Get Mystery Box with random crypto!

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ስለሙስሊሞች በሰጡት አስተያየት ተቃውሞ ተነሳባቸው ህንድ 1.42 | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ስለሙስሊሞች በሰጡት አስተያየት ተቃውሞ ተነሳባቸው
ህንድ 1.42 ቢሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 200 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊም ነው
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ ስለሙስሊሞች በሰጡት አስተያየት ተቃውሞ እንደተነሳባቸው ተገልጿል።
የህንዱ ዋና ተቃዋሚ ኮንግረስ ፓርቲ ምክርቤት የምርጫ ህጎችን በመጣስ በሙስሊሞች ላይ ተገቢ ያልሆነ አስተያየት ሰጥተዋል ባላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ላይ የምርጫ ኮሚሽን እርምጃ እንዲወስድ አቤቱታ ማቅረቡን ሮይተርስ ዘግቧል።
ለሶስተኛ ዙር የስልጣን ዘመን እየተወዳደሩ ያሉት ሞጄ ባለፈው እሁድ ባቀረቡት የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ሙስሊሞችን "ሰርጎገቦች" በሚል መጥራታቸው ከተቃዋሚዎች ከፍተኛ ትችት አስነስቶባቸዋል።
የሞዲ የሂንዱ ብሔርተኛ ባራቲያ ጃናታ ፓርቲ(ቢጄፒ) እና አጋሮቹ ሙስሊሞችን በህገወጥ መንገዱ ከፓኪስታን የመጡ ሰርጎገቦች ሲሉ ይጠሯቸዋል። ሙስሊሞችን ባላቸው ከፍተኛ የወሊድ ምጣኔ ምክንያት የሚተቹት የሞዴ ፓርቲ እና አጋሮቹ የህንድ ሙስሊም ህዝብ አብዛኛ ቁጥር ያለውን ሂዱን ሊበልጥ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።
ህንድ 1.42 ቢሊዮን ህዝብ ያላት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 200 ሚሊዮን የሚሆነው ህዝቧ ሙስሊም ነው።
የኮንግረስ መሪ አቢሸክ ማኑ ሲንግቪ እንደገለጹት  የሞዴ ያልተገባ ንግግር እጩ ተመራጮች፣ መራጮች እጩዎችን "በሀይማኖት" "በማህበረሰባዊ ማንነት" ወይም "በሀይማኖታዊ ምልክቶች" እንዲመርጡ ወይም እንዳይመርጡ እንዳይጠይቁ የሚከለክለውን የምርጫ ህግ ጥሷል።
የምርጫ ኮሚሽኑ ይህንን እንዲመለከተው ማመልከታቸውን ሲንግቪ ተናግረዋል።
የሞዲ መንግስት ሙስሊሞችን በማግለል በተደጋጋሚ ክስ ይቀርብበታል።ነገርንግን ሞዲ የሚነሱባቸውን ሁሉንም ክሶች አስተባብለዋል።
Join @ayuzehabeshaofficial