Get Mystery Box with random crypto!

🌴🌴ባቡ ረያን ቻናል🕋

የቴሌግራም ቻናል አርማ babureyann — 🌴🌴ባቡ ረያን ቻናል🕋 ባ
የቴሌግራም ቻናል አርማ babureyann — 🌴🌴ባቡ ረያን ቻናል🕋
የሰርጥ አድራሻ: @babureyann
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 759
የሰርጥ መግለጫ

ሙስሊም በዚች ዱንያ ላይ እንደ መንገኛ ነው በዚህ መንገድ ሲያልፍ መልካምን የሰነቀ በርግጥም ታላቅ ማሸነፍን አሸነፈ‼
እንኳን ወደ ቻናሌ በሰላም መጣቹ የመንገድ ጓዶቼ
ወደ አላህ ከጠራ መልካምንም ከሰራ እና እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለ ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማነው
@ashabu_babureyan የመወያያ ግሩፓችን ነው
አስተያየቶን @akhlakibot ላይ ያስቀምጡልን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 08:57:44 <ይሄ የትኛው ዲንነው?> ሲል ጠየቀ... ይሄ አጋጣሚ ለዛ ሰው መስለም ምክኒያት ነበር ይባላል። የኛ ዲን ይሄ ነው ኢኽዋኒ... <ሶፍፋችሁን አስተካክሉ። ቀልቦቻችሁ እንዳይፋለሱ ረድፍ አታፋልሱ። አዋቂዎች ከኔ አጠገብ ይሁኑ። ከዚያም ከነርሱ (በደረጃ) የሚቀጥሉት ይለጥቋቸው> የሚለውን የሃቢባችንን ንግግር የተከተለ ውብ ዲን። በዒባዳም በዱንያም ሃጃዎች ተርቲብ የማይለየው ዲን። አላህ አኽላቃችንን አሳምረን በጀነት የሳቸውን ጉርብትና የምንወፈቅ ያድርገን። ንግግር አበዛሁባችሁ አፍወን... አሁን አስተካክላችሁ፤ እንደቅድሙ ሳትገፋፉ በሶፍፋችሁ መውጣት ትችላላችሁ...>> ተሰናብተውን ንግግራቸውን ቋጩ። ማሻአላህ... አጎቴ ይሄን አኽላቁን ያመጣው እንዲ ካለው ወዳጆቹ ፀባይ መሆኑን ተገነዘብኩ። ከኋላችን የነበሩት ሰዎች ተስተካክለው በሶፍፎቻቸው ሲወጡ የኢማሙ ንግግር ልባቸው ላይ መፃፉ ያስታውቅ ነበር። አጎቴ ወደሳቸው ሲያመራ... እኛ ደግሞ ተራችን ደርሶ መውጣት እስክንችል መጠባበቅ ቀጠልን።
*
*
ይቀጥላል...

@babureyann
@babureyann
15 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 08:57:06 መካሪም
(ክፍል አስራ ሰባት)
(ያስ ሁዳ)
.
.
<<አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ... አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ...>> ኢማሙ አሰላምተው የጁምዐን ሰላት አጠናቀቁ። እነሱን ተከትለን እኛም ሰላታችንን ጨረስን። ኢማሙ ዱዐዕ እና ተስቢህ አድርገው ከጨረሱ በኋላ አጭር ንግግር አስከትለው <<... ሁላችሁም በሶፍፎቻቹ ሰልፎች ነው የምትወጡት፤ እንዳትገፋፉ... እጅብ ብላቹም እንዳትወጡ። ሰሞኑን ያለብንን ፊትና የምታውቁት ነው... ስለዚህ ራሳችሁን ጠብቁ...>> የሚል ማሳሰቢያ አከሉበት። በየቦታው የተገደበ የሰው ቁጥር በመወሰኑ 100 የማንሆን ሰዎች ተራርቀን ነበር የሰገድነው። ስንወጣም 'ብዙ ሰው ገብቷል፤ ለጤናም አስጊ ነው' ብለው የሰላቱን መፈቀድ ተቃውመው አዛ ሲያደርጉን የነበሩት ደንቦች ለንግግራቸው ማስረጃ እንዳንሆናቸው ሲባል ተጠንቅቀን ነው የምንወጣው፤ አጎቴ እኔና ሪድዋንን ከቤት ጀምሮ አስጠንቶን ነው የመጣነው። እኛ የመጀመሪያው ሶፍ ላይ ስለነበርን እና አጎቴም ከኢማሙ ጋር መቆየት ስለሚፈልግ እኔ ሪድዋንና ሙህሲን በቦታችን እንደተራራቅን ተቀምጠን የሌሎቹን መውጣት መጠባበቅ ጀመርን። በመሃል የተወሰኑ ሰዎች ተቻኩለው ያለ ተራቸው ለመውጣት በሩ ላይ መሰባሰብ ጀመሩ... እነሱን ያዩ ሌሎችም 'እየተወጣ ከሆነማ አይቀር...' በሚል ስሜት መውጫው ላይ ግርታ ፈጠሩ። በደቂቃዎች ውስጥ በሩ ጋር ድምፆች በዙ፤ 'ሶፍህን ጠብቅ...' 'ምን አገባህ...' አይነት ጥል ይመስላል። ኢማሙ የሰዎቹ ንግግር አልሰማ ባይነት ያስቆጣቸው ይመስላሉ... ተነስተው ወደ በሩ አመሩ። እኛ ካለንበት ምን እንደተባባሉ አይሰማም... ብቻ ግን ሁሉም ወደየቦታው ተመልሶ ሲቀመጥ ተመለከትን።
.
<<ተመለሱ ብለዋቸው ነው?>> ሪዱ ግራ በመጋባት እያየኝ፤ ከሙህሲን ጋር እያወሩ የተፈጠረውን አላስተዋሉም። ትከሻዬን ወደላይ እየሰበቅኩ እንደማላውቅ ነገርኳቸው። ኢማሙ ከሁላችንም ፊት ቆመው ኢስላማዊ ሰላምታ ከሰጡ በኋላ ንግግራቸውን ጀመሩ።
<<... ጥያቄዬን አክብራችሁ ልታዳምጡኝ ስለተመለሳችሁ ጀዛኩሙላህ።>> ንግግራቸውን ገታ አድርገው በአይናቸው ካሰሱን በኋላ <<አፍወን የቅድሙ ሰው የት ሄደ?>> ከመሃከላችን አንዱን ጠየቁት።
<<ወጥቷል ኡስታዝ...>> መለሰላቸው። ኢማሙ ፈገግ እንደማለት አሉና...
<<...አዪ...ኸይር እሺ... በጣም ቸኩሏል አላህ ሃጃውን ያግራለት... አሁን የምነግራችሁ ግን ለሁላችሁም ነው። እሱ ሶፍፉን ቀይሮ ቀድሞ ለመውጣት ስለቸኮለ ብቻ ብዙዎቻችሁ አላስፈላጊ ትርምስ ውስጥ ገብታችኋል። ተሰግዶ እንዳለቀ ተምቢህ የሰጠሁት አሁን የተፈጠረው እንዳይፈጠር ነበር.... ግን ኸይር፤ ከዚ በኋላ እንዳይደገም መስራት ነው። ለምዶብናል መሰል ሁሉም ቦታ እንደ እንስሳ እንጋፋለን አሁን ላይ...>> የብዙዎች የሳቅ አይነት ድምፅ ተጉረመረመ። <<አይደለም እንዴ? አዎ... አጂብ ሃታ መስጂድ ውስጥ! ይሄኮ ዲናዊ አደብ አይደለም... ኢስላም እኮ ለሁሉም ነገር ተርቲብ ያለው ዲን ነው። እንኳን ለሰው ልጅ ቀርቶ ለፀሃይና ጨረቃ መፈራረቅ ሳይቀር ቅደም ተከተል ያለው ዲን ነው።

لَا ٱلشَّمْسُ يَنۢبَغِى لَهَآ أَن تُدْرِكَ ٱلْقَمَرَ وَلَا ٱلَّيْلُ سَابِقُ ٱلنَّهَارِ وَكُلٌّ فِى فَلَكٍ يَسْبَحُونَ

{ፀሐይ ጨረቃን ልትደርስበት አይገባትም፡፡ ሌሊትም ቀንን (ያለ ጊዜው) ቀዳሚ አይኾንም፡፡ ሁሉም በመዞሪያቸው ውስጥ ይዋኛሉ፡፡} አይደለም እንዴ ያለው አላህ (ሱ.ወ) በቁርዐን ላይ? ፀሃይ እንደኔና እንደናንተ ቸኩላ ሌሊት 6 ሰዐት ላይ ካልመጣሁ ብትል የሚከተለው ችግር ይታያችሁ...>> ብዙዎቹ አስበውት ሳቁ፤ እኔንም ፈገግ አደረገኝ... ኢማሙ ረጋ ብለው በልዝብ አነጋገር ሰውን የሚማርኩ አይነት ናቸው። ለዛም ይመስለኛል ተመለሱ ሲባሉ ብዙዎቹ ሳይከራከሩ የተመለሱት።
<<አዎ በዙሪያችሁ ያለውን አለም ስርዐት ተፈኩር ስታደርጉ በጣም ነው የምትደነቁት።

وَحُشِرَ لِسُلَيْمَٰنَ جُنُودُهُۥ مِنَ ٱلْجِنِّ وَٱلْإِنسِ وَٱلطَّيْرِ فَهُمْ يُوزَعُونَ

{ለሱለይማንም ሰራዊቶቹ ከጋኔን፣ ከሰውም፣ ከበራሪም የኾኑት ተሰበሰቡ፡፡ እነሱም ይከመከማሉ፡፡} ለጦር በሚያመች መልኩ ይሰለፋሉ እንደማለት ነው። ሱብሃነላህ ጂኖችና አእዋፋት እንኳን ከኛ የተሻለ ስርዐት አክባሪ ናቸው። ከኛ በመጠን በጣም የሚያንሱት ጉንዳኖች ሳይቀር ያላቸውን ተርቲብ ተመልከቱት! ታዲያ እኛስ ኢኽዋኒ? ተያይተን የማይናገር ሰው ከሆነ፤ ወይም በአቅም ደከም ያለ ከሆነ ከፊት መጥተን እንገባለን። በልባችን የኛ ሃጃ ከዛ ሁሉ ህዝብ ሃጃ በላይ አስቸኳይ መሆኑን አምነናል... አላህ ያስተካክለን። ባንክ ላይ፣ ሱቅ ላይ... ለምንም ሃጃ በሰልፋችን መቆምና መጠበቅ አንወድም አይደል? ሳንወሻሽ... እኔም አልወድም በነገራችን ላይ...>> በድጋሚ ፈገግ አደረጉን
.
<<... ግን የዲኔ መገለጫ ስለሆነ ተገድጄም ቢሆን አከብራለሁ። መቸኮል ጥቅም የለውም... ወደ ሰላት ሲመጣ እንኳን መሮጥ የተጠላ ነው... ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት <ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር የዐረፋ ቀን ተንቀሳቀስኩ። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከበስተኋላቸው ግፊያ፣ ዱላና የግመል ጩኸት ሰሙ። በአለንጋቸው ምልክት ሰጡና:- <ሰዎች ሆይ! ረጋ በሉ። መልካም ነገር በመቻኮል አይሆንም> አሉ።> ብለውናል። አዎ በመቻኮል አይሆንም! አስቡት የሰው ልጅ ከተጣደፈ እንኳን መጣደፍ የሚገባው ወደ ጌታው ሲያመራ ነው። ወደ ሰላት መሮጥ ካልተፈቀደ ከአላህ ቤት ወጥተው ወደ ዱንያ ለማምራት መሮጡ ተገቢ ነው?

وَأَقْسِطُوٓا۟ إِنَّ ٱللَّهَ يُحِبُّ ٱلْمُقْسِطِين

{በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና፡፡} እኮ ነው የኛ መመሪያ... አይደለም እንዴ? እኛ ዛሬ ላይ ያለንበትን ግን ተመልከቱት። መስጂድ በር ላይ መቻኮል መገፋፋት... ዑምራ ላይ መገፋፋት... ሃጀረል አስወድ ላይ ሳይቀር ጥል ነው፤ ሽማግሌ ህፃን ብሎ ማገናዘብ እየጠፋ ነው። በአደብ መውጣት ብንችል ኖሮ እኮ እስካሁን ግማሾቻችሁ ቤቶቻችሁ ደርሳችኋል... ቸኮላችሁ.. ተገፋፋችሁ... ተጣላችሁ... በ 5 ደቂቃ ውስጥ የሚያበቃ የነበረውን ስርዐት በማበላሸታችሁ ይኸው 20 ደቂቃ ከኔ ጋር እንድትቆዩ በራሳችሁ ላይ ፈረዳችሁ... በርግጥ 20 ደቂቃ መገሰ'ፅ ይሻል ነበር?>> ብዙዎቻችን በሳቸው መገሰ'ፃችን እንዳስደሰተንና እንዲቀጥሉ በሚል አይነት አጉረመረምን።
<<... ሃሃሃ የኔንም ሰዐት ነው እንጂ የምትወስዱት ችግሩ። ለማንኛውም አንድ ዳዕዋ ላይ የሰማሁትን ታሪክ ላጫውታችሁና ላብቃ... ካስረፈድኩባችሁ አፉ በሉኝ፤ የቸኮላችሁ መውጣት ትችላላችሁ..>> ሁላችንም እንዲቀጥሉ ተስማምተን ተቀመጥን። <<መርሃባ... ሳትቸኩሉ ነው ስትጋፉ የነበረው... ሃሃሃ ኸይር ጥሩ። አንድ አውሮፓዊ ነው አሉ... በቲቪ ሃጅ የሚያደርጉ ሰዎች ሲተረማመሱ ይመለከታል። <እነዚህ ሰዎች ተስተካክለው ለመሰለፍ ምን ያህል ጊዜ የሚወስድባቸው ይመስልሃል?> ሲሉ ጠየቁት። <ሰዐታት> ሲል መለሰ። <እሺ አራት ፎቅ ሙሉ መሆናቸው ቢነገርህስ?> አሉት። <12 ሰዐት ይወስድባቸዋል> ሲል መለሰ። <አንዱ ከሌላው ሁሉም የተለያየ ቋንቋ ያላቸው መሆናቸው ቢነገርህስ?> አሉት። <መቼም ተስተካክለው አይሰለፉም> ሲል በእርግጠኝነት መለሰ። ትንሽ ቆይቶ ሙዐዚኑ አዛን ሲያሰማ ሁሉም በደቂቃዎች ውስጥ ሰፋቸውን አስተካክለው ተመለከታቸው፤ በጣም ተደነቀ።
17 views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:40:01 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ያ ጀመአ ለማስታወስ ያክል ነው
ነገ ሀሙስ ነው ይህንን ቀን ውዱ ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ይፆሙት ነበር ሱና ነው! !!!
ስራዎቻችንም ወደ ሰማይ ከሚወጡባቸው ቀናቶች አንዱ ነው የቻልን ሰዎች እንፁም ያልቻልንም ለሚችሉት ሼር በማድረግ አጅሩን እንሸምት ኢንሻአላህ
ረያን የተባለችዋ የጀነት በር ለፆመኞች ተዘጋጅታለች!!!!!!

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@babureyann
@babureyann
@babureyann
104 views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:43:32 መካሪም
(ክፍል አስራ ስድስት)
(ያስ ሁዳ)
*
*
ዛሬ ቤቱ ውስጥ ቀለል ያለ ሽምግልና አለ። ትልቅ ነገር እንዳታስቡ፤ አክስቴ አስማን ከወንድሟ ሚስት ጋር የተፈጠረባቸውን አለመግባባት ለመፍታት ያህል የአክስቴ አስማ ወንድም ቤት ስለመጣ ነው። ግጭቱ ቀላል ነው አሉ እንጂ ትንሽ ከበድ ሳይል አይቀርም። ዞሮ ዞሮ እነሱ ንግግራቸውን እስኪጨርሱ እኔና ሪድዋን ሂዱ ከመባላችን በፊት ዐሉን ይዘን ለመናፈስ ከቤት ወጥተናል።
*
<<ሪዱ... የማይመለከትህን ጠየቅህ አትበለኝና... በአክስቴ አስማ እና በዘይነብ መሃል ያለው ግጭት መች የተፈጠረ ነው?>> አንዱ ካፌ ጋር ደርሰን እንደተቀመጥን ግራ በመጋባት ጠየቅኩት።
<<አክስቴ ዘይነብ ናት ጥፋተኛ... ከዛ ኡሚ ሰደበቻት... ከዛ ስራዋ ሲበላሽባት ሁለተኛ አንቺ ቤት አልመጣም ብላ አክስቴ ኡሚን ሰደበቻት። ከዛ በቃ አይነጋገሩም...>> ዐላዕ ቅልቅል እያለች ተሽቀዳድማ መለሰችልኝ።
<<እስኪ አትቅለብለቢ ግማሽ የሆንሽ...>> ሪዱ ብስጭት እያለባት።
<<ልክ ናት ሪዱ?>>
<<ኧረ ምን ልክ ናት... ማለት ኡሚ እንደተናገረቻት ልክ ናት... ግን እሷ እንዳለችው አይደለም።>>
<<እና?>>
<<ምን መሰለህ... አክስቴ ዘይነብ የሴት ልብሶች ከውጪ በሰዎች አስመጥታ እዚ ታከፋፍላለች። አንድ ቀን፤ እንዲ መስጂዶች ውስጥ መሰባሰብ ሳይከለከል በፊት ኡሚና እሷ መስጂድ ጁምዐ ሰግደው አብረው ሌላ ቦታ ለመሄድ ተቀጣጥረው ነበር። ኡሚ መስጂድ ስትገባ አክስቴ ቀድማ ደርሳ ሰላቱ እስኪጀመር ብላ የተወሰኑ ጨርቆችን እዛ ላሉት ሴቶች ስታሳይ አገኘቻት። ከዛ 'አላህ ንግድሽን ትርፋማ አያድርገው...ምን እየሰራሽ ነው መስጂድ ውስጥ' ብላ ተቆጣቻት። በዚ ትንሽ ተነጋገሩ... አክስቴም እንዴት ትረግመኛለች ስለምትጠላኝ ነው ብላ አኮረፈች። በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአጋጣሚ አላህ አዞበት ስራዋ ኪሳራ ገጠመው። 'ባንቺ አፍ የመጣብኝ ነው..' ብላ ኡሚን ብዙ ተናገረቻት። ከዛን ጊዜ ጀምሮ እሷም እኛ ቤት አትመጣም ኡሚም እሷ ጋር አትሄድም... 4 ወር ሊጠጋቸው ነው።>>
<<በዚ ብቻ ይሄን ያህል ጥል? አጎቴ እንዴት ዝም አለ...>>
<<ኧረ ብዙ ጊዜ ሊያስታርቅ ሞክሯል፤ አክስቴ እምቢ እንዳለች ቀረች እንጂ።>>
<<አክስቴ አስማ ራሷ ግን ልክ አይደለችም... ማለት ብትሸጥ ምን ችግር አለው?>>
<<እንዴ አድናን ምን ሆነሃል... መስጂድ ውስጥ? አይቻልም እኮ... የመስጂድ አደብ አይደለም።>>
<<የመስጂድ አደብ ስትል?>>
<<መስጂድ ውስጥ ስትገባ ብቻ የምትከተለው አደብ አለው። መስጂድ ማለት እኮ የአላህ ቤት ነው... የንጉስ ቤተመንግስት ስትገባ እንኳን እንዴት ነው? የራሱ አደብ አለው አይደል? መስጂድ ደግሞ የአላህ {ዐ.ወ} ቤት ነው፤ ከዛም የገዘፈ ክብር ሊኖረው ይገባል። አላህ {ሱ.ወ} ዘንድ ለአንዲት ከተማ በጣም የሚወድላት መስጂዶቿ መሆናቸውን ሙስሊም በዘገበው ሃዲስ ተላልፎልናል። ከአላህ ውዴታ የራቀ ቦታዋ ደግሞ ገበያዎቿ ናቸው ብለውናል፤ ምክኒያቱም ሰዎች አላህን ከማውሳት የሚዘናጉበት ስለሆኑ። ስለዚህ አላህ ከምንም ቦታ በላይ በሚወዳቸው መስጂዶቹ ውስጥ የምትከተለው አደብ ሊኖር ይገባል። ለምሳሌ ድምፅህን ከፍ ማድረግ አትችልም መስጂድ ውስጥ። ቡኻሪ በዘገበው ሃዲስ ኢብኑ የዚድ ምን ብለዋል...<<አንድ ሰው በጠጠር መታ አደረገኝ። ስመለከት ዑመር ኢብኑ አል-ኸጣብ ሆነው አገኘኋቸው። <ሒድና እነዚያን ሰዎች አምጣልኝ> አሉኝ። አመጣሁላቸው። <<የጧኢፍ ሰዎች ነን> አሉ። <የሃገሬ ሰው ብትሆኑ ኖሮ እቀጣችሁ ነበር። በአላህ መልዕክተኛ {ሰ.ዐ.ወ} መስጂድ ውስጥ ድምፃችሁን ከፍ ታደርጋላችሁን!?> >> ብለው እንደተቆጧቸው ነግሮናል። አንዳንዴ ደግሞ ጩኸቱ ቀርቶ ጎን ለጎን ስለሌላ ሃጃ የሚያንሾካሹኩ ሰዎች ታያለህ... አንዳንዴ ኹጥባ እየተደረገ ሳይቀር! በተለይ ሴቶቹ ጋር ይበዛል ትላለች ኡሚ... ብቻ እሱ በራሱ አደብ አይደለም።
.
ድምፅ ብቻ ሳይሆን አለባበሳችን ራሱ በደንብ የታሰበበት፤ ንፁህና ያማረ ሊሆን ይገባል ወደ መስጂዶች ስናመራ።

يَٰبَنِىٓ ءَادَمَ خُذُوا۟ زِينَتَكُمْ عِندَ كُلِّ مَسْجِدٍ َ

{የአዳም ልጆች ሆይ! (ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ፡፡} እኮ ነው ያለው ዙል ጀላል በቁርዐኑ ላይ። ንጉስ ፊት ስትቀርብ እንደምትጨነቀው አላህ ፊትም ስትቀርብ ንፅህናህ፣ አለባበስህ፣ ጠረንህ ግድ ሊሰጥህ ይገባል። ለአላህ {ዐ.ወ} ቀርቶ በዙሪያህ ለሚሰግዱትም መጨነቅ ስላለብህ አይደል እንደ ነጭ ሽንኩርት ያሉ ምግቦችን ተመግበን መስጂድ መግባት የተከለከለው?>>
<<እሱማ ልክ ነው... የመስጂድ አደብ ያልከው። ግን ከነአክስቴ ጥል ጋር ምን አገናኘው?>>
<<በደምብ ይገናኛል.. እነዚህ ያልኩህ ሁሉ አደብ እንደሆኑት ሁሉ፤ መስጂድ ውስጥ የጠፋን እቃ ማፈላለግ መገበያየት የመሳሰሉትን ዱንያዊ ሃጃዎችን መፈፀምም የተጠላ ነው። ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} <<መስጊድ ውስጥ ሲሸጥ ወይም ሲገዛ የተመለከታችሁትን ሰው:- <አላህ ንግድህን ትርፋማ አያድርገው> በሉት። የጠፋ እቃውን ሲያፈላልግ የተመለከታችሁትን ድግሞ <አላህ አይመልስልህ> በሉት።>> ማለታቸውን ሀሰን በሆነ ሃዲስ ተዘግቧል። መስጂዶች የተሰሩት ለአላህ ዒባዳ ብቻ ነው... ለሌላ ነገር ሲውሉ ከተመለከትህ መከልከሉ ግድ ይላል። ኡሚ ደግሞ የሰውን ጥፋት የማሽሞንሞን ትዕግስት ስለሌላት ቀጥታ ተናገረቻት።>> እንዲ እየተጨዋወትን ለኛ ያዘዝነው ማኪያቶና የዐሉ ሚሪንዳ ቀረበልን።
<<ጀዛከላህ... ስለ መስጂድ አደብ ይሄን ያህል አላውቅም ነበር... አንተ ግን ይሄን ሁሉ ሃዲስ ሸምድደህ ነው?>>
<<አዎ... ከወደድከው... ልክ አንተ ባለፈው ሳናግርህ የዘፈን ስንኞችን ሳልፈልጋቸው ነው የምይዛቸው እንዳልከኝ፤ እኔም እንደሰማኋቸው ቃል በቃል ባይሆንም ልቤ ላይ ተፅፈው ይቀራሉ። ድሮ ባባ ከደርስ ስንመለስ የሸመደድኳቸውን ያስደግመኝ ነበር። ከባድ ነው ግን ደጋግመህ ስትሞክር ይሳካል... እኔም በከፊል ተሳክቶልኛል>> ሳቅ እያለ። በዚሁ ተነስቶ ጥሩ ስለሚለው የቁርዐን ሂፍዝ ዘዴ ጠይቄው እያማከረኝ ሳናስበው ሰዐቱ ከነፈ።
*
ከቤት ከወጣን ከ 4 ሰዐታት በኋላ ተመለስን። አጎቴ የአክስቴን ወንድም ሊሸኘው አብረው ወጥተው ነበር። አክስቴ ፊቷ ፈካ እንዳለ በአሁኑ የእርቁ ጥያቄ የመጣው ከራሷው ከአጎቴ ሚስት ስለነበር ተግባብተው ተነጋግረው እንደፈቱት ነገረችን፤ አልሃምዱሊላህ። ወደ መኝታ ክፍሌ ተመልሼ ዐስርን ከሰገድኩ በኋላ ሪድዋን ጥሩ ነው ያለኝን የሂፍዝ መንገድ ለመሞከር የመጀመሪያ እርምጃዬን ጀመርኩ።
*
*
ይቀጥላል...

@babureyann
@babureyann
50 views04:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:50:25
ኢትዮጵያ!(ሀበሻ)
እሷ የእውነት ምድር ነች!"
< ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)>

አላሁመንሱርና ፊ በለዲ ኢትዮጵያ!

የቢላልን ሀገር የነ ነጃሺን በዕዝነት አይንህ እያት አንተው ያረህማን

@babureyann
88 views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:31:34 ከአንተ ውጪ ማን አለን ያ አላህ

አባታችንን ከአፈር አንስተህ ሰው አደረከው
እኛን ከደካማ ፈሳሽ አስገኝተህ ሰው አደረከን
ሪዝቃችንን እራሱ ማግኘት የማንችል ስኖን አስመቸህልን
ከእንስሳት የተሻልን እንድንሆን አእምሮ ለገስከን
የተፈጠርንለትን አላማ እንዳንረሳ ሙስሊም አረከን
ተቆጥሮ የማያልቅ ፀጋን ሰጠሀን
እልፍ አእላፍ ምስጋና ይገባህ

አላህ ሆይ ሩሀችን ከኝ ተለይታ ሰዎች በሚያጥቡን ቀንም እዘንልን
በጨርቅ ጠቅልለው ጉርጓድ ውስጥ ሲያስገቡንም እዘንልን
አፈሩን በላያችን ላይ ሲመልሱም እዘንል
ከዛ ቡሀላ ላለውም ከኛ ጋር ሁን
አላህ ሆይ በዚያ ቀንም ከኝ ጋር ሁን

ካንተ ውጭ ማን አለን ያ አላህ!!!!!

@babureyann
@babureyann
@babureyann
122 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:30:12 #3 አል-ወዱድ

ትርጉም:- ባሮቹን የሚወድ(የሚያፈቅር) ባሮቹም እሱን የሚወዱት(የሚያፈቅሩት)

ልቤ ለመውደድ ቅርብ ለመጥላት ደግሞ እሩቅ ነው። በውበታቸው አልያም በመልካም ባህሪያቸው የወደድኳቸውን ሰወች ታምራላችሁ አልያም እወዳችኋለሁ ብሎ ለመናገር አልሰስትም።ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ለምትወዱት ሰው መውደዳችሁን ንገሩት አይደል ያሉት? ምን አልባት ይህን ስሜቴን የማልገልፀው ተቃራኒ ፆታ ከሆነ ነው(ያው ታቃላችሁ ለነሱ ከተናገራችሁ የሚከተለውን) ታድያ ውዴታዬን እና አድናቆቴን በመንገሬ ብዙ ሰወችን አፍርቻለሁ (የኮሩብኝም ሳይረሱ)። ከወደድኳቸው፣ ውዴታዬን ባማረ ቃል ከነገርኳቸው ሁሉ የወዱድ ግን ይለያል። በልጅነት እድሜዬ ገና ፍቅሩ ሲጀምረኝ አላህን ምን ያህል ትወጅዋለሽ? ሲሉኝ ለአፌ ከሁሉም አስበልጬ እላለሁ እንጂ ከውዷ እናቴ እንኮን አስበልጬ አልወደድኩትም ነበር። ስለሱ ያለኝ እውቀት ሲጨምር የእውነት እየወደድኩት ፣የእውነት እየናፈቅኩት መጣሁ።ያፈቀሩትን ማስከፋት ያለውን ህመም ትዕዛዙን በጣስኩባቸው እያንዳንዱ ደቂቃዎች ታመምኩት፤ያፈቀሩትን መናፈቅ ያለውን ስቃይ ለማስረዳት ከከበደው ማንኛውም ሰው በላይ ተረዳሁት፤ እኔ ብቻ የምወደው፣የማፈቅረው፣የምናፍቀው መስሎኝ ስብሰለሰል ከስሞቹ አንዱ እኮ ወዱድ ነው ከአንቺ አስቀድሞ በጣም ይወድሻል ሲሉኝ እሷ ጋር ብቻ ያለ ስሜት መስሎት ስትብሰከሰክ የነበረች ሴት ያፈቀረችው ሰው በጣም አፈቅርሻለሁ ብሎ ቀድሞ ሲነግራት ደስታዋ ወደር አጥቶ ከምታነባው እጥፍ በደስታ አነባሁ። እንደሚወደኝ፣ ከእንስፍስፏ እናቴ በላይ እንደሚያዝንልኝ ፣ሲወደኝ እንደኔ ለደካማ ፍጡር ሳይሆን ለመላዕክቶች ዋና ለታላቁ ጅብሪል እንደሚነግር ስሰማ ደስታዬን በቅጡ ሳላጣጥም የናፍቆት ማዕበል ያላትመኛል። ሲከፋኝ ከእቅፎ ስር ተወሽቄ እስኪቀለኝ ከማለቅስበት የእናቴ የሞቀ እቅፍ በላይ መስገጃዬ ላይ ተደፍቼ ለሱ መንገር ህመሜን ያቀለዋል። በእምባ እርሼ ወዱድ የሆነው ጌታ እያየኝ እንደሆነ ሳስብ የምትወደውን ሰው ትኩረት ማግኘቷን ስታውቅ በደስታ የምታደርገው ከሚጠፋት እንስት በላይ የማደርገው ይጠፋኛል፤ ልዩነታችን እሷ እራሶን ለማስዋብ ስትጥር እኔ ግን ፍቅሬ እና ናፍቆቴ ብሶ ውስጤ የታፈነው ብሶት እና ደስታ ይባስ በእምባ ያጥበኛል። የመልካም ስራዬ ማነስ እና የሀጢያቴ ብዛት ከጀነት ተስፋ ሲያስቆርጠኝ አል-ወዱድ የሆነው ጌታ በምትወደው ባሪያው ባንቺ ጨክኖ የሚንቀለቀል የጀሀነም እሳት እንዲያከስልሽ ፣ስትናፍቂው የኖርሽውን የሱን ፊት ከልክሎ የዘለአለም ስቃይ እንዲውጥሽ አያደርግም፤ ባንቺ አይጨክንም።
ውዴታው እንደሰው አይደለም! አጠፋሽ ብሎ የናፈቅሺውን ፊቱን አይከለክልሽም፣ ጨክኖ እሳት አይወረውርሽም፤ ምክንያቱም ወዱድ(የሚወድ) ጌታ ነው ይሳሳልሻል እላታለሁ።
የናፈኩትን ፊትህን ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) እንዳበሰሩን ጀነት ውስጥ እስካየው የእውነት ያፈቀረ ባሪያህን ተግባር እንድታላብሰኝ እለምንሀለሁ።

ያወዱድ ናፈቅከኝ....

rehima hussen

@babureyann
@babureyann
@babureyann
111 views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:12:23 መካሪም
(ክፍል አስራ አምስት)
(ያስ ሁዳ)
*
*
<<ምነው አመሻቹ?>> አክስቴ እንደገባን ደንግጣ እያየችን፤ ስትደውል እኔም አጎቴም አላነሳንላትም ነበር። ከስንት ንትርክ ተርፈን እንደመጣን አላወቀችም... ኧረ ምን ንትርኩ ብቻ ከሞትም ጭምር ነው የተረፍነው። ሌላኛው መኪና በመጨረሻው ሰዐት ፍሬን መያዝ ባይችል ኖሮ አሰቃቂ አደጋ ነበር የሚደርሰው... የኛ መኪና ግን ከሱ ሽሽት አንዱ ፖል ጋር መጋጨቱ አልቀረም። ዐሉ ብቻ ከፊተኛው ወንበር ጋር ተጋጭታ ሲነስራት ነበር... ሌሎቻችን ደህና ነን። አጎቴ፣ የዛኛው መኪና ሹፌር እና የኛ ሹፌር ሲጨቃጨቁ.... እኔ ደግሞ የዐሉን ደም ለማስቆም እየሞከርኩ ሳረጋጋት ነበር የቆየነው። በስተመጨረሻም ሌላ መኪና ጠርተን ተመለስን..
.
<<ደህና ነን አልሃምዱሊላህ... ትንሽ ችግር ተፈጥሮ ነበር ተፈቷል>> አጎቴ ድክም ብሎት መጅሊሱ ላይ አረፍ እያለ። ከአክስቴ ጋር ከተጣሉ በኋላ እንዲ ፊቱን ሲያጠቁር ሳየው የመጀመሪያዬ ነው።
<<ማማ ብታዪ ቅድም..>>
<<ሽሽሽ.. ዐላእ.. ደህና ነን... ግቢና ወደ ክፍልሽ አረፍ በይ፤ ደክሞሻል>> ወሬ ሲጋነን እና ሲቀባበሉ መስማት አይወድም። ዐሉ ተነስታ ወደ ክፍሏ ገባች። እኔም ወደ ክፍሌ ልገባ ስል አጎቴ ጠራኝ..
<<አድናን.. ሪድዋን... ኑ አንዴ...>> ሪድዋን ምን እንደተፈጠረ ግራ እየገባው ተጠጋ፤ እኔም ተመልሼ ተቀመጥኩ። <<እናንተ አሁን ወጣቶች ናችሁ... ወደፊት አላህ ካለ የየራሳቹን መኪናዎች ትይዛላችሁ... እስከዛም ድረስ ደግሞ እንደተሳፋሪ የየራሳችሁ ግዴታዎች አሉባችሁ... አይደለም?>> ኮስተር ብሎ ጠየቀን... አጎቴ ይቅር ብሎ የማያልፈው ነገር የለም፤ ዛሬ ግን በጣም አምርሯል.. ሁለታችንም ጭንቅላታችንን በአዎንታ ነቀነቅን።
<<ስለዚ ስትጓዙም ስትነዱም ህጎችን አክብሩ... የፍጥነት ወሰኑን ከሆነ የፍጥነት ወሰኑን... የመንገድ መብራቱንም ከሆነ እንደዛው። ይሄ የሀገሩ ህግ ስለሆነ ብቻ አይደለም... ኢስላምም አይቀበለውም... አኽላቅ አይደለም። ይሄ ቀልድ አይደለም... የሰው ህይወት የሚጠፋበት ነው!! መንገድ የራሱ ሃቅ አለው... ከነዛ መሃል አንዱ ከሌሎች ላይ ጉዳትን መከልከል ነው። ቅድም ስልህ እንደነበረው ፈሳድን መከልከል ነው። እንደፈለጋችሁ በፍጥነት አሽከርክራቹ ከተጋጫችሁ በኋላ "መብቴ ነው... ህይወቱም የራሴ መኪናዋም የኔ" ብሎ ነገር የለም!... መብራት ሳታዩ መኪና ላይ እየገባችሁ "የራሴ ሰዉነት ነው ማንንም አልጎዳሁም" ብሎ ቋንቋ አይሰራም!... ህጎች አሉ... ራሳችሁን እንዴት መጠበቅ እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ... ስለዚ ግድየለሽ አትሁኑ፤ የአክላቃችሁን መጓደል ነው የሚያመላክተው።

وَلَا تُلْقُوا۟ بِأَيْدِيكُمْ إِلَى ٱلتَّهْلُكَةَِ

{በእጆቻችሁም (ነፍሶቻችሁን) ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡} ብሏል አላህ {ሱ.ወ} በቁርዐን ላይ... ወደ ጥፋት በሚያመራችሁ ነገር ላይ መብት ብሎ ነገር የለም!

وَعِبَادُ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى ٱلْأَرْضِ هَوْنًا

{የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት...ናቸው፡፡}... አለቀ! እንደ አሽከርካሪም እንደ መንገደኛም ህጉን ጠብቀን ሌሎችን ሳናሸብር በዝግታ መሄድ ነው አደቡ... በአላህ ዘንድ የሚስመነዳው እሱ ነው። እናንተ ወጣቶች ናችሁ... ወደፊት ደግሞ ገና ብዙ ፈተና ይጠብቃችኋል። አንዳንዶቹ ጓደኞቻቸውን ለማስደንገጥ ብለው አጉል ሙከራ ሲያደርጉ... ሲቸኩሉ... አልያም በስሜት ሲያበሩ ነው አደጋዎች የሚከሰቱት። <ሙስሊም ሙስሊምን ሊያስደነግጥ አይፈቀድለትም።> ብለውናል ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}... ስናሽከረክር አብረውን ለተሳፈሩትም ቀልብ ጭምር ማሰብ ጥሩ ነው። አደጋ ባይደርስ እንኳን በነሱ ጭንቀት እኛ ላይ ጥፋት ይመዘገባል! በሌላ ሀዲስ ደግሞ <ወደ ወንድሙ በመሳሪያ የጠቆመ እስከሚታቀብ ድረስ መላእክት ይረግሙታል።> ብለው አስጠንቅቀውናል። ለምን ይመስላችኋል? ምክኒያቱም ለቀልድም ቢሆን በመሃል ሸይጧን አለና አደጋ እንድታደርሱ ሊያደርጋችሁ ይችላል። ለቀልድ ብላችሁ ጓደኛችሁን ስትገፈትሩት የመኪና ሲሳይ ሊያደርገው ይችላል። ለመደሰት ብላችሁ በፍጥነት ስታሽከረክሩ እናንተንም... ከፊታችሁ የሚገባውንም ሰው... አብሯችሁ የተሳፈረ ሰውን ነፍስም እንድታጠፉ ሊያደርጋችሁ ይችላል። ያለጥፋቷ የጠፋች ነፍስ ደግሞ አላህ ዘንድ ቅጣቷ ከባድ ነው!

مِنْ أَجْلِ ذَٰلِكَ كَتَبْنَا عَلَىٰ بَنِىٓ إِسْرَٰٓءِيلَ أَنَّهُۥ مَن قَتَلَ نَفْسًۢا بِغَيْرِ نَفْسٍ أَوْ فَسَادٍ فِى ٱلْأَرْضِ فَكَأَنَّمَا قَتَلَ ٱلنَّاسَ جَمِيعًا وَمَنْ أَحْيَاهَا فَكَأَنَّمَآ أَحْيَا ٱلنَّاسَ جَمِيعًا َ

{በዚህ ምክንያት በእስራኤል ልጆች ላይ እነሆ ያለ ነፍስ (መግደል) ወይም በምድር ላይ ያለማጥፋት (ካልሆነ በስተቀር) ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው ማለትን ፃፍን}... ብሎናል ጀባሩ። በያዝነው መኪና ንዝህላል መሆን ውጤቱ የአንድ ቤተሰብ መበተን ሊሆን ይችላል፤ ያን ያህል ከባድ ነው! ያ የጠጣ ሹፌር እንደዛ መኪናውን ባያበር ኖሮ ምናልባት አህመድም ዛሬ...>> ንግግሩን ሳይጨርሰው አቆመው። በስሜት አወጣው እንጂ እስካሁን የተረበሸበትን ምክኒያት ላለመናገር አፍኖ ይዞት ነበር... እኔን ላለመረበሽ ሲል። እሱ እስኪለው ድረስ ልብ አላልኩም ነበር... ለካ ባባን የቀማኝ ያ የተረገመ አደጋ ነው! ያ ሁሉ መዘዝ... የኔና የማማ ስቃይና እምባ... የአባትን ፍቅር የማጣቴ ምክኒያት የዛ ሹፌር ግድ የለሽነት ነው! አጎቴ ወንድሙን ከምንም በላይ ይወደው እንደነበር ማማ ብዙ ጊዜ ነግራኛለች... ድንገት ስላጣው 4 አመት አልፎትም የመኪና አደጋ ጉምዝዝ ይለዋል። ሳስታውሰው እንደ አጎቴ ፊት ሁሉ የኔም ፊት ጥቁር አለ... የሃላፊነት ስሜት የጎደለው ሹፌር!
<<አፍወን አድናን... በጣም ተረብሼ ስለነበር ነው።>>
<<አብሽር አጎቴ... ልክ ነህ ጥንቃቄ የሚፈልግ ነገር ነው።>>
<<እናንተም ራሳችሁን ጠብቁ... እንደ እግረኛም ወደፊት እንደ ሹፌርም። ቅጣቱ በሁለቱም አለም የሆነ ከባድ ነገር ስለሆነ.. ሰው ባትገሉ አካል ታጎድላላችሁ... በሱም ትጠየቁበታላችሁ። ነፍስን ማጥፋት ደግሞ የከፋ የአኼራ ቅጣት ይጠብቀዋል... የሟች ቤተሰቦችም ይተሳሰቧችኋል>> ንግግሩን ጨረሰ።
.
በዝምታ ትንሽ ከተቀመጥን በኋላ አክስቴ ምን እንደፈጠረ በቀስታ ጠየቀችው... ተረጋግቶ ሊደርስብን ስለነበረው አሰቃቂ አደጋ ያስረዳት ጀመር። እኔ የባባ ሀዘን ድጋሚ ስለተቀሰቀሰብኝ አስፈቅጃቸው ትንሽ አረፍ ለማለትና ለመረጋጋት ወደ መኝታ ክፍሌ አመራሁ። አጎቴ ልክ ነው... ያ ሹፌር የኔና የማማ ሃቅ ይከተለዋል። ልርገመው... ወይስ አጎቴ ከሳምንታት በፊት እንዳለው አውፍ ልበለው? ከራሴና ከእምባዎቼ ጋር እየተሟገትኩ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ።
*
*
ይቀጥላል...

@babureyann
@babureyann
110 views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:51:53 "ቢቢቢቢቢጵ..." መኪናው ክላክስ እያሰማ በፍጥነት አቅጣጫውን ሲቀይር ብንን አልኩ። ልቤ በፍጥነት ይመታል... ዐሉ ትጮሃለች... የኛ ሹፌር ከሌላኛው መንገድ ያልጠበቀው መኪና ሲገባበት መኪናዋን ወዳልተፈለገ መስመር አዞራት... ከሌላኛውም አቅጣጫ ሲያበር የነበረ መኪና በራሱ መንገድ ስንገባበት ለማቆም ይታገላል...

"ሲጢጢጢጥ".....ኢላሂ!!!


ይቀጥላል...

@babureyann
@babureyann
138 views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:51:53 መካሪም
(ክፍል አስራ አራት)
(ያስ ሁዳ)
*
የማይቀረው ክልከላ እዚም አገር ተጠናክሮ ከታወጀ ቀናት አልፈዋል። ለመኪናዎች መውጫ ሳይቀር ፈረቃ በመቀመጡ አጎቴ አንዳንድ ቀን በመኪናው አንዳንድ ቀን ደግሞ በታክሲ ሆኗል ወደ ስራው የሚሄደው። ዛሬ ግን ከስራ ቀርቶ እኔና ዐሉን ለማንሸራሸር እቅድ ይዟል። ሪድዋን ጓደኛው ቤት ምሳ ተጋብዟል... አጎቴም ለዛ ይመስለኛል እንድንወጣ የፈለገው፤ እንዳይደብረን።
.
አጎቴ በሌላ ሰው መኪና መሄድ አይወድም መሰለኝ፤ አልያም እኔንጃ... ብቻ ምቾት አይታይበትም። በነገራችን ላይ ህጉ የሰውንም ቁጥር ይገድባል። አጎቴ ዐሉን ይዞ በአንድ ጎን... እኔ ደግሞ በሌላኛው ጎን ተቀምጠናል፤ የሚፈቀደው 2 ሰው በመሆኑ። ዐሉ አጎቴ እግር ላይ ተቀምጣ ከፊቷ ያለውን መቀመጫ ወንበር በእጇ ትልጠዋለች።
<<ዐላዕ!>> አጎቴ እጇን ከወንበሩ ላይ እያስለቀቃት። ለጊዜው ታርፍና ረዥም ሰዐት ተጉዘን ረስታው ትቀጥላለች። እንዲሁ እንዳልን ወደ መዝናኛው ደረስን። ዐሉ ገብታ ስትጫወት እኛ ደግሞ ለሷ መጫወቻዎች ሳንቲሞችን እየገዛን ስናወራ ቆየን። አንዳንድ ለትላልቆች የተዘጋጁ መጫወቻዎች ጋር እኔም ገብቼ ተጫወትኩ። ስንጨርስ ምሳ ሰዐት አልፎ ስለነበር መናፈሻውን ከሩቅ የሚያሳየን ቦታ ላይ ተቀምጠን መመገብ ጀመርን።
<<አድናን...እዛ ጋር ያለችዋን አበባ አየሃት?>>
<<የቷ?>>
<<ያ ቺ... ከሚስቀው ፎቶ ጎን ያለችው ቀዩዋ!>> በእጇ ጭምር ወደ መናፈሻው እየጠቆመችኝ።
<<እ... አየኋት፤ ምን ትሁን?>>
<<ቀጥፈህ አምጣልኝ... ማንም ሳያይህ...>>
<<ለምን ራስሽ ሄደሽ አትቀጥፊያትም?>>
<<እኔ ህፃን ስለሆንኩ ይቆጡኛላ!>> አንጀቴን ለመብላት እየሞከረች። ሁለታችንም መነሳት ስላልፈለግን እንጂ በአካባቢው ልብ የሚለን ሰው ያለ አይመስለኝም። ስንፎካከር አጎቴ ጣልቃ ገባ..
<<ሁለታቹም አትቆርጧትም። መብታቹ አድርጋቹት የምትገባበዙለት ስራ ልክ አለመሆኑ ገብቷችኋል?>>
<<የማንም አይደለችም እኮ ባባ... ደግሞ ጊቢው ውስጥ ብዙዙዙዙ አበቦች አሉ። ምንም አታጎልም...>> ዐሉ ንጭንጭ እያለች ጁሷን መጠጣት ቀጠለች።
<<ዐሉ ጠዋት ጀምሮ እያልኩሽ ነበር... የህዝብ መገልገያ ባለቤት የሌለው አይደለም። ባለቤቱ ሁሉም ነው... ያንቺ መገልገያ እንደሆነው ሁሉ የሌላውም ነው። ጠዋት የመጣንበት መኪና አንቺ ዛሬ አበላሸሽው... ነገ መኪናውን ለመጠቀም የሚመጣ ሰው መኪናው ላይ ያለውን ሃቅ በአግባቡ መጠቀም አይችልም።>>
<<ነባትና ሃያት ግን ትምህርት ቤት ጠረዼዛ ላይ ይፅፋሉ። እረፉ ስላቸው <ቀጣይ ሌላ ተማሪ ሲመጣ ስለሚፅፍበት እኛም መብታችን ነው> አሉኝ...>> ብቻዋን ጥፋተኛ መባል አትወድም። ድርቅናዋ ገርሞኝ መሳቅ ጀመርኩ።
<<ላ... አያስቅም አድናን። አንተ እዚ ስላልኖርክ ነው እኔን የሚያናድደኝ ነገር የማይገባህ! ባለፈው ስለ ቆሻሻው ስንነጋገርበት ትዝ ይልሃል አይደል? ልክ እንደዛው ሁሉ የመንግስትን ንብረት በማውደም ላይ ያልተሰማራ ዜጋ አታገኝም። በባስ ሄደህ አታውቅም አይደል? በታክሲም አልሄድክም እዚ ከመጣህ... በሚያስገርም ሁኔታ ሆነ ተብለው የተገነጠሉ የሚመስሉ ወንበሮች አሉ። በየ መስኮቶቹ የባስ ትኬቶች ተጠቅጥቀው መስኮት መክፈት አትችልም፤ ያውም በየስቴሽኑ እና እዛው ባሱ ውስጥ ራሱ መጣያ እያለ። በየታክሲው ወንበር ጀርባ አፀያፊ ጥቅሶችን ታነባለህ... በየመንግስት መስሪያ ቤት ግድግዳ ላይ ብዙ ውድመቶች ታያለህ። ምክኒያቱን ስትጠይቃቸው " ተወው መንግስት ይሄን ይሄን አድርጎ አማሮናል" ይሉሃል... ካልሆነም "ግብር ስለምከፍል ያው የኔው ገንዘብ ነው" የሚልህም አለ። ቤቱ ውስጥ ሰራተኛው እቃ ስትሰብር "ስበሪው የኔ ገንዘብ ስለሆነ ይጥፋ" የሚል የለም፤ ታዲያ የህዝብ ንብረት ላይ ለምን ይደረጋል? መኪናውን እያፈጠነ ወስዶ ከመብራት ጋር ካጋጨ በኋላ" እንኳንም ሰው ያልሆነ" ይልሃል... የመንገድ መብራቱ በመውደሙ ማታ እዛ ቦታ ላይ ለምትደፈር ሴት ሃላፊነት የለበትም? የሚያበሳጭህ እኮ ሙስሊሞቹም ማውደም ላይ ሲሰማሩ እንደ ጥፋት አለማየታቸው ነው። ይሄ የኢስላም አኽላቅ አይደለም... ይሄኮ አንድ የኢፍሳድ አይነት ነው። ዐዘ ወጀል በአሹዐራእ ላይ ሊኖረን ስለሚገባን አኽላቅ ሲያነሳ

وَلَا تَبْخَسُوا۟ ٱلنَّاسَ أَشْيَآءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا۟ فِى ٱلْأَرْضِ مُفْسِدِينَ

{«ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ላይ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ፡፡} ነበር ያለን። እኛ እየሰራን ያለነው ግን በተቃራኒው ነው! ልጆቻችንን በነቢና አኽላቅ ማሳደግ ተስኖን ጥፋትን እንደ መብት እስኪይዙት ድረስ... ወላህ ያሳፍራል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር መሆኑ ሳይሆን ሰው አይቷቸው እንዳይቆጣቸው ሆኗል የሚሰጉት። ነቢና {ሰ.ዐ.ወ} እኮ ሸይኽ አልባኒ ሀሰን ነው ባሉት ሃዲስ የሲድር ዛፍን የቆረጠ ሰው አላህ ሱ.ወ በጭንቅላቱ ወደ እሳት ይከተዋል ብለው ማስጠንቀቃቸው ይነገራል። የሲድር ዛፍ ሲሉ በአረብ ምድር የምትበቅለውን ጥላ ሰፊዋንና ፍሬያማዋን ዛፍ ብቻ ማለታቸው አይደለም፤ ልክ እንደሷ ሰዎች ለምግብ፣ ለመጠለል፣ ለማረፍ ወዘተ የሚጠቀሙባቸውን ማንኛውንም ዛፎች እያስታወሱን ነው። እነዚህን ዛፎች እንኳን ካለምክንያት መቁረጥ አላህን የሚያስቆጣ ሆኖ ሳለ እኛ ግን ይሄን መሰል ቅጣት መፍራት ቀርቶ ተቃራኒውን ማድረግ ላይ በርትተናል። ዛሬ አበባ ሲቆርጡ አናስቆማቸውም... ነገ ምንም ያላደረጋቸውን ዛፍ ገዝግዘው ይጥላሉ። ራህማኑ የኛን አኽላቅ ያስተካከለው ነቢና ሰ.ዐ.ወን በመላክ ከሳቸው እንድንማር በመምራት ነበር።

وَلَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ بَعْدَ إِصْلَٰحِهَا َ

{በምድርም ውስጥ ከተበጀች በኋላ አታበላሹ፡፡} ብሏል አል-አእራፍ ላይ። ምድርን ያበጃት ነቢና {ሰ.ዐ.ወ}ን ሲልክ ነበር... ሁሉም ነገር ከትላልቅ ዘንቦች እስከ ጥቃቅን ጥፋቶች ግልፅ ተደርጎ ከተቀመጠልን በኋላ ምንም አይነት ፈሳድ እንዳንሰራ አስጠነቀቀን። እኛ ግን እያደረግን ያለነውን ተመልከት...>> ብስጭት እያለ። ያናደደው ከዐሉ ጥያቄም በላይ እኔ እንደቀልድ ቆጥሬው መሳቄ ስለመሰለኝ ድንግጥ ብያለሁ። ለደቂቃዎች ዝምታ ከሰፈነ በኋላ አስተናጋጇ ሂሳቡን አምጥታ ዝምታችንን ሰበረችው። አጎቴ ረጋ ብሎ ስለ ጥፋትነቱ ለዐላዕ ያስረዳት ጀመር። በዚህ ሁኔታ ከቆየን በኋላ ሂሳብ ከፍለን ከካፌው ወጣን።
.
ዐላዕ አበባውን ለአክስቴ ስጦታ ልትሰጣት ፈልጋ መሆኑን ስለነገረችው ስንወጣ አንድ ትንሽዬ እቅፍ አበባ ገዛላት፤ በጣም ያምራል። እስከምንገዛ ራይድ ጠርቶ ስለነበር ብዙም ሳይቆይ ደረሰ። በቅድሙ አቀማመጣችን ተመልሰን ገባን... ዐሉ እጇ ከቅድሙ አረፍ ብሏል፤ ምናልባት በያዘቻቸው አበቦች ልቧ ተሰርቆ ነው። ሹፌሩ ከልክ በላይ ያፈጥናል..
<<ያ አኺ ቀስ በል... አልቸኮልንም>> አጎቴ ልቡ ስቅል ብሎበታል። ሹፌሩ ትንሽ ረገብ ያደርገውና መልሶ የፍጥነት መንገድ ላይ ያለን ይመስል ያበረዋል። ከሱም ብሶ በመሃል ስልክ ተደውሎለት ልቡ ወደ ስልኩ ተሰረቀ። ሊያነሳው ፈልጎ ትራፊክ በዙሪያው አለመኖሩን ለማረጋገጥ ያማትራል። እንደ ሌላው ቀን አጎቴ መንገዱን እያሳየኝ ልናወራ አልቻልንም። ዐሉ ከፊቷ ያለውን ወንበር ጭምድድ አድርጋ ከመያዟ መፍራቷ ያስታውቃል። ቅድም ስለ ፖል ያወራው ትዝ አለኝ...
137 views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ