Get Mystery Box with random crypto!

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ __ የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋ | ATC NEWS

የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
__

የጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በግንቦት 2016 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም አዲስም ሆነ ነባር፣ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን የኦንላይን ምዝገባው ከሚያዚያ 7/2016 እስከ ሚያዚያ 21/2016 ዓ.ም ብቻ የሚቆይና ከተጠቀሰው ቀን በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፦

- የግል ትምህርት ተቋማት ተመዛኞች ከምዝገባ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (ETA) Authenticate ማስደረግና ስማችሁን ከባለስልጣኑ ወደ ጤና ሚኒስቴር ማስላክ ይጠበቅባችኋል፡፡

- ከጥር 1/2015 ዓ.ም በኋላ የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች የትምህርት ሚኒስቴር መውጫ ፈተና(Exit Exam) ማለፍ ይጠበቅባችኋል፡፡

- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡ #MoH


ለጥቆማ @atc_newsbot
https://t.me/atc_news