Get Mystery Box with random crypto!

#ባል_አስይዞ_ቁማር ፡ ፡ #ክፍል_አርባ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ያልተኖረበት የአንድ ወር | አትሮኖስ

#ባል_አስይዞ_ቁማር


#ክፍል_አርባ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ያልተኖረበት የአንድ ወር ቅድመ ክፍያ ቃል ከፍሎ የሄደ ቢሆንም እሷ የስድስት ወር ተጨማሪ ቅድመ ክፍያ ከፈለች...ይሄንን ቅድመ ክፍያ ቃል ሲኖርበት ለነበረ ክፍል ብቻ ሳይሆን ከዛ ቀጥሎ  ለነበረች አንድ ክፍል ቤትም ጭምር ነው የከፈለችው። ክፍሏን እንደአዲስ ቀለም አስቀባችው.....ሙሉ እቃ ፤ አልጋ፤አነስተኛ ፍሪጅ፤ቴሌቪዠን አንድ ጠረጰዛና ሁለት ወንበሮች አስገባችበት ...እንዲህ ያደረገችው የቃልን አባት ከመቄዶንያ አስወጥታ እቤት በማምጣት እራሷ  ልትንከባከባቸው ስለወሰነች ነው።አዎ ይሄንን ዕቅድ ካቀደችበት እለት አንስቶ  በውስጧ ደስታ እየተሠማትና ከድብርቷም በመጠኑም ቢሆን እየተላቀቀች ነው።

አሁን ሙሉ በሙሉ ዝግጅቷን ስላጠናቀቀች ወደሜቅዶኒያ ሄዳ አባትዬውን   የምታመጣበት ቀን ነው።ከመውጣቷ በፊት በሞባይሏ ያዘጋጀችውን ቤት ፎቶ ደጋግማ አነሳችው...ለመምጣት  አሻፈረኝ እንዳይሏት ምን ያህል ተጨንቃ እንዳዘጋጀችላቸው   በምን ያህል መጠን ቁርጠኛ መሆኗን  እሳቸውን ለማሳመን እንዲያግዛት አስባ ነው።በዛ ላይ በማሳመኑ ስራ ቀላል እንዲሆንላት ከእሷ በላይ የሚያውቋትንና ከልጃቸው ባልተናነሰ ያሳደጓትን ጊፍቲን ይዛ ነው የምትሄደው።

የራሷን መኪና እየነዳች እግረ መንገዷን ጊፍቲን ካለችበት አንስታ መቂዶኒያ ደረስን.... መኪናዋን አቁማ ከጊፍቲ ጋር ጎን ለጎን በዝግታ እርምጃ(ያው እርጉዝ ስለሆነች)ወደ ቃል አባት ያሉበት አካባቢ ሲደርስ ያልተለመደ ግርግር ነገር ገጠማቸው...ጊፍቲን ወደኃላ ተወችና ፈጠን ፈጠን እያለች ወደፊት ተጓዘች.... ደረሰች፡፡ ከአስር የሚበልጡ ሰዎች በቦታው ይተረማመሳሉ...አንዳንዶቹ ከንፈራቸውን ይመጣሉ...የሆነ ቀፋፊ ስሜት ሳትፈልግ በግድ ወደ ሰውነቷ ሲሰርግ ታወቃት..ወደ አንድን አዛውንት ተጠጋችና"አባባ ምን ተፈጥሮ ነው?"ስትል  ጠየቀቻቸው፡፡

"ያው ሰው ከንቱ አይደል?አንድ ጓደኛችን ሞቶ ነው"

"ወይ እግዚያብሄር ነፋሱን ይማር."አልኩኝ፡፡

‹‹ወዬኔ ጋሽ ሞገስ...በቃ ሞተ "እያለች አንድ ሴት በስሯ አለፈች፡፡

"ጋሽ ሞገስ?  ይሄን ስም የት ነው የማውቀው? ስትል እራሷን ጠየቀች ተምታባት..በዚህ ጊዜ ከኃላዋ ቀርታ የነበረችው ጊፈቲ ስሯ ደርሳ ነበር.."

"ምን ተፈጠረ ?"ስትል ጠየቀቻት፡

"ሰው ሞቶ ነው?ጋሽ ሞገስ የሚባሉ ሰውዬ ናቸው አሉ"ነገረቻት

"ሞገስ?ሞገስ ማን?"አደነጋገጧ አስፈሪ ነበር፡፡

‹‹ምነው ታውቂያቸዋለሽ እንዴ?››

"የቃልዬ አባት...."
ዠው አለባት...‹‹የተምታታብኝ ለካ ለዛ ነው?"አለች፡፡

‹‹ምንድነው እየሆነ ያለው? ማነው የነካሽው ሁሉ ወድያው ይብነን ወይ ይክሰም ብሎ የረገመኝ?።ስትል አማረረች
""""
ከጊፍቲ ጋር ሆነው የቃልና አባት ቀብር በተገቢው መንገድ አስፈፀሙ....ቅልብጭ ያለች የእብነበረድ ሀውልትም አሰራችላቸው። እሳቸው ከሞቱ በኋላ በፊት የሚሰማት  ሀዘን ብቻ አይደለም እየተሰማት ያለው ።ጉልበት የማጣትና ተስፋ የመቁረጥ ሰሜት ጭምር ውስጧን እያወደመው ነው። አሁን በዚህ ሰአት እሳቸው ሀውልት ጋር ቁጭ ብላ እየተከዘች ነው፡፡

ፊት ለፊቷ ዝርፍፍ ያለች የብሳና ዛፍ ትታታለች ...የበጋው ንዳድ እሷን ብቻ ሳይሆን ዛፏንም የጎዳት መሰላት።ቅርንጫፎቾ የተሸከሞቸው አብዛኛው ቅጠሎች ወይበዎል።አረንጎዴ ቀለማቸው ተመጦ ወደ ቢጫነት እያዘገሙ ነው።ድንገት ከወደ ምዕራብ በኩል ብዛት ያላቸውና ከእሷና ከዛፉ በተቃራኒው በውበት ያሸበረቁ ወፎች ተንጋግተው  መጥተው ሰፈሩበት ...ግማሽ የሚሆነው ቅጠሉ እየተቀነጠሰ ወደ መሬት ረገፈ...፡፡አዘነች ውስጧ እስኪሰበር ድረስ አዘነች..፡፡ያዘነችው ለዛፉ በማዘን አይደለም ለራሷ እንጂ...የእሷም ለዘመናት የገነባችው ተስፋዋ ድንገት መጥቶ ህይወቷን በነቀነቀው መከራ ልክ እንደዚህች ዛፍ ቅጠሎች ነው እርግፍ ያለው።እርግጥ ዛፍ ከጥቂጥ ሳምንታት በኃላ ክረምት ገብቶ ዝናብን ሲያርከፈክፍለት በደስታ ከድርቀቱ አገግሞ እንደሚለመልም መወየብ ታሪክ ሆኖ አረንጓዴ እንደሚለብስ ታውቃለች .‹‹.የእኔስ  ዝናብ መቼ ይሆን አስገምግሞ መጥቶ የሚያርሰኝ እና ከድርቀቴ የሚፈውሰኝ።›ስትል ጠየቀች…

ሰው ግን  በሚሊዬን ህያዋን መካከል እየኖረ ሚሊዬን ህያዋንን በመንገድ ላይ እየገፈተሩና እየገላመጡ መጥቶ እንዲህ  በድን ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ከበድን ጋር ማውራት.?››ስትል በራሷ  ድርጊት ተደመመች፡፡

"ያው የቃል አባት ስለሆኑ የእኔም አባት ኗት...ደግሞ ያው አባትም የለኝም። ምን አልባትም እንደእርሶ የሞተ ይመስለኛል..እንደዛ ከሆነም  የሁለታችሁንም ነፍስ አምላክ ይማራት።››ትንፋሽ  ወስዳ ጉሮሮዋን በምራቋ ካረጠበች በኃላ ንግግሯን አራዘመች፡፡

<<እና ይሄውሏት ቃል ጥሎኝ ከጠፍ በኃላ ለቀናት ሳዝንና ስጨነቅ ከርሜ ነበር እና ድንገት ስለእርሶ ትዝ ሲለኝ ውስጤ ተስፋ ሰነቀ...የፈለገ በእኔም ሆነ በጠቅላላ አለሙ ቢጨክን በአባቱ አይጨክንም ስል አሰበኩ፡፡በእርሶ ላጠምደው ወሰንኩ። ያው ያውቁ የለ እኛ ሴቶች ያፈቀርነውን ወንድ የራሳችን ለማድረግ የተለያዩ ስውር ዘዴዎችን እንጠቀማለን...ለምሳሌ የምናፈቅረው ወንድ አልጨበጥ ብሎ ካስቸገረን ሌሎች ወንዶች እየፈለጉንና እየተከተሉን እንደሆነ እንዲያውቅ እናደርጋለን...ቅናት ውስጥ ገብቶ ከመቀደሜ በፊት ልቅደም እንዲል እኮ ነው ።ወይም ደግሞ የተሳሳትን በማስመሰል  ልጅ እናረግዝና ውሳኔው ከባድ እንዲሆንበት እናደርጋለን ….አዎ በፍቅር ጉዳይ ሴቶች ቁማርተኞች ነን፡፡

እንደሚያውቁት እኔ ደግሞ ቃልዬ አብሮኝ ስለሌለና  የት እንዳለም ስለማላውቅ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ስለዚህ የነበሩኝ ብቸኛ የመጫወቻ ካርዴ እርሶ ነበሩ  ። ወደቤታችን ማለቴ ወደቃል ቤት ልወስዶት ለቀናት ለፍቼ ብዙ ብዙ ነገር አዘጋጅቼ  ያማረች ክፍል አዘጋጅቼሎት ነበር...የምትንከባከቦትም ወጣት ነርስ ቀጥሬሎት ነበር..እናም ደግሞ እስከመጨረሻው ድረስ ልንከባከቧት አልሜና ወስኜ ነበር...ከአሁን በኃላ አስርና ሀያ አመት ይኖራሉ የሚል ግምት ነበረኝ...እና በዛ የጊዜ ርዝመት ውስጥ ቃል አንድ ቀን እርሷን ለማየት ሲል ብቻ  ተመልሰሶ ሊመጣ ስለሚችል አንድ ላይ ሲያገኘን ይደሰታል..እናም ምን አልባት ዳግመኛ ጥሎኝ ለመሄድ  ልቡ አሻፈረኝ ትላለች የሚል ምኞት ሰንቄ ነበር ...እንደው ያ ባይሆን እንኳን  አንድ ቀን ተመልሶ ይመጣል እያልኩ ነፍሴን በተስፋ ሞልቼ ህይወቴን በጥበቃ ለማስቀጠል  ወስኜ ነበረ...ግን ምን አልባት የልቤን ሀሳብ አማልዕክቱ ሰምተው መጥተው ሹክ ብለዎት መሠለኝ የሀሳቤ ተባባሪ ላለመሆን ሞተው ጠበቁኝ። ግድ የለም አሁን በሁሉ ነገር ተስፋ ቆርጬያለሁ...እሱን ለመጠበቅ ያለኝን እቅድም እርግፍ አድርጌ ትቼዋለሁ..ግን ህይወቴን እንዴት እንደምቀጥል ምንም አላውቅም..?መቼ መሳቅና መቼ ደግሞ ማልቀስ እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል...በሉ ደህና ይሁኑ...አልፎ አልፎ ብቅ ብዬ አዬዎታለሁ።ቃልዬ አደራ ብሎኛል።

ልፍለፍዋን  ጨርሳ ከመቃብሩ ድንጋይ ላይ ተነሳች፡፡

ይቀጥላል