Get Mystery Box with random crypto!

የእናቴ ልጅ ክፍል ሃያ ሦስት ወደ ጊቢ ስገባ ሸማግሌው የሚበሉትን ጨርሰው ውሃ | አትሮኖስ

የእናቴ ልጅ
ክፍል ሃያ ሦስት

ወደ ጊቢ ስገባ ሸማግሌው የሚበሉትን ጨርሰው ውሃ ሲጠጡ አገኘዋቸው። እናቴም እነደግነሽም ወደውስጥ ገብተው ነበር ፡አቤል ብቻ በረንዳው ላይ ቁጭ ብሎ ሰውዬው አንዳች ነገር ያነሱ ይመስል ይከታተላቸዋል የአቤል ሁኔታ ገረመኝ አሁን እኚ ሽማግሌ ምኔን ይነኩኛል ብሎ ነው ጠምዶ የያዛቸው ለራሳቸው የያዙትን ብርጭቆ እንኳ በቅጡ ወደአፋቸው ለማድረስ የተቸገሩ ነው የሚመስሉት ።
  አቤልን ችላ ብዬ ወደ ሽማግሌው ተጠግቼ ቁጭ አልኩ ደንገጥ አሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኜ ፈገግ አልኩ እናም የሚንቀጠቀጠው እጃቸው ላይ ያለውን ብርጭቆ ተቀብዬ መሬት አስቀመጥኩት ።
"አአመሰግናለው ልልጄ "አሉኝ
"ኧረ አባት አይጨነቁ "አልኳቸው በተቀደደ ቲሸርታቸው ውስጥ የሚታሁኝ አጥንቶቻቸው የተሸበሸበው ቆዳቸው ብዙ ስቃዮችን እንዳሳለፉ ይናገራሉ
"እሺ ልጄ አሁን በልቼ ጨርሻለው ልሂድ መሰለኝ "አሉ
"አይ ቆይ ቆይ ትንሽ ከኔ ጋር ይጫወታሉ "አልኳቸው
"አይ ልጄ ስለምን ልንጫወት ነው"አሉ ፈራ ተባ ብለው
"እዚ በተደጋጋሚ ይመጣሉ እንዴ ሁሉም ሰው ያውቆሆታል ከኔ በቀር"አልኳቸው
"እእ አዎ አልፎ አልፎ ርሃብ ሲጠናብኝ እዚ እመጣለው እናትህ ደግ ሴት ናት "አሉ አዘን ብለው
"አዎ እናቴ ደግ ናት "አልኳቸው እንዳቀረቀሩ ዝም አሉ
"ስሞት ማነው "አልኳቸው
"አበራ አበራ አይሉ እባላለው "አሉ
"ደስ የሚል ስም ነው አበራ አይሉ ደስ ይላል"አልኳቸው ።ዝም አሉ በጣም የጨነቃቸው ይመስላሉ የበታችነት ስሜት ሳይሰማቸው አይቀርም
"አባት በማንኛውም ሰአት ወደዚ ቤት መምጣት ይችላሉ ምንም ነገር እንዳያሳስቦት ፡ ከፈለጉ ደሞ እርሶ እሺ ይበሉኝ እንጂ እዚ እኛጋር አትክልተኛ ሆነው እንዲሰሩ እናቴን ላሳምንሎት እችላለው "አልኳቸው ።ይሄን ስላቸው አሻግረው ወደ አቤል አየት አደረጉ
"ምነው አልፈለጉም "አልኳቸው
"አይ ይቅርብኝ ያለውበትን ሁኔታ ለምጄዋለው አታስብ "አሉ
"በቃ አሳቦትን ከቀየሩ በማንኛውም ጊዜ ይጠይቁኝ "አልኳቸው ።እሺ በሚል እራሳቸውን ነቀነቁልኝ ለምን እንደው አብሬ አቸው መቆየት ፈልጌ ነበር እሳቸው ግን ተጣደፉ ።ይሁን ብዬ አሰናበትኳቸውና ወደ ትልቁ ቤት ሄድኩ አቤል ሽማግሌው እንደወጡ ካረጋገጠ በዋላ ወደውስጥ ገብቷል ስገባ ቁርሰሸ ቀርቦ ቡናው ተጥዶ ሞቅ ሞቅ ብሏል ። ይሄ የቤተሰብ ስብስብ ይመቸኛል ደስስስ የሚል ስሜት ይሰጠኛልም።
ሕይወት እኔንና ቤተሰቤን በፍቅር ይዛን ወደፊት መጓዛን ቀጥላለች ።እናቴ ደግነሽ ባዩሽ ማማ አቤልን ጨምሮ ሁላችንም ሰላማዊ በሆነው ትልቁ ቤታችን በደስታ እያሳለፍን ቀናቶች ተቆጠሩ ። የኔ የደስታ ምንጭም ጨምሯል በብሌን ግልፅና ያልተገደበ የፍቅር አዙሪት ምክንያት።  የብሌንን ፍቅር ብፈራውም እስካሁን የፈራውት አልደረሰም። ያልተለመደው ግልፅነቷ የኔንም ድብቅነት ገላልፆ ፊለፊት አውጥቶ ከማሳየት በስተቀር አልተጎዳውም ። እንደዛተችው ጥላኛለች እቅፏ ውስጥ ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴትልጅ ገላ እንዳውቅ ስሜቱንም እንዳጣጥም አድርጋኛለች ፡ በፍቅር ጠብ አድርጋኛለች ። እናም በዚ ደስተኛ ነኝ ዙሪያዬን የሚያስብልኝ ሰው ነው የከበበኝ ማለት እችላለው ፡ አቤልም ደና የሆነ ይመስላል  እናቴም አቤልን ወደ ውጭ ለመላክ ያሰበችው አሳብ ሊሳካላት ተቃርቧል ፡ መጀመሪያላይ እሱም አቅማምቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ፍቃደኛ ሆኗል  በተለይ የሚሄድበት ሀገር ሲዊዲን ነው ሲባል እዛ ያስቀመጠው ነገር ያለ ይመስል ደስ ብሎታል ፡ እኔ ግን በአቤል መሄድ እርግጠኛ መሆን ከብዶኛል ፡የሚሄድም ከሆነ ደርሶ የሚመለስ ነው የሚመስለኝ  አቤል እኮ ነው። ተቀብሎ መኖር የለመደ እጁ ለስራ ይሰለጥናል ማለት ከበደኝ ።
እናቴ ደሞ የመጀመሪያ ስራዋ አቤልን ከእኛ ማራቅ የሆነ ይመስል በገንዘብም ላይታች በማለትም እየበረታች ነው ። እሷ አሁንም ድረስ አቤል ላይ ያላትን አቋም አልቀየረችም እሱን ማመን ከብዷታል ከእኛጋር በቆየ ቁጥር አንዳች ዱብዳ እንደሚያወርድ ነው የምታስበው  እኛ ሽማግሌ እንኳ ሲመጡ ሁሌም አቤል እንደተቆጣ ነው እሷ ደሞ ስለ አቤል ሆና ይቅርታ እንደጠየቀች ነው ። ይሄ በራሱ እንኳ እንድትፈራው አድርጓታል ፡ሁሌም እኔን ወንድምህ ነው ውደደው ነገርግን እየተጠነቀከው ትለኛለች ።
ከቀናቶች በዋላ የአቤል የውጪ ፕሮሰስ ጉዳይ ተሳካና የሚሄድበት ቀን ተቆረጠ እናቴ ትልቅ እፎይታ ሆነላት የሚያስፈልጉትን ነገር ሁሉ አዘጋጀች  ባዩሽና አክስቴ ደግነሽም ዳቦ ቆሎ በርበሬ ሲያዘጋጁ ከረሙ ።ብሌን እራሱ አልቀረችም ስለ እኔ ብላ ስዊዲን አገር ከሚኖሩ ጓደኞቿ ጋር ተደዋውላ ነገሮችን በማመቻቸት   የበኩሏን ስትወጣ።  እኔ ግን በጣም ቅር ብሎኛል አቤል ምን ሊሆን ነው እዛ ሄዶ ስራ ሰርቶ አያውቅ በሰው አገር ሲቸገር ሲያዝን እየታየኝ ጨነቀኝ ።
የማይቀር ነገር ሆነ እና ይኽው ልንሸኘው ተዘጋጀን   እንደነገ ሊሄድ ማታ ላይ ተሰባስበን የመጨረሻ ምሽት እያሳለፍን ነው ሁላችንም ዘና ልናረገው ሞከርን እሱ ግን ምንም አይነት የስሜት ለውጥ ሳያሳይ ቆይቶ ነበር ወደ ምሽት አራት ሰአት አካባቢ ግን የስሜት ለውጥ ይታይበት ጀመር ምን አልባት ሰአቱ ሲደርስ ተረብሾ ይሆናል ብዬ ነበር ፡ እናቴ በትኩረት ትከታተለዋለች ፡ አቤል መቁነጥነጥ ጀመረ ፡አሁንም አሁንም ወደውጪ እየወጣ ይመለሳል ፡ በመጨረሻ ስልክ ተደውሎለት ወጣ ፡ደግነሽ ተከተለው ብላኝ ነበር ልከተለው ስንቀሳቀስ እናቴ ተመለስ አለችኝ እሱም ሰው አግኝቼ እመለሳለው አታስቡ ብሎን ፈጠን አለ እርስ በእርስ ተያየን ። እናቴ በቤት ውስጥ ወዲ ወዲያ እያለች ታስባለች እኔም እስኪመጣ ተጨነኩ ፡  ለምን ድነው ተጣድፎ የወጣው የሁላችንም አሳብ እሱው ጋር ሆነ,,,,,,,


ደራሲ Unknown

ይቀጥላል......
    ሀሳብ አስተያየታችሁን 
@Tsiyon_awit አድርሱኝ
   ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj