Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያናግሩን:-ኢሰማኮ ኢሠማኮ ትላንት በአዲስ አበባ በአዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀው የሠራ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያናግሩን:-ኢሰማኮ
ኢሠማኮ ትላንት በአዲስ አበባ በአዳራሽ ውስጥ ባዘጋጀው የሠራተኞች ቀን በዓል ላይ የተሳተፉ ሠራተኞች ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ እንዲያነጋግሯቸው መጠየቃቸውንሶን ገልጧል
ሠራተኞቹ ችግራቸውን ለመንግሥት ለማስረዳት መድረክ አለመመቻቸቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው መግለጣቸውን ኢሠማኮ ጠቅሷል። ዐቢይ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር መወያየታቸውን የጠቀሱት ሠራተኞቹ፣ እስካሁን ከሠራተኞችና ከተወካዮቻቸው ጋር አለመወያየታቸው እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል ተብሏል። የመድረኩ ተሳታፊዎች፣ የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ከሠራተኞች ችግር አንጻር ሃላፊነቱን አልተወጣም በማለት መውቀሳቸውም ተገልጧል። የዘንድሮው የወዛደሮች ቀን የተከበረው፣ መንግሥት ዝቅተኛ የሠራተኛ ደመወዝ የሚወስን ቦርድ እንዲያቋቁምና የደመወዝ ግብር እንዲቀንስ ኢሠማኮ ዓመቱን ሙሉ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሳያገኙ ነው።
"ፈጣን እና እውነተኛ ሀገራዊ መረጃ እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial