Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ስልክ እያነጋገሩ ያሽከረከሩ ከ6 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ስልክ እያነጋገሩ ያሽከረከሩ ከ6 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች መቀጣታቸው ተነገረ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመነት ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ ከ25 ሺህ በላይ  አሽከርካሪዎችን መቅጣቱን አስታውቋል።
ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 9 ወራት ውስጥ በ33 መንገዶች ላይ ከፍጥነት ወሰን በላይ ያሽከረከሩ 25 ሺህ 888 አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ያላሰሩ 3 ሺህ 800 አሽከርካሪዎች በደንብ መተላለፍ መቀጣታቸው ተገልጿል ።

በተጨማሪም 204 ሞተረኞች የግጭት መከላከያ ቆብ ወይም ሄልሜት ሳያደርጉ ፣ 6504 አሽከርካሪዎች ስልክ እያነጋገሩ በመገኘታቸው በደንብ ቁጥር 395/2009 መሰረት ቅጣት እንደተጣለባቸው ተጠቁሟል ።

በዚህም የተነሳ የሞት አደጋ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ6 ነጥብ 34 በመቶ  መሻሻል መታየቱ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።
"ለፈጣን መረጃ ቻናላችንን Join አድርጉ
http://t.me/ayuzehabeshaofficial
http://t.me/ayuzehabeshaofficial