Get Mystery Box with random crypto!

የኢራን ፕሬዝዳንት ከእስራኤል በኩል ለሚሰነዘር ጥቃት 'ከባድ' ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ቃል ገቡ የ | Ayu Zehabesha-Official (አዩ ዘሀበሻ)

የኢራን ፕሬዝዳንት ከእስራኤል በኩል ለሚሰነዘር ጥቃት 'ከባድ' ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ቃል ገቡ
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከኳታር አሚር ጋር ሀገራቸዉ በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን የአየር ላይ ጥቃት ስኬታማ እንደሆነ ገልፀው ኢራን ወደፊት በጥቅሟ ላይ ስጋት ካለባት የበለጠ “አሳማሚ” ጉዳት እንደምታደርስ በነበራቸዉ የስልክ ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የኢራን የዜና ወኪል እንደዘገበው  በኢራን ፍላጎት ላይ የሚወሰደው ትንሹ እርምጃ በእርግጠኝነት በሁሉም አጥፊዎቹ ላይ ከባድ ፣የተስፋፋ እና የሚያሰቃይ ምላሽ ይጠብቀዋል ስንል በግልፅ እንናገራለን” ብለዋል።
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ ካኒ ለመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ቴህራን ማንኛውንም የእስራኤል አጸፋ ተከትሎ የምትወስደው እርምጃ እንዳሁኑ ኢራን ተጨማሪ 12 ቀናት ምላሽ ለመስጠት ስለማትጠብቅ በጥቂት ሰከንዶች ልዩነት መልስ እንሰጣለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ በበኩላቸዉ ሀገራት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ አሳስበዋል፡፡የእስራኤል ከፍተኛ ዲፕሎማት "በኢራን ላይ የፖለቲካ ጥቃትን" እየመራሁ እገኛለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ወደ 32 ለሚሆኑ ሀገራት ደብዳቤ ልኬያለሁ እናም በኢራን ሚሳኤል ጥቃት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል እና የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ለመጠየቅ በደርዘን የሚቆጠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እና የአለም መሪዎችን አነጋግሬያለሁ ብለዋል።
የእስራኤል ወታደራዊ አዛዥ ሄርዚ ሃሌቪ በኢራን ጥቃት ቀላል ጉዳት በደረሰበት ወታደራዊ ጣቢያ በመገኘት ለወታደሮች እንደተናገሩት የኢራን ድርጊት የአጸፋ ምላሹን ያገኛል ሲሉ ተናግረዋል።
Join
http://t.me/ayuzehabeshaofficial