Get Mystery Box with random crypto!

“ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግ | ማዕተብ

“ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግዚአብሄር ሔዋንን የረገማት ርግማን ባንቺ ተሽሯልና፡፡”
“ድንግል ሆይ ባማረ በተወደደ ነገር ሁሉ መሰልሁሽ ምስጋናሽን ግን ለመፈፀም አልቻልኩም፡፡እግዚአብሄርን ባመሰገንሁ ጊዜ ባንቺ ለስሙ ምስጋና አቀርባለሁ ፤ በስምሽም ፀሎቴን በፀለይሁ ጊዜ ፀሎቴን ለልጅሽ አቀረብሁ፤ዳግመኛም ውዳሴሽን ወደማወቅ ባህር ልዋኝ ወደድሁ ፡ ወደ ክብርሽ ገናንነት ወደብ እደርስ ዘንድ ደከምሁ ፡ ያንዲቷን ማእበል ሞገድ ያህል ስንኳን አላለፍሁም፡፡ ወደ ፅርሀ አርያም ጠፈር ለመድረስ የሚቻለው ማነው? ከምድር በታች ወዳለው ባህር መሰረትስ መዋኘት ማን ይችላል? ድንግል ሆይ ክብርሽን ገናንነትሽን ጠንቅቆ መናገር የሚቻለው ማነው?።”
“ድንግል ሆይ የማያከብርሽ ለልእልናሽም የማይሰግድ ለዘላለሙ ርጉም ነው፡፡ በፍፁም ልቦናው የማይወድሽ ፡ ከትልቅ ሃሳቡም የማያከብርሽ ርጉም ነው ፤ በከንፈሮቹ የማያመሰግንሽ፣ ባንደበቱም የማይመርቅሽ ርጉም ነው ፤ ለክብርሽ የማይሰግድ ለገናንነትሽም የማይገዛ እድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ገሃነመ እሳት ነው፡፡”

ድንግል ሆይ በአማላጅነትሽ አትለይን አሜን።

[_አርጋኖን | አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ_]