Get Mystery Box with random crypto!

ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ mogesabreham123 — ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች
የቴሌግራም ቻናል አርማ mogesabreham123 — ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች
የሰርጥ አድራሻ: @mogesabreham123
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.38K
የሰርጥ መግለጫ

<<በተለያዩ ርዕሰ ጎዳዩች ላይ የሚሰጡ የስነ ልቦና ትምህርቶች( Psychology Lessons)እንዲሁም ጠቃሚ ምክሮች (Tips) ማህበረሰባዊ ፍልስፍናዋች( Social philosophies) የሚቀርቡበት ቻናል ነው>>ሞገስ አብረሀም
https://t.me/joinchat/AAAAAFNFGBxM7CRSIEwftg
@Mogesabreham

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-25 12:26:27 ቤተሰብህን ለመቀበል የሚያስፈሩ አበይት ነጥቦችን ለማንሳት እንሞክር
Important points to accept family

በኤልሳ(መጽሔተ ሕይወት)


ለልጅህ በቂ መሆን እንደማትችል ማሰብ(Thinking that you can't be enough for a child)

ሐላፊነት ለመቀበል ለልጅህ የሚሆን ሀይል እንደሌለህ ማሰብ
(Thinking that you dont have the strength respnsibility to the child)

ስራ የማጣት ፍራቻ (fear of jop loss) ወዘተ የሚመስሉ ችግሮች በህይወትህ ውስጥ ትልቅ ፍራቻ የሚያመጡብህ ነገሮች ናቸው።
ወዳጄ :- አሸወይናን ናፍቀው አግባ የሚሉህ ሰዎች የማህበረሰብ ደስታ ተመልካች እንይ የሚሉ ባዮች ናቸውና በህይወትህ ውስጥ እንዲገቡ አትፍቀድላቸው አባትነት ማለት ልክ አንተን እንደወለደክ አባት መሆን መቻል ነው ከሱ የወረስካቸው እያንዳንዱ ገጸባህሪያት ስትኖርባቸው ክፍ አባት ወይም የአለም ምርጥ አባት ትሆናለህ ምክንያቱም አንተ የአባትነት ድክመት ስላለብህ የምትወርሳቸው እያንዳንዱ ነገሮች የቤተሰብህ ተጽእኖች ናቸው።

  ወዳጄ:- አሁን አንተ የራስህን ጎጆ የምትቀልስበት እና የራስህ ዓለም የምትኖርበት ሰዓት አሁን ነው ለዚህም ደግሞ ማህበረሰቡ አንዱ የስነልቦናህ ጭንቀት ናቸውና ከነሱ ዓለም ለመራቅ ስትሞክር ቤተሰብ ምንያህል የፍቅር ዓለም መሆኑን ትረዳለህ።

  የአለም ምርጡ አባት ሆይ:-

ሚስትህን አክብር እና በፍጹም ፍቅርህን አትንፈጋት

ኋላቀር ንዴትህን የመተው ልማድን አካብት

ለልጆችህ የምታሳየው ባህሪህን ተጠንቀቅ

በቤተሰብህ እርግጠኛ ሁን

ያሳለፍከውን ህይወት ጥሩን ብቻ ተጠቀም

  ወዳጄ አንተ ዛሬ አባት ልትሆን ነው የልጅህንም መሰላል አጥብቀህ ያዝ ካለበዛያ የመሰላሉ አቀማመጥ ልጅህን ይጎደዋል።

https://t.me/AAAAAFEloxR
196 viewsMoges abreham, edited  09:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 19:21:16 ትርጉም የለሽ ፍልሚያ!

አንድ የከራረመ የጠቢባን ምክር እንዲህ ሲል አንድን እውነት ያስታውሰናል፡- “አሳማ መቆሸሽ በፍጹም አያስፈራውም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ቆሸሸም አልቆሸሸም ምንም ትርጉም ከሌለው ፍጥረት ጋር ‘የአቆሽሽሃለሁ … አታቆሽሸኝም’ አይነት ፍልሚያ ውስጥ ከመግባት ተቆጠቡ”፡፡

ቢሸነፉም ባይሸነፉም፤ ስማቸው ቢጠፋም ባይጠፋም፤ ቢከስሩም ባይከስሩም፤ ቢታሰሩም ባይታሰሩም፤ ምንም ግድ ከማይሰጣቸውና ምንም ነገር እንደማይጎድልባቸው ከሚያስቡ ሰዎች ጋር ፍልሚያ ይቅርባችሁ፡፡

ፍልሚያችሁን በጥንቃቄ ምረጡ፡፡ የምትመርጡት ፍልሚያና ከምን አይነት ሰዎች ጋር እንደምትፋጠጡ የምትወስኑት ውሳኔ ለራሳችሁ የሰጣችሁትን ከብር አመልካች ነውና

Dr.eyob mamo
373 viewsMoges abreham, 16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:14:34 የፍቅር ግንኙነትዎን ሊገድሉ የሚችሉ
ጉዳዮች(በሰብለወንጌል አይናለም)ዘሳይኮሎጂስት

የፍቅር ህይወት በተሞክሮ ውስጥ የምናልፍበትና በሂደት የምናዳብረው ክህሎት ነው፡፡ እንደ ሰው በፍቅር ግንኙነት ውስጥ መፈጸም የማይገባንና የፍቅር አጋራችንን ስሜት
ሊጎዱ የሚችሉ ስህተቶችን ልንፈጽም እንችላለን፡፡

ለምሳሌ፡ የጓደኛችንን የልደት ቀን መርሳት፡ በቀጠሮ ሰዓት መዘግየት፡ የፍቅር ጓደኛችንን የስጦታ ምርጫ አለማወቅናየመሳሰሉት ለጊዜው ቅሬታ ቢፈጥሩም፤ ተወቃቅሰንና
ተነጋግረን በይቅርታ ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ይሁን እንጂ የፍቅር ግኑኝነታችን ጤናማ ሆኖ እንዳይቀጥል የሚያደርጉና ቀጣይነቱን እንድንጠይቅ የሚያስገድዱን ስህተቶችም ይኖራሉ፡፡

የሚከተሉት አምስት ስህተቶች በፍቅር ግንኙነት ላይ አዳጋ ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጉዳዮች
ውስጥ ይካተታሉ፡፡

1. ምልዑነትን መጠበቅ (Expecting Perfection):-
ብዙዎቻችን ወደ ፍቅር ግንኙነት የምንገባው ፍቅረኛችን ውብ እንደሆነ/ች እና በሁሉም ነገር ደግሞ ብቁ እንደሆኑ አድርገን አስበን ነው፡፡ በጊዜ ሂደት ውስጥ የፍቅር አጋራችን ጉደለቶች መታየት ሲጀምሩ ያንን ሰው አስበነው ወደ ነበረው ምልዑነት ለመቀየር ግርግር
መፍጠር እንጀምራለን፡፡ ሰዎች ደግሞ በባህሪያቸው በማንነታቸው እንዳሉ ተቀባይነት እንዲያገኙ እንጂ “የመቀየር አለብህ/አለብሽ ” ግፊት ብዙም ምቾት አይሰጣቸውም፡፡ ለዚህ መፍትሄው የፍቅር አጋርዎን አሁን ባለበት ሁኔታ ሳያቅማሙ መቀበል፤ ሁሉም ሰው (እራስዎን ጨምሮ) ጉድለቶች እንዳሉበት መረዳትና
የፍቅረኛችንን ክፍተቶች እኛ መሙላት የምንችልበት መንገድ ካለ መሞከር የተሻለ ነው፡፡


2. መወስለት (Cheating)፡- ፍቅር በመርህ ደረጃ የሁለት ተቀራኒ ፆታዎች የአካልና የመንፈስ ውህደትን ይጠይቃል፡፡ ከፍቅረኛችን አሻግረን ሌላ ይምናይ ከሆነ፤ ይባስ ብሎም ከሌላ ተቃራኒ ፆታ ጋር የስሜት ትስስር
መፍጠር ወይም ወሲብ መፈጸም የፍቅር ግንኙነትን በፍጥነት ከሚገድሉ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ስህተት ውስጥ የገቡ ከሆነ ማድረግ የሚገባዎት የፈጸሙትን ስህተት ለፍቅረኛዎ ነግሮ፤ በቀጣይ መደረግ ስለሚገባው ጉዳይ መወያየት ነው፡፡ውስልትናን ከፍቅር ጓደኛ ደብቆ ማቆየት ቢቻልም በግንኙነታችን ላይ ተጽዕኖውን በተለያየ መንገድ ስለሚያሳርፍ ፍቅራችንን ይገድለዋል፡፡


3. ማኩረፍ (Silent treatment):- በፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመግባባቶችና ጸቦች ይከሰታሉ፡፡ ይሁን እንጂ ችግሮችን ለመፍታት የምንመርጠው መንገድ ማኩረፍ፤ ስልክ መዝጋትና መሸሽ ከሆነ የፍቅር ግንኙነታችን እየገደልነው ነው፡፡ ፍቅርን ጠብቀው ከሚያቆዩ ምሰሶዎች አንዱ ግልጽ ውይይት ነው፡፡ ንዴታችን እስኪበርድልን ጠብቀን በአልተግባባንበት ጉዳይ ላይ መነጋገር ወደተሻለ መንገድ ይመራናል፡፡ በተቃራኒው ያልተወያየንባቸው አለመግባባቶች በውስጣችን በተጠራቀሙ ቁጥር፤ ግንኙነታችን
በየጊዜው ይረበሻል፡፡


4. ውሸት (Lying ):-የፍቅር ግንኙነትን ጤናማነት ጠብቀው ከሚያቆዩ ነገሮች አንዱ ሀቀኝነት ነው፡፡ ማንኛውንም ጉዳይለፍቅረኛችን/ የትዳር አጋራችን በግልጽ የመናገር ልምድ ሲኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ነገር ግን ጓደኛችን በሆነ ጉዳይ ላይ ስንዋሽ ከያዘን/ከያዘችን በቀጣይ ለመታመን ዋስትና
የለንም፡፡ ለምሳሌ፡- ስራ ቦታ አምሽቼ ወደ ቤት
እየገባሁ ነው ያሉት አፍቃሪዎ ከሌሎች ጓደኞችዎ ጋር ካፌ ውስጥ ሲዝናኑ እንደነበር ቢያውቅ በሌላ ቀን ስራ ቦታ ቢያመሹ እንኳን የፍቅረኛዎን እምነት ማግኘት ይከብዳል፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን እውነቱን ብቻ
የመነጋገር ልምድን ማካበት ይኖርብናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር የመወያየት ባህል ቢኖረን ግንኙነታችን ይጠነክራል፡፡ ከፍቅር
አጋራችን ደብቀን የምንይዛቸው ጉዳዮች ካሉ በጊዜ ሂደት ግንኙነታችንን ሊያሻክሩ ይችላሉ፡፡


5. ቂም መቋጠር (Holding a grudge ):- ማንም ሰው ከስህተት የጸዳ አይደለም፡፡ ከዚህ በፊት የተሰሩ ስህተቶችንና ይቅርታ የተጠየቀባቸውን ጉዳዮች ሁልጊዜ እንደ አዲስ እያነሱ ፍቅረኛን መውቀስ፤ አንቺኮ ከዚህ በፊትም እንዲህ አድርገሽኛል፤ አንተኮ
ባለፈውም እንዲህ በድለኸኛል እየተባባልን
የምንነታረክ ከሆነ ፍቅራችንን ውሃ እያስበላነው ነው፡፡ ከቂምና በቀል ያልጸዳ ግንኙነት መሰረቱ ጽኑ አይሆንም፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ያለፉ ስህተቶቸን በይቅርታ መርሳት፤ ወደፊት ደግመው እንዳይከሰቱ ደግሞ መፍትሄ መቀየስ ያሻል፡፡


https://t.me/joinchat/AAAAAFNFGBxM7CRSIEwftg
449 viewsMoges abreham, edited  19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:20:42 በዘዴ መጨነቅ 1
(በነጋሽ አበበ ዘ-ሳይኮሎጂስት)


ጭንቀት ጨርሶ አስፈላጊ ነገር እንዳልሆነ የምንገልፅባቸው ብዙ ዓይነት ዘይቤዎች አሉን፡፡ “ሺህ ዓመት አይኖር” እንላለን፤ ድመቷም “ያው በገሌ ነው” ብላለች አሉ፡፡


ምንም እንኳን ከልክ በላይ የሆነ ጭንቀት አጥፊ ቢሆንም በልኩ የሆነ ጭንቀት ግን አልሚ እንደሆነ የሳይኮሎጂ ባለሙያዎች ያምናሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ብዙ ነገሮች አጥፊ የሚሆኑት ወሰናቸውን ሲያልፉ ይመስላል፡፡


ከዓመታት በፊት አንድ በግብፅ በረሀ ውስጥ ስለሚኖሩ ባህታዊያን አንድ መጽሐፍ እንዳነበብኩ አስታውሳለሁ፡፡


አንብቤ ከጨረስኩ በኋላ አሁንም ድረስ ውስጤ የቀረ የአንድ ትልቅ አባት አባባል አለ፡፡ “ከልክ በላይ የሆነ ነገር ሁሉ ከሰይጣን ነው” ይሰኛል፡፡ ልክ እንደዚሁ ሁሉ ከልክ በላይ የሆነም ጭንቀት የአእምሮ ህመምን ይወልዳል፡፡


አእምሮ ሲታመም መላ አካል፣ ማንነት፣ እና ሕይወት ይታመማል፡፡ ስራ ሰርቶ ውሎ መግባት ይከብዳል፤ ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ ልክ የለሽ ጭንቀት የስኬት ጠርም ነው፡፡ በጭንቀት ሀሳብ የተሞላ
አእምሮ ጥርት ባለ መንገድ ማሰብ አይችልም፤ የፈጠራ አቅሙ ዝቅተኛ ነው፤ ለሌሎች በቅርብ ርቀት የሚታይ ነገርለእሱ ከአድማስ በአሻገር የተቀመጠ ላም አለኝ በሰማይ ዓይነት ነገር ይሆንበታል፡፡


በሌላ በኩል ግን በመጠኑ መጨነቅ ጥቅም ይሰጣል፡፡ ይህንን ሊንዳ ፊልድ “Just do it now” የሚለው መጽሐፏ ውስጥ “በዘዴ መጨነቅ” ትለዋለች፡፡ ጭንቀቱ በቁጥጥራችን ስር ሆኖ የመፍትሄ እና መድኃኒት፣ ስኬት እና ሙላት፣ ጤናና ጥንካሬ ምንጭ መሆን ይችላል ማለት ነው፡፡
393 viewsMoges abreham, edited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 00:47:41 ለራሳችን መንገር የሌለብን 4 ነገሮች


የተለያዩ ችግሮች ውስጥ የምታልፉበት አጋጣሚ ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለችግሮቹም ራሣችሁን ተጠያቂ ታደርጉ
ይሆናል፡፡ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ
ብትሆኑም ግን ደካማነታችሁን የሚያጎሉና
ከሠዎች በታች ሆናችሁ እንድትታዩ የሚያደርጉ
ቃላትን መጠቀም የለባችሁም በማለት የሥነ-ልቦና ምሁራን ይመክራሉ፡፡ እነኚህ ቃላት አስተሳሰባችን ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የመፍጠር
አቅማቸው ከፍተኛ ነው፡ ፡


ለራሳችን የምንናገራቸው አሉታዊ ቃላት ከፍተኛ
ጉዳት እንዳላቸው ከሕይወት ልምዴ ተገንዝቤያለሁ የሚሉት የሥነ-ልቦና ባለሙያው
ማይክ ቡንድራንት በተለይ የሚከተሉትን ቃላት ለራሳችሁ ፈፅሞ መንገር የለባችሁም ይላሉ፡፡


1. የማልረባ ነኝ

ይህ በራስ መተማመናችሁን በቀጥታ የሚገድል አነጋገር ነው፡፡ የማትረቡ ወይም አንዳች ዋጋ የሌላችሁ መሆኑን ለራሳችሁ
መንገር አሉታዊ አስተሳሰብ በአእምሯችሁ እንዲሰርፅ የማድረግ ኃይል ስላለው ቃሉን መጠቀም ተገቢ አይደለም፡፡


2. አልችልም

አንዳንድ ነገሮችን በምትፈልጉት ደረጃ መስራት የማትችሉባቸው ሁኔታዎች በሚፈጠሩበት ጊዜ አቅማችሁን ልትጠራጠሩ ትችላላችሁ፡ ፡ የምታደርጉት ነገር ጥቅም እንደ ሌለው ለራሳችሁ መንገር ለሥራ ያላችሁን የተነሳሽነት ስሜት ይቀንሠዋል፤ አቅማችሁን ያሣጣችኋል፡፡ ይህ አነጋገር እውነታውን ከመግለፅ በላይ ራሳችሁን መልሶ የማጥቃት አቅም አለው፡፡ አንድ ነገር ከመሥራታችሁ በፊት እወድቃለሁ/ አይሣካልኝም ከማለት ይልቅ ደጋግሞ በመሞከር ለውጤት መብቃት እንደምትችሉ ማመን አለባችሁ፡፡


3. ሠዎች አይወዱኝም

ሠዎች አይወዱኝም የሚለውን ስሜት በአእምሯችን ማስረፅ ሌሎች ከእኛ የተሻሉ እንደሆኑ እንድናስብና ለራሳችን ጥረት
ተገቢ ውጤት እንዳንሠጥ ያደርገናል፡፡ በሌሎች ያለመወደድ ስሜት ከተሠማን ደግሞ ለራሳችን የምንሠጠው ክብርም ይቀንሳል::


4. ለውጥ ማምጣት አልችልም

አንድን ነገር ለመለወጥ አቅማችሁ ካልፈቀደ ራሣችሁን አታስገድዱት፡፡ ፍፁም መሆንንም ከራሣችሁ አትጠብቁ፡፡ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የምትሠጧቸው ሀሳቦች የራሳቸው
አዎንታዊ ተፅእኖ አላቸው፡፡ ስለዚህ ‹ለውጥ ማምጣት አልችልም›› የሚለው ቃል ለራሳችሁ መንገር ከሌለባችሁ አሉታዊ ቃላት መካከል አንዱ ነው፡፡


በአጠቃላይ ስሜታችሁን የሚጎዱ እንዲህ ዓይነት ቃላትንና አነጋገሮችን መጠቀም ትታችሁ አንደበታችሁን በመጠበቅ በየዕለቱ ለምታከናውኗቸው ተግባራት ትኩረት በመስጠት ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ፡፡



ምንጭ፡- Psychcentral.com
382 viewsMoges abreham, 21:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 20:46:25 ስብሃት ገብረእግዚአብሄር አንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፥

"በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ፤ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ፤ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ፤ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ፤ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ይችላሉ።"በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል።አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው
አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ
ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
"ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ፥ በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ፤ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡልችሀል፤ መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑችሁዋል። ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆናቹኋል፤ ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑላችሁዋል።
583 viewsMoges abreham, edited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:11:11 ጥያቄ፡-

ሰላም ዶ.ር ስለምታደርግልን መልካም ነገር ሁሉ እ/ር ውለታህን ይክፈልህ...

ዶ.ር የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ ሰወች ለምን አታገባም እያሉ ይጨቀጭቁኛል፣ማተራመስ ፈልገህ ነው ይሉኛል ...እኔ ግን ፍቅረኛ አጣሁ ምንም አሁን ላይ ሁሉም ሴቶች ከኔ ጋር ላለመሆን የተስማሙ እስኪመስለኝ ድረስ ብቼኝነት እየተጫወተብኝ ነው ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ገብቻለሁ...ማንም አይፈልገኝም የሚል ስሜት እያደረብኝ ነው...አቊሜ እና መልኬ ቆንጆ ከሚባሉት ብሆን እንጅ አስቀያሚ አይዴለሁም....ምን ላድርግ

መልስ፡-

ከሁሉ በፊት በአንድ ነገር እንስማማና፣ ትዳር መያዝ ያለብህ ለትዳር እድሜህ ስለደረሰ፣ ትዳር የመያዝ ፍላጎት ስላደረብህ፣ ለትዳር የምትሆን የፍቅር አጋር ስላገኘህና ወደጋብቻ ለመሄድ ትክክለኛው ጊዜ እንደደረሰ ስላመንክበትና የፍቅር አጋርህም ስላመነችበት ነው፡፡

ሰዎች “ለምን አታገባም” ስላሉህ መጨነቅና እንደዛ እንዳይሉህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብህ ማሰብ የማይሆን ውሳኔ ውስጥ እንድትገባ ይገፋፋሃል፡፡ ትዳር ከያዝክ በኋላ ያንን ትዳር እድሜ ልክህን የምትኖረው አንተ ነህ እንጂ ካላገባህ በማለት የሚነዘንዙህ ሰዎች አይደሉም፡፡

ሶስት ነገሮች በሚገባ እንደታጤን ላሳስብህ

1. ከላይ እንደጠቀስኩልህ የሰዎች ንዝነዛ ካስጨነቀህ ፍቅረኛ ለማግኘት ስለምትፍጨረጨር ሂደቱን ያበላሽብሃል፡፡ ትክክለኛ ምልከታና ምርጫ የሚኖረህ ካለምንም የውጪ ግፊት ተረጋግተህ ስትኖር ነው፡፡

2. የጠቀስከው “ድብርት” እና የመሳሰሉት ስሜቶች በራስህ ላይ ጫና ከማምጣታቸው ባሻገር ሰዎች በአንተ ላይ ያላቸውን አመለካከት ይነካዋል፡፡ የተጨናነቀ፣ የተደበረና ግራ የገባው ሰውን ለመቅረብ የማይፈልጉ ሴቶች ብዙ ናቸው፡፡ አሉታዊ ስሜቶችን ትተህ አዎንታዊ ስትሆን ጥሩ ጥሩ ሰዎች ከአንተ ጋር ለማሳለፍና አንተን ለማወቅ ክፍት ይሆናሉ፡፡

3. “አቋሜ እና መልኬ ቆንጆ” ነው ያልከውን አመለካከትህንም መለስ ብለህ አስብበት፡፡ ይህ አመለካከት በራሱ ምንም ችግር ባይኖውም፣ ምናልባት ብዙዎችን ሴቶች አይመጥኑኝም የሚል እሳቤ ይዘህ እንዳይሆን፡፡

በተረፈ፣ ሰዎች ስላንተ የሚያስቡትንና የሚናገሩትን ነገር፣ በሴቶች ላይ ያለህን አመለካከትና ሴቶች ሁሉ ያደሙብን ይመስለናል የሚሉትን የከረሩ ሁኔታዎች ረገብ አድርጋቸውና ራስህንና ዓላማህን በማግኘትና በማሳደግ ስትኖር ሁሉም ነገር ተከትሎ ይመጣል፡፡

ዶክተር ኢዮብ ማሞ

የዶክተር ኢዮብ ማሞን ስነልቦናዊ ጽሑፎች ለማግኘት እነዚህን ሊንኮች ይጠቀሙ።

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
738 viewsMoges abreham, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 22:24:49 ለውጡን ቀስ በቀስ አድርገው!

አንድ ትልቅ ድርጅት በወቅቱ ዋና ዳይሬክተር ስላልነበረውና መቅጠር ያስፈልገው ስለነበር የድርጅቱ ቦርድ ከብዙ ውይይትና አማራጭ ካመለከቱት ሰዎች መካከል የአንዱ ሰው የስራ ልምድና ብቃት ስለሳባቸው ይህንን ሰው ቀጠሩት፡፡ ይህ ሰው በጣም ተራማጅና አራማጅ፣ እንዲሁም ለውጥን የሚወድ ፈጣን ሰው ነው፡፡

በዚያ መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ጥቂት ከሰራ በኋላ አንድን በእንግዳ መቀበያው አካባቢ በአጉል ቦታ ለብዙ አመታት ተቀምጦ የነበረ ዴስክ ቦታውን ለመቀየር ፈለገ፡፡ ይህንን ሃሳቡን ግን ቦርዱ አላመነበትምና ብዙ ተከራከሩ፡፡ በመጨረሻ በራሱ ፈቃድ የዴስኩን ቦታ ቀየረው፡፡

በዚህ ምክንያት ቦርዱ ከተሰበሰበ በኋላ፣ ይህ ሰው እኛን የማይሰማን ከሆነ መባረር አለበት ብለው ስለወሰኑ አባረሩትና ሌላ ዳሬክተር ቀጠሩ፡፡

ይህ አዲስ ዳይሬክተር ገና ስራ እንደጀመረ ከታዩት ሁኔታዎች አንዱ የዚህ የዴስክ አጉል ቦታ መደንቀር ነበር፡፡ ስለሁኔታው ጸሃፊዋን ሲጠይቃት፣ “ይህንን ዴስክ ከዚህ ዘወር የሚያደርግልን ሰው ብናገኝ ጥሩ ነበር፡፡ ሆኖም፣ ከአንተ በፊት የነበረውን ዳይሬክተር እንዲባረር ያደረገ ዴስክ ስለሆነ ባትነካው ይሻልሃል” አለችው፡፡ ይህ አዲስ ዳይሬክተር ግን ብልህ ሰው ስለነበረ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቅ ነበር፡፡

አንድ ቀን ከብዙ ጊዜ በኋላ የቀደመው ዳይሬክተር ወደዚያ መስሪያ ቤት ሲመጣ እርሱ እንዲባረር ምክንያት የሆነው ዴስክ ከነበረበት ስፍራ እርሱ ቀድሞውኑ ሊቀይረው ወደነበረበት ስፍራ ተንቀሳቅሷል፡፡ በጣም በመገረም አዲሱ ዳይሬክተር ከቢሮው እስከሚወጣ በመጠበቅ ራሱን ካስተዋወቀው በኋላ፣ “ይህንን ዴስክ ከነበረበት ስፍራ አሁን ወዳመጣኸው ስፍራ ለመቀየር ሞክሬ በዚያ ምክንያት ነው ስራዬን ያጣሁት፡፡ ለመሆኑ እንዴት አድርገህ አንቀሳቀስከው? ቦርዱስ እንዴት ዝም አለህ?” በማለት ጠየቀው፡፡

መልሱ አጭርና ግልጽ ነበር፡- “ብዙ ጊዜ ቢፈጅብኝም፣ በየገዚው አንዲት ሴንቲሜትር ብቻ በማንፏቀቅ እዚህ አመጣሁት!” አለው፡፡ ዴስኩ ያለበትን አዲስ ቦታ ቦርዱ ያስተዋለው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነበር፡፡

እንደሚወራው ከሆነ አዲሱን ቦታ ስለወደዱት ነው ዝም ያሉት፡፡
አንዳንድ ጊዜ ማድረግ የምንፈልገው ነገርና ማምጣት የምንፈልገው ለውጥ ትክክለኛ ሆኖ ሳለ ካለአግባብ የምንጋጨው፣ ያሰብነውን ከማከናወን የምንገታውና ተስፋ የምንቆርጠው እኛ የታየንንና ሌሎቹ ያልታያቸውን ነገር በቶሎ ለማድረግ ስንሞክር ነው፡፡

ለውጥ ሂደት ነው! ለውጥ ጊዜን ይፈልጋል! ትልቅ ለውጥ በየቀኑ የሚደረግ የጥቂት ነገር ጥርቅም ነው፡፡ ስለዚህ፣ ከሰዎች ጋር መታገላችሁንና መከራከራችሁን አቁሙና ለውጡን ቀስ በቀስና ሰዎች በማያስተውሉት መልኩ “አንቀሳቅሱት”፡፡ ለውጡ ከመጣ በኋላ ጥቅሙንና ብልጫውን ሲያዩ ያን ጊዜ ሰዎች ይገነዘቡዋችኋል፡፡

Dr eyob mamo
739 viewsMoges abreham, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 22:31:39
ቅን የሆኑ ሰዎች ጠንካራ ስብእና ከገነቡ ሰዎች ውስጥ ይመደባሉ። ቅንነት የተጣመመውን ነገር አቃንቶ ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን መጥፎውንም ተገባር በመልካም ጎኑ ማሰብ እና መመልከት መቻል ነው። የቅን ሰው ጥያቄና መልስ ከየትኛውም ተንኮል የጸዳ ነው። በርግማን አንደበት የበለጸገን ሰው አፉ እንጂ ሆዱ ባዶ ነው ÷ሰርቆ አደሩን ቢቸግረው እንጂ ወዶ አይደለም ÷ነፍሰ ገዳዩን ደግሞ ሰይጣን አሳስቶት ነው የሚሉ ቅን ሰዎች ሁሉንም ክስተቶች በቀና መንገድ መመልከታቸው ዋጋ ቢያስከፍላቸው ሁሉንም ክስተት በክፋት ከሚተረጉሙ ሰዎች የተሻል የልብ ንጽሕና አላቸው።

ቅንነት ሞኝነት አልያም አለማወቅ አይደለም። ቅንነት በጣም የተወሳሰቡ ችግሮችን መፍታት ምንችልበት ለተንኮል የተጠነሰሱ ሀሳቦችን የምናከሽፍበት ልዩ ጥበብ ነው።ተራራ የሚያክል ስጋትህን በቅኖች መሀል ይዘህ ስትገኝ ድንገት ሳታስበው ሸክምህ ይቀልሀል።ከብዙ አንድ ይህ ቅንነት በተፈጥሮ ይቸረዋል ምኒሽር የሚያስመዝዝ ስራ ሰርተህ ፊታቸው ስትቆም ሥራህ እኮ ይሔ ይሔ ጠቀሜታ አለው ብሎ ፍርሀትህን ሁሉ በአንዴው ሲያከስመው ስታይ የዓለም ሰላም ማጣት የቅኖች ማነስ እንደሆነ ትረዳለህ።

ምክርህን ስድብ÷ምርቃትህን ርግማን÷ሀሳብህን ትንኮሳ አድርገው የሚያቆስሉህ ሰዎች በእርግጠኝነት በቅንነት መረዳት ከእነሱ የተለያቸው ናቸው። ቅንነት ቅናትን የሚያስቀር እና ግጭቶችን የሚያጠፋ በጥቂቶቹ ብቻ የሚገኝ ስጦታ ነው። በቅንነትህ ውስጥ ማግኘት ያለብህን ነገሮች ታጣ ይሆናል ቅንነትን አጥቶ ከአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ከመዘፈቅ ግን በቅንነት ኖሮ የሚፈልጉትን እስኪያገኙ መታገስ የተሻለ ነው።

M@2012
956 viewsMoges abreham, 19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 21:26:12
ከጤነኛው ይልቅ እብድ ነጻነት አለው!! እብድ ነጻነቱን ያወጀው ጤነኞች ከተባሉት በተሻለ ሁኔታ የአእምሮ ነጻነት ስላአለው ነው። እርቃን የመሔድ መዘዝን እሱ ከቆብ አይቆጥረውም÷የሰዎች ሳቅና ቧልታ ምንም ተጽእኖ አይመጣበትም። ብዙዎቻችን ጤነኞች ነን ብለን የእብድ ያህል ጥቂት የአእምሮ ነጻነት ስለሊለን የሰዎችን ሳቅ ስላቅ እየፈራን ምንፈልገውን ትተን ማንፈልገውን እንኖራለን።

ከሰዎች እጅ አፈትልኮ መውጣት ነጻነት ሊሆን ይችላል÷ረጅም ዓመት ከታሰሩበት እስር መፈታትት ነጻነት እንልው ይሆናል÷ከጨቋኝ አገዛዝ እና መሪ መላቀቅንም እንዲሁ ነጻነት እንልዋለን።ከእነዚህ ሁሉ ነጻነቶች ግን እረፍት የሚገኘው ከራስ አስተሳሰቦች ነጻ መሆን ነው።ህይወታችንን ካመሰቃቀሉብን አስተሳሰቦች ነጻ ካልወጣን የምንነካው ሁሉ የከሸፈ የምንቀምሰው ሁሉ ሪት ይሆንብናል።

ሰዎች የሚተቹብን ስብእናችን የሚወለደው ነጻነት ባጣው አእምሯችን ነው።ከክፉ ሀሳቦች መውጣት ካልቻልክ የሚንቀሳቀስ እስረኛ ነህ።ሁል ጊዜ ሰዎች ስላንተ ሚያስቡትን በማብሰልሰል ትጨነቃለህ÷በራስ መተማመንህ እለት እለት እየወረደ ይመጣል÷ሰዎች የማይወዶህ እየመሰለህ ብዙ ተከፍተሀል÷አጠገብህ ሰዎችን ባጣህ ቁጥር አመሌ ቢከፋ ነው እያልክ ቆዝመሀል÷የሚናገሩትን ሁሉ ለእኔ ነው በሚል እንቅልፍ አጥተሀል÷ሲነቅፉህ ፊት ሲነሱህ ብቸኝነትን መርጠሀል። የዚህ ሁሉ መልስህ አዎ ከሆን አንተ በሀሳቦችህ ታስረህ እየኖረክ ነው ማለት ነው።

መፍትሔው ቀላል ነው የስነ ልቦናህ ትኒሽ መሆን ምክንያቱ የሀሳቦችህ ምክንያታዊ አለመሆንና ትኒሽ መሆን ነው።ይህን ከተረዳህ እራስህን ቀለል አድርግና ወርደህ ከሰዎች ጋር ያለህን መስተጋብር አዳብረው ከሰዎች አስተሳሰብ ተምረህ አንተ ከታሰርክባቸው አስተሳሰቦችህ ነጻ ትወጣለህ።

M@(2012)
821 viewsMoges abreham, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ