለውስኑ እንጂ
ለዘመናቱ ባለቤት ለአንተ አይደለምና የሚመጡትን ቀናት 'ባንተው እደፍራለሁ።

ሊመጡ ያሉ ቀናት በውስጣቸው ሸክፈው የያዙትን በውል አላውቅም፣ ግና በአንተ እንደተያዙ አውቃለሁና ልቤም ጀገን መንፈሴም ቆፍጠን ማለቱ ይቀጥላል!

አንተ "እዚያ" የምትለው ስፍራና ያኔ (ወደፊት) የምትለው ጊዜ የለም። ለአንተ ለኢ-ውስኑ አምላኬ ስፍራዎች ሁሉ እዚህ፣ ጊዜያትም ሁሉ "አሁን" ናቸው፤ ያልኖርኳቸው ዘመኖቼም ሁሉ በአቆጣጠርህ "እዚህና አሁን" ናቸው።

አዱሱ ያልሁት ዓመት በዘንድህ ያረጀ፣ ይመጣል ያልሁትም ዘመን በፊትህ ያለፈ ነው። ምጡቅ ነህና ከጅማሬው ፍጻሜውን ተናግረኻል፣ ረቂቅ ነህና ከቀኖቼ ቀድመህ ኖረኻል፣ ከዘላለም ነህና አዲስ ያልሁትን አስረጅተኻል። ስለዚህም፦ አንተነትህ እኔነቴን ይወስነዋል!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
2.7K viewsBarnabas Bekele, edited  17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 22:47:17 ነፍሶlogy!
(ከበርናባስ በቀለ)

ነፍስ ማረፊያዋ ባለፈው ወር የገዛኸው ባለ ስፕሪንጉ ፍራሽ አይደለም። ቤትህ ያለው ዘመናዊና ዘናጭ ሶፋም ስጋህን ቢያሳርፍ እንጂ ለነፍስህ ምኗም አይደለም።

በእግዚአብሔር ማረፍ እስካልቻልክ እረፍት ርቆህ ሌሎችንም እረፍት ስትነሳ ትኖራለህ፤ በእርሱ በማረፍ ደግሞ ለሌሎችም እረፍት ምክንያት መሆን ትችላለህ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
◊ @barnabasism ◊
3.9K viewsBarnabas Bekele, edited  19:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 16:44:10 እኔና ሰላምተኛዋ ወዳጄ!

እሷ፦ "ባርኒ ደህና ነህ?"

እኔ፦ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና!

እሷ፦ "ሁሉ ሰላም!?"

እኔ፦ አይደለም! እኔ ደህና ነኝ።

እሷ፦ "ምን ተፈጠረ? ችግር አለ ባርኒ?"

እኔ፦ ምነው!? ለምን እንደሱ አልሽ?

እሷ፦ "ሰላም አይደለም!" አልከኝ እኮ!

እኔ፦ ሰላም አይደለም አላልኩሽም ወዳጄ! ያልኩሽ "ሁሉ ሰላም አይደለም" ነው።

እሷ፦ "ልዩነታቸው ምንድነው?"

እኔ፦ "ሁሉ" የሚል ቃል የማይጠቅም ቃል ነው እያልሽኝ ነው? ማለቴ፦ "ሰላም" ከሚለው ፊት ሁሉ ሲጨመር ምንም ለውጥ አይመጣም ነው 'ምትዪው?

እሷ፦ "እስቲ በአማርኛ እናውራ ባርኒ!?"

እኔ፦ በአጭሩ ለማለት የፈለኩት በምድር ስንኖር መቼም "ሁሉ ሰላም" አይሆንም! ያለነው የወደቀ ዓለም ውስጥ ነውና። "ሁሉ ሰላም" የሚሆነው በሚመጣውና መሲሑ ብቻውን በሙላት የሚገዛበት ዓለም ነው። ሲቀጥል፦ እኔ ደህና ልሆን ግዴታ ሁሉ ሰላም መሆን የለበትም! "ሁሉ" የሚለው ቃል ውስጥ ቤተሰቤ፣ ማህበረሰቤ፣ አገሬና አህጉሬም ጭምር ይገኙበታል! ይህ ሁሉ ሰላም ባልሆነበት ለምን "ሁሉ ሰላም" እላለሁ!?

እሷ፦ ኦኦኦኦ! እና በሚቀጥለው ቀን ደህንነትህን ልጠይቅ የምትፈልገው በምን መልኩ (ቃል) ነው? ትክክለኛውስ የቱ ነው?

እኔ፦ "ባርናባስ ሰላም ነህ? ደህና ነህ?" ጥሩ እንደሆነ አስባለሁ። ትክክለኛውም መንገድ እሱ እንደሆነ አስተውላለሁ።

እሷ፦ "አይ... ባርኒ! ለማንኛውም ተመስግነሃል"

እኔ፦ ተቀብዬአለሁ! ሰላምሸ ይብዛልኝ። እና ደህና ነሽ? የጋራ አጀንዳ ላይ ውይይቱ ቀጠለ!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
1.5K viewsBarnabas Bekele, edited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-10 13:13:12 ሐኪሙን እናሳክመው!

በዙሪያው ባሉት ሰዎች ሁሉ ዘንድ ይወደዳል፤ ጽናት መታወቂያው ነው። ለሌሎች መኖር የሕይወት ዘመን ጥሪው እንደሆነ በጽኑ ያምናልና ሌሎች ቀና እንዲሉ አንገቱን ይደፋል፣ ፈገግ እንዲሉም ያለቅሳል።

ይኸው ለትውልዴ የጽናት ምሳሌ የሆነው ወዳጄ (የልቤ ሰው) ሰሞኑን ከባድ ተግዳሮት ተደቅኖበታል። ራዕዩ አህጉር አቀፍ ነው! ሰሞኑን የገጠመው ተግዳሮት ግን በእኔና በጥቂት ወዳጆቼ ሊቀረፍ የሚችል ነው።

እጅግ የሚያማምሩና ለነገዋ አገር ተስፋ የሰነቁ ሁለት ልጆች አሉት፤ ሁለቱንም ልጆቹን በተመሳሳይ ኬዝ እያስታመመ ሁሉን እርግፍ አድርጎ ቁጭ እንዳለ አጫወተኝ። ከስልክ ጥሪው በኋላ...

ለአገሬም ሆነ ለትውልዴ የሚጠቅሙ ፕሮጀክቶቹ ከተጋረጠበት ፈተና እና የፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳይቆሙ "እኔ ማድረግ የምችለው ምንድነው?" ብዬ ራሴን ጠየኩኝ! እስካሁን ሳስበው ቆየሁና ይኸው ወደ እናንተም ይዤ መጣሁኝ።

እነዚህን በመሰሉ ክፉ ቀናት ለሰዎች ሰው ሆኖ የመገኘት ሸክሙና ልምዱ ያላችሁ ወዳጆቼ አብረን አንዳች ማድረግ ብንችል ደስ ይለኛል። እንዴትና በምን መልኩ የሚለውን በውስጥ የምናወራ ይሆናል።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
1.4K viewsBarnabas Bekele, edited  10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 18:57:06 ተናጋሪ ነህ!?
(ከበርናባስ በቀለ)

ስለ ንግግር ስታስብ "መቼ (time)፣ የት (place)፣ ምን (content)፣ ለማን (audience) እና እንዴት (manner) ላውራ?" የሚለውን ሁልጊዜ ማሰብና ራስህን መጠየቅ አለብህ። ይህን ማገናዘብ ትተህ (የአየር ሰዓት ተገኘ ብለህ) የምታወራ ከሆነ ሥርዓት-አልበኝነት is loading!

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
2.6K viewsBarnabas Bekele, edited  15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 22:24:13 በዓሉና ሕይወቱ!

የመጀመሪያው አዳም (የዔደን ገነቱ) አመጽ ታሪክ በመስቀሉ ሲዘጋ በትንሳኤው ደግሞ የአዲስ ሕይወት ምዕራፍ በር ወለል ብሎ ተከፍቷል።

የትንሳኤው ዓላማ ታዲያ የትንሳኤ ሕይወት እንጂ የትንሳኤው በዓል አይደለም። ትንሳኤው የአዲሱ ሕይወት (ማንነት) ልደት አዲስ ምዕራፍ እንደመሆኑ ከትንሳኤው በኋላ ሕይወቱ ይቀጥላል።

ሕይወቱ ግድ የማይሰጣቸው በዓሉን ግን ጠብ እርግፍ ብለው የሚያከብሩ ከትንሳኤው ዓላማ ጋር ተላልፈዋልና እንዘንላቸው።

እንኳን አደረሳችሁ።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
2.8K viewsBarnabas Bekele, edited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-08 09:24:29 የክሱ ማስረጃ!
          (ከበርናባስ በቀለ)

የማይኖርበትን እውነት የሚሰብክ ሰባኪ በራሱ ላይ የክስ ፋይል እየከፈተ ሲሆን ወዲህና ወዲያ እየተወራጨ የስብከቱን ሃሳብ ሲተነትን ደግሞ በትልቁ ዳኛ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ክሱን በማስረጃ እያስደገፈ ነው።

ለአስተያየትዎ፦ @barnica
Join ➘ & Share ➝
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
     ◊   @barnabasism  ◊
2.4K viewsBarnabas Bekele, edited  06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 21:54:12 ወደ ፍጻሜዬ 365 ቀን ተጠጋሁ!

ይህች ቀን ከእናቴ ማህጸን ወደ ኢትዮጵያ አገር የመጣኹባት ቀን ናት። ይኸው ቀን ታዲያ በሕይወቴ ትልልቅ ሥፍራ ከምሰጣቸው ቀናት መካከል አንዱ ሲሆን ያለፈውን ዘመን ኦዲት እያደረግሁ ቀጣዩን ለመቀበል በብዙ ፍርሃት የዘመናት ባለቤት ፊት የምቆምበት ነው።

"በእድሜህ ላይ አንድ አመት ተጨመረልህ" ሲሉኝ ግን አይዋጥልኝም፤ የምኖረው ከተመደቡልኝ የእድሜ ዘመናት እየተቀነሰ እንጂ በእድሜዬ ላይ ሌላ አመት እየተጨመረ አይደለምና። "ተጨምሮልሃል" እያላችሁማ አታዘናጉኝም! ተቀንሶብኛል።

የዘበርጋ ልጅ ማርቆስ ድርጅት (Facebook) የልደት ቀኔን ለሰፊው ሕዝብ ከስምንት ቀናት በፊት ይፋ አድርጎ የነበረ ሲሆን ትክክለኛው የልደት ቀኔ መጋቢት 20 መሆኑን ስነግራችሁ በዚያ እለትም ሆነ ዛሬ በመልካም ምኞታችሁ አብራችሁኝ ለነበራችሁ ወዳጆቼ ምስጋናዬ እጅግ ብዙ ነው።

ባለፈው አመት በመንገዴ አብራችሁኝ የነበራችሁና ህልሜን እንድኖር ያገዛችሁኝ ወዳጆቼ በሕይወቴ የተገለጠው በጎነት ያለ እናንተ እውን አይሆንም ነበርና ስማችሁ በእኔ ዘንድ ክቡርና ጥዑም ሆኖ ይቆያል። ብዙ መውደዴ በያላችሁበት።

ለአሳብ አስተያየትዎ፦ @barnica
Join & Share
@tzbtebrn @tzbtebrn
@tzbtebrn @tzbtebrn
1.7K viewsBarnabas Bekele, edited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 09:04:34 ጆ ባይደን ለምን ከእኔ አይማሩም!?
           (ከበርናባስ በቀለ)

ከሰሞኑ "የአሜሪካን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ መሪ ደውለው ስልኩ አተነሳላቸውምና ዓለም ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ልትሄድ ነው።" የሚሉ መረጃዎች ሲዘዋወሩ አይቻለሁ።

እንዴ!? የእነርሱ (የሁለቱ) ስልክ እንዴት ነው የዓለምን አቅጣጫ ሊቀይር የሚችለው? የዓለም አቅጣጫ መዘወሪያ ያለው እነርሱ እጅ ነው እንዴ!? አሁንስ አበዙት! በዚህ ከቀጠልን አንድ ቀን "የጆ ባይደንን ድመት አንዱ የጎሮቤት ወጠምሻ ድመት ገላምጧታልና ዓለም ሌላ ታሪክ ውስጥ ልትገባ ነው" መባላችን የት ይቀራል?

ቆይ ግን፦ ባይደን ከአንድ አንድ ስልክ እንዲነሳላቸው የሚፈልጉት ለምንድነው? ደውለው ካልተነሳላቸው ለምን መልሰው አይሞክሩም!? አሊያም ለምን በቴሌግራማቸው አይጽፉላቸውም? Imoስ የላቸውም? ለምን በቅንነት አያስቡም? SMS ማድረጉስ ማንን ገደለ!?

እኔ ስልክ አልተነሳልኝም ብዬ አኩርፌም አላውቅ! ባይደን ግን ለምን ከእኔ አይማሩም!? ብዬ ልጽፍ አሰብኩኝና ለካ ነገሩ ፖለቲካዊ ነው። የእኔ ስልክ ተነሳ አልተነሳ ለውጡ የሚኖረው እኔ ጋር ነው። ሁለቱ (የባይደንና የUAE መሪ) ስልኮች ጀርባ አገር፣ ሥልጣንና ሕዝቦች እንዳሉ ሳስብ ይኸው አርፌ ቁጭ!

ለአሳብ አስተያየትዎ፦ @barnica
Join & Share
@tzbtebrn @tzbtebrn
@tzbtebrn @tzbtebrn
1.5K viewsBarnabas Bekele, edited  06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-13 11:38:52 ወንድም አለህ/ሽ!

የበላችሁት ጣፍጧችሁ፣ የለበሳችሁት ሞቋችሁ፣ የዘራችሁት ብዙ አፍርቶላችሁ፣ የነካችሁት ተባርኮላችሁ፣ በክፋት የሚነሳባችሁ ተከልክሎላችሁ በሰላምና በጤና ወጥታችሁ እንድገቡ የሚመኝና የሚማጸን ወንድም እንዳላችሁ ታውቁ ይሆን!?

አምላኬ ክፉውን ዘወር ያድርግላችሁ! አሁናዊ ፈቃዱንም በየእለቱ ይግለጥላችሁ። ከብዥታ ምልልስና ከድንግዝግዝ ኑሮም ይታደጋችሁ፤ ቀናችሁ የምትሰለጥኑበት (የሚሠራላችሁ) እንጂ የሚሰለጥንባችሁ አይሁን። ከጠላትም ቀስት ከወዳጅም ፍላጻ ተሰወሩልኝ። እምር፣ ድምቅ... ፍክት በሉልኝ!

ለሃሳብ አስተያየትዎ፦ @barnica
Join & Share
@tzbtebrn @tzbtebrn
@tzbtebrn @tzbtebrn
1.3K viewsBarnabas Bekele, edited  08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ