Get Mystery Box with random crypto!

“ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግ | ማዕተብ

“ድንግል ሆይ ፦ አዳም ከልጆቹ ጋር ያመሰግንሻል በሱ የተፈረደ መርገመ ስጋ ባንቺ ጠፍቷልና ፡ እግዚአብሄር ሔዋንን የረገማት ርግማን ባንቺ ተሽሯልና፡፡”
“እመቤቴ ማርያም ሆይ ፦ ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንደበት የሃይማኖት አለት ተብሎ ጴጥሮስ የተጠራባት አለት አንቺ ነሽ፤ የሐዋርያት ጉባኤ የምትሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ባንቺ ተመሰተች፤ የንጉሱም ሙሽራ ባንቺ ተጌጠች፤ ባንቺም ምሶሶች ቆሙ፤ ሕንፃዋ ባንቺ ፀና፣ ግድግዳዋም ባንቺ ተሰራ፣ ጠፈሯም ባንቺ ተጠፈረ፣ ዋልታዋም ባንቺ ተዋቀረ፣ ጭምጭሟም ባንቺ ተጨመጨመ፤ ደጆቿም ባንቺ ተከፈቱ፤ መቃን መድረኳም በልጅሽ ደም ተረጨ፤ድንግልን በጠራ ጊዜ ልጇን እየጠራ ልጇን የባህርይ መሰረት ሲያደርገው ድንግልን ደግሞ የፀጋ መሰረት ሲያደርጋት ነው። ክርስቶስ የለበሰው ስጋ የነሳው ነፍስ የድንግል ማርያም እንደሆነ ይናገር ዘንድ ይህን አለ።”

“የእውነተኛ ፀሐይ እናት ድንግል ማርያም ሆይ ላንቺ እገዛለሁ፤ ፍጥረት ሁሉ ላንቺ ይገዛልና፤ የልጅሽ ስም በሁሉ ከተነገረ ዘንዳ ያንቺ ስም ከዚያ ይነገራልና፡፡ የዓለም ሁሉ ክብር የነገስታትም ብዕላቸው ድንግል ሆይ ነገስታትና መኳንንት ዓለምም ሁሉ ከእግርሽ በታች ከጫማሽ ወድቀው ይገዛሉ፡፡”