Get Mystery Box with random crypto!

> - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ > ተናግረዋል። ፕሬዝደንቷ ይሄን | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

<< ተግባር ከሌለ መወያየት ብቻውን ባዶ ተስፋ ነው >> - ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ << መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም፤ መተግበር እንዳለበት >> ተናግረዋል።
ፕሬዝደንቷ ይሄን ያሉት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሴቶችን ተሳፎ በተመለከተ በትናንትናው ዕለት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።
<< በኢትዮጵያ መናናቅ እና የት ይደርሳል ማለት ችግር ሲፈጥር እየታየ መሆኑንም >>  ፕሬዝደንቷ አመልክተዋል።

<< መወያየት ብቻውን በቂ አይደለም >> ያሉት ፕሬዝደንቷ << መተግበር መቻል እንደሚኖርበት በግልፅ ቋንቋ ተናግረዋል። 

አክለውም << እንደ ሀገርም የመወያየት ችግር ባይኖርም መሠረታዊ ችግሩ አፈፆፀም መሆኑንም >> አብራርተዋል።

ውይይቶች ተሞክሮዎች ሁሉ መሬት ወርደው  ካልተተገበሩ ባዶ ተስፋ መስጠት ነው ያሉን ሳህለወርቅ የምክክር ሂደቱ ችግሮችን በዘለቄታዊነት ለመፍታት የሚደረግ ጥረት እንጂ ለተወሰነ ጊዜ የተወሰኑ ሲሉ የጠሯቸውን ሁኔታዎች ለማስተገሻ እንዳልሆነ  ግልፅ ማድረግ  ይገባል ብለዋል።

የማይሆን ተስፋ ሆኖ እንዳይታይም በጣም ሲሉ በገለፁት ደረጃ  መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግም አመላክተዋል።  << ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ መስራት ያስፈልጋል በማለትም ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው  እንወያይ እንጋገር ከማለት የዘለለ አይደለም >> ሲሉ ተችተዋል።

ሳህለወርቅ እንደሚሉት << አሁን በተለይ መናናቁ እና የት ይደርሳል መባባሉም ለሀገሪቷ ችግር እየሆነ መጥቷል >> ሲሉ አንክሮ ሰጥተዋል።

በመሆኑም እንደሀገር ያለብንን ችግር ለመቅረፍ የሚረዳው አማራጭ ሰው ያለውን ሁሉ ሓሳብ እንዲያዋጣ ማበረታታት እና መረዳት ብሎም መግባባት ነው ብለዋል።

በንግግር ፋንታ ቂምንና ማግለልን ብሎም መሰል ነቀፌታዎችን  ማስወገድ ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።

በሌላ በኩል ህዝብ ማዕከል ያደረገ ውሳኔ ሲሰጥ ሴቶችን አካታች ማድረግ ግዴታ መሆኑን አስቀድመው በህወሓት ሃይሎች እና በፌደራሉ መንግስቱ መካከል  የነበረውን ጦርነት በቋጨው የፕሪቶርያ ዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት ሴቶች አለመወከላቸውን ጠቁመዋል። 

በጦርነቱ ሂደት ውስጥ ሴቶች ደርሶባቸዋል ያሉትን  ከፍተኛ ጉዳትም እስታውሰዋል።

ይሁን እንጂ አሁን ላይም  በተመሳሳይ መልኩ ሀገሪቷ ውስጥ ውጊያዎች፣ ጦርነቶች፣ መገዳደልና  መፈናቀል መኖሩን አስቀድመው በጥቅሉ  ከጦርነት ካለመግባባት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች መኖራቸወን ገልፀዋል።

በመጨረሻም በርትቶ መስራት፣የተናገሩትን መኖር እንደሚገባ አስገንዘበው ስራችን የሚወሰነውም የህዝቡን ኑሮ በመለወጥ ላይ፣ ሰላምን ለማስፈን መሆኑን አስቀድመው  ሰለም  ደግሞ << በመደለል >> ብቻ የሚገኝ አይደለም ብለዋል።

ምንም እንኳን ሳህለወርቅ ከመወያየት ባሻገር ተግባር ግድ እንደሚል አፅዕኖት ቢሰጡም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን < ምክክርሩን > ሲያጠናቅቅ ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ምክረሃሳቡን ከማቅረብ በዘለለ የመተግባር ስልጣን እንደሌለው በታህሳስ 2014 ዓ.ም የጸደቀው የማቋቋሚያ አዋጅ ያስረዳል።
"የቴሌግራም ቻናላችንን ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ያድርጉ"
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial