Get Mystery Box with random crypto!

‹‹ጥዋት ሜቅዶኒያ አንሄድም እንዴ?›› ‹‹አይ የነገው ይለፈኝ›› ‹‹በቃ እስከመኪናሽ ሸኝሻለሁ | አትሮኖስ

‹‹ጥዋት ሜቅዶኒያ አንሄድም እንዴ?››

‹‹አይ የነገው ይለፈኝ››

‹‹በቃ እስከመኪናሽ ሸኝሻለሁ…

አልተቃወመችውም

እንዳለውም እስከመኪዋ ድረስ ሸኛትና እስከዛሬ ሲያደርግ ከነበረው በተለየ መልኩ በደንብ ወደራሱ ስቦ ከሰውነቱ ጋር ለጥፎ አንገቷ ስር ገባና በስሱ ሰሟት ምንም ሳይናገር ፊቱን አዙሮ ወደቤቱ ተመለሰ…መኪናውን ማስነሳት ዘንግታ ወደውስጥ ገብቶ በራፍን እስኪዘጋ ድረስ ፈዛ እያየችው ነበር…‹‹ወይኔ በፈጣሪ እንደው ትእግስት ኖሮኝ ጥቂት ሳምንታት መጠበቅ ብችል እራሱ ቃል አፍ አውጥቶ አፈቅርሻለሁ የእኔ ሁኚ ብሎ ጥያቄ እደሚያቀርብልኝ አሁን ከሳመኝ አሳሳም መረዳት ችያለሁ…ግን አንገቴን ስለሳመኝ እንዲህ የወረረኝ ከንፈሬ ላይ ከንፈሩን ያሳረፈ ቀን ክንፍ አውጥቼ መብረሬ አይቀርም ›› ስትል አሰበችና ፈገግ አለችና በልዩ ደስታ እንደተዋጠች መኪናዋን አስፈንጥራ ወደቤቷ ሸመጠጠችው፡፡

ይቀጥላል