Get Mystery Box with random crypto!

ቅን የሆኑ ሰዎች ጠንካራ ስብእና ከገነቡ ሰዎች ውስጥ ይመደባሉ። ቅንነት የተጣመመውን ነገር አቃንቶ | ሳይኮ እና ጠቃሚ ምክሮች

ቅን የሆኑ ሰዎች ጠንካራ ስብእና ከገነቡ ሰዎች ውስጥ ይመደባሉ። ቅንነት የተጣመመውን ነገር አቃንቶ ማዳመጥ ብቻ ሳይሆን መጥፎውንም ተገባር በመልካም ጎኑ ማሰብ እና መመልከት መቻል ነው። የቅን ሰው ጥያቄና መልስ ከየትኛውም ተንኮል የጸዳ ነው። በርግማን አንደበት የበለጸገን ሰው አፉ እንጂ ሆዱ ባዶ ነው ÷ሰርቆ አደሩን ቢቸግረው እንጂ ወዶ አይደለም ÷ነፍሰ ገዳዩን ደግሞ ሰይጣን አሳስቶት ነው የሚሉ ቅን ሰዎች ሁሉንም ክስተቶች በቀና መንገድ መመልከታቸው ዋጋ ቢያስከፍላቸው ሁሉንም ክስተት በክፋት ከሚተረጉሙ ሰዎች የተሻል የልብ ንጽሕና አላቸው።

ቅንነት ሞኝነት አልያም አለማወቅ አይደለም። ቅንነት በጣም የተወሳሰቡ ችግሮችን መፍታት ምንችልበት ለተንኮል የተጠነሰሱ ሀሳቦችን የምናከሽፍበት ልዩ ጥበብ ነው።ተራራ የሚያክል ስጋትህን በቅኖች መሀል ይዘህ ስትገኝ ድንገት ሳታስበው ሸክምህ ይቀልሀል።ከብዙ አንድ ይህ ቅንነት በተፈጥሮ ይቸረዋል ምኒሽር የሚያስመዝዝ ስራ ሰርተህ ፊታቸው ስትቆም ሥራህ እኮ ይሔ ይሔ ጠቀሜታ አለው ብሎ ፍርሀትህን ሁሉ በአንዴው ሲያከስመው ስታይ የዓለም ሰላም ማጣት የቅኖች ማነስ እንደሆነ ትረዳለህ።

ምክርህን ስድብ÷ምርቃትህን ርግማን÷ሀሳብህን ትንኮሳ አድርገው የሚያቆስሉህ ሰዎች በእርግጠኝነት በቅንነት መረዳት ከእነሱ የተለያቸው ናቸው። ቅንነት ቅናትን የሚያስቀር እና ግጭቶችን የሚያጠፋ በጥቂቶቹ ብቻ የሚገኝ ስጦታ ነው። በቅንነትህ ውስጥ ማግኘት ያለብህን ነገሮች ታጣ ይሆናል ቅንነትን አጥቶ ከአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ከመዘፈቅ ግን በቅንነት ኖሮ የሚፈልጉትን እስኪያገኙ መታገስ የተሻለ ነው።

M@2012