Get Mystery Box with random crypto!

አስትሮኖሚ 🚀🔭

የቴሌግራም ቻናል አርማ astronomy21bk — አስትሮኖሚ 🚀🔭
የቴሌግራም ቻናል አርማ astronomy21bk — አስትሮኖሚ 🚀🔭
የሰርጥ አድራሻ: @astronomy21bk
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.05K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ለ አስትሮኖሚ አፍቃሪያን የተዘጋጀ፤በ ህዋ ላይ ስላሉ ነገሮች የሚያቀርብ ቻናል ነው።
=› በዚህ ቻናል ውስጥ ስለ፦
👉🏾 አስደናቂው የኢትዮጵያ የህዋ ስልጣኔ
👉🏾 በስርአተ ፀሀይ ያሉ ነገሮች
👉🏾 በጋላክሲያችን ያሉ ነገርች
👉🏾 በምድር ስላሉ አስደናቂ ነገሮች
፨የምናይ ይሆናል፨
YouTube
https://youtube.com/channel/UClfQSinys6_kEjpn-l_nzow

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-21 16:59:26
ለመሬት ቅርብ የሆነችው ፕላኔት ማን ናት?
Anonymous Quiz
23%
ሜርኩሪ
46%
ማርስ
23%
ቬነስ
6%
ጁፒተር
2%
ሳተርን
810 voters5.7K views13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 19:35:37
የአለማችን ጥልቁ ጉድጓድ እና አስገራሚው ግኝት

የአለማችን ጥልቁ ጉድጓድ የሚገኘው በሩሲያ ሲሆን የተቆፈረው ደግሞ ለሳይንሳዊ ምርምር ነበር።

የጉድጓዱ እርዝመት ደግሞ 13km ወይም 13,000m ነው ሳይንቲስቶች አስቀድመው እስከ 15 km የመቆፈር እቅድ ይዘውለት ነበር ይሁን እንጂ ጉድጋዱ ከተገመተው ሁለት እጥፍ በላይ በመሞቁ እና በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ቁፍሮው እንዲቆም ተደርጓል።

በቁፍሮው ሳይንቲስቶች ሶስት አስገራሚ ግኝቶችን አግኝቷል አንዱ እና ዋንኛው ግኝት ደግሞ በተለምዶ ሲሆል ወይም ገሀነብ የሚባለው ቦታ ከመሬት በታች ይሆን እንዴ ? ያስባለ ነበር።

ሳይንቲስቶች ቁፍሮዎን ካቆሙ በዋላ የደምፅ መቅጃን ወደ ስምጡ ጉድጓድ ልከው የሰሙት ድምፅም ይሄንኑ የሚደገፍ ነበር።

ሳይንቲስቶቹ ከምድር በታች ሰማን ያሉት አሰቃቂው ደምፅ በተለምዶ ሲሆል/ገሀነብ ውስጥ የሚቃጠሉ ፍጡሮች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።

ይሁን እንጂ ብዙዎች ይሄንን ግኝት አልተቀበሉትም ነበር እንደ ምክንያት የሚነሳው ደግሞ ይሄንን የመሰለ መረጃ ማግኘት ከቻሉ ለምን ቁፍሮን አቆሙት የሚለው ጥያቄ ነው።
አ.አስትሮኖሚ
@astronomy21bk
@astronomy21bk
5.1K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 19:27:41
ኢትዮጵያ ስንት ሳተላይት አምጥቃለች?
Anonymous Quiz
3%
5
58%
2
30%
1
2%
10
7%
3
856 voters4.3K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-18 19:44:52 የቀጠለ

የፕላኔታሪ ሳይንቲስት የሆነው ሪቻርድ ቢንዜል ይህን ጉዳይ "ደስታ የሚሰጥ ነገር ቢኖር እንደዚህ ግዙፍ የሆነ አካል በጣም ቀርቦ የሚታየው በሺሕ ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ በመሆኑ ነው፣ ስለሆነም ይህ ክስተት ምን ዓይነት ዕድል ነው? በማለት ነበር የገለጸው፡፡ የአስቴሮይዱ ቅርበት እና መጠኑ ደማቅነቱን ስለሚጨምር ወደ 2 ቢሊዮን ገደማ የሚደርሱ ሰዎ በባዶ ዓይናቸው አስትሮይዱ ሲያልፍ ማየት መቻል አለባቸው ብሏል ቢንዜል፡፡

በእርግጥ ሳይንቲስቶች የጠፈር ዐለቱ ወደ መሬት ከመቅረቡ በፊት በቂ ዝግጅት ለማድረግ ድፍን 10 ዓመታት አላቸው ያ ማለት ከክስተቱ መማር የሚፈልጉትን ነገሮች በዝርዝር ለማስቀመጥ፣ መሬት ላይ ምን ዓይነት ነገሮችን መከታተልና የሚያጋጥሙ ነገሮችን እንዴት መቋቋም እንደሚቻል ለማወቅ እንዲሁም ለዚህ ተግባር የሚውሉ መንኵራኵሮችን ለማዘጋጀት ጊዜ አላቸው ማለት ነው፡፡

ምንም እንኳን ሳይንቲስቶች አፖፊስ በ2029 ምድርን እንደማይመታት በአዎንታዊነት ቢናገሩም፣ ለወደፊት በብዙ 0ሠርተ ዓመታት ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን እንዳይከሰቱ ማድረግ ገና አልቻሉም፡፡ ከምድር በቅርብ ርቀት ፀሐይን የሚዞሩ ሌሎች በርካታ ትላልቅ የጠፈር ዐለቶች አሉ።

የፕላኔት መከላከያ (planetary defense) ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች እነዚህን ነገሮች በመከታተል ስጋት የሚፈጥሩ ማናቸውንም ሰማያዊ አካላት ማስቀየስ የሚችሉ መንገዶችን ያዘጋጃሉ፡፡ ስለ አፖፊስ የተሰበሰበው መረጃ ሳይንቲስቶች ስለእነዚህና ሌሎች አስትሮይዶች ምን እንደሚያውቁ የሚያሳውቅነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ልዩ የጠፈር ዐለት እስከ ዛሬ ድረስ በጣም አደገኛ እንደሆኑ በሳይንስ ሊቃውንት ከተለዩት አስትሮይዶች ጋር 80 በመቶ ያህል ተመሳሳይነት አለው።

የአስትሮይድ ሳይንስ ሊቃውንት እና የፕላኔቶች የመከላከያ ባለሙያዎች ቀደም ብለው ነው ይህንን ሥራ የጀመሩት ተከታታይ በቀረቡት ጥናቶች ከአሁን ጀምሮ በ2029 ስከሚከሰተው የአፖፊስ በቅርብ ርቀት ማለፍ ድረስ ባሉ ጊዜያት ሊያጤኗቸው በሚገባቸው ርዕሶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል፡፡ እነዚያ የታቀዱት ምርመራዎች የሰው ልጅን የማወቅ ፍላጎት እንዲሁም የምንኖርበትን ሥርዓተ ፀሐይ የበለጠ በመረዳት ዙሪያ ያሉ ጥያቄዎችን በማንሣት ሁለቱን የጥናት ርፎች የሚያገናኙ ድልድዮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ያህል የምህንድስና ጠቢባን የጠፈር ዐለቱን ለመፈረካከስ ወይም ከምድር ጋር እንዳይጋጭ የምሕዋር መንገዱን በማዛባት ከመሬት ጋር የሚኖረውን ግጭት የሚከላለሉበትን ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል ግንዛቤን ማግኘት ከፈለጉ የአፖፊስ ውስጣዊ መዋቅር ሁነኛ የመረጃ አካል ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም መረጃ አፖፊስ እንዴት 1ደተገነባ ፍንጭ ሊሰጥም ይችላል።

በ2029 ከምድር በቅርብ ርቀት አስትሮይዱ በሚያልፍበት ወቅት አንዲዛባ ማድረግ የሚችለው የምድር የስበት ኃይል መጠን ቁልፍ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ አንዳንድ የሳይንስ ሊቃውንት ከዚህ ቀደም በቅርብ ርቀት በመብረር ያለፉት አስትሮይዶችም ተጽእኖ እንደደረሰባቸው ይናገራሉ።
ለፕላኔቶች የመከላከያ ጠበብቶች በጣም አስፈላጊ የሆነ ንድ ጥያቄ የአስትሮይድ ሳይንስ ሊቃውንት የሚጠይቁት ነገር ቢኖር - የፀሐይ ጨረር የአፖፊስን ምሕዋር በምን ያህል መጠን ተጽዕ እንደሚያደርግበት ነው፡፡ የያርኮቭስኪ ተጽዕኖ (yarkovsky effect) ተብሎ የሚጠራው ይህ ክስተት
በአስትሮይዱ የቀን እና የሌሊት ጎኖች (የፀሐይ ብርሃን የበራባቸውና ያልበራባቸው) መካከል ባለው የሙቀት ልዩነት የሚከሰት ነው፡፡
#ሼር
@astronomy21bk
@astronomy21bk
4.0K views16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 18:01:31 አፖፊስ (Apophis) አስትሮይድ

አፖፊስ (Apophis) የተባለ ግዙፍ አስቴሮይድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በዕለተ ዐርብ ሚያዚያ 5/ 2021 ዓ.ም ወይም እንደ ጎርጎርዮሳዊው አቆጣጠር ሚያዝያ (April 13, 2029) ከምድር በቅርብ ርቀት እንደሚሄድ ሳይንሳዊ ጥናቶች ያሳያሉ።

በተጠቀሰው ቀንና ዓመት ሥርዓተ ፀሐይ አስደሳች ስሜት የሚሰጥ ነገር ያስተናግዳል፡፡ አንድ ትልቅ አስትሮይድ በሰማይ ላይ እየከነፈ ይታያል - “ይህ ክስተት የሚያስፈራ ሳይሆን ልዩ የደስታ ስሜት የሚሰጥ ነው” ይላሉ የዘርፉ ሳይንቲስቶች፡፡

አፖፊስ (Apophis) ወይም 99942 አፖፊስ በመባልም የሚጠራው ይህ አስትሮይድ ወደ 1,100 ጫማ (340 ሜትር) ወደ ጎን የሚረዝም ሲሆን፤ ከመሬት በ19,000 ማይሎች (31,000 ኪ.ሜ) ባለ ርቀት ውስጥ ያልፋል፡ መሬትን የመምታት ዕድሉ
ኪ.ሜ) ባለ ርቀት ውስጥ ያልፋል፡፡ መሬትን የመምታት ዕድሉ 2.7 ፐረሰንት ነው! ይህም በጣም አስፈሪ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ሳይንቲስቶች ለክስተቱ በጎ አመለካከት በመያዝ _ ምድርን እንደማይመታት ይናገራሉ፡፡

እንደውም ሳይንቲስቶቹ እንደሚሉት ከሆነ ወደ ምድር የሚቀርቡ አስትሮይዶችን በትክክል እንዲገነዘቡ የሚያስችል በሕይወት ዘመን አንድ ጊዜ የሚያገኙት ዕድል ነው ባይ ናቸው፡፡

በዚህ በተጠቀሰው ዕለት አንድ የብርሃን ሽራፊ በሰማይ ላይ ይበራና፤ እየደመቀ ፍጥነቱን እየጨመረ ሲሄድ ይታያል: አን ነጥብ ላይ ሲደርስ ልክ እንደ ትንሹ ድብ (ttle Dipper) ላይ እንዳሉት ከዋክብት ይደምቃል፡፡

ይህ ታዲያ ሳተላይት ወይም አውሮፕላን ሳይሆን 99942 አፖፊስ የተባለው አስትሮይድ ነው እንደ አጋጣሚ ሆኖ በጥንታዊው ግብጽ “የነውጥ ጌታ” (lord of chaos) የሚል ስያሜ የተሰጠው አስትሮይድ አፖፊስ ከ2004 ጀምሮ ይታወቃል፡ ይህም አስትሮይድ ወደ በምድር አቅራቢያ ያለ አካል በእንግሊዝኛው ኒር-እርዝ ኦብጀክት /near-Earth object NEO) በመባል ይታወቃል ናሳ እንደተናገረው፣ ምንም እንኳን ሳይንቲስቶች በቅደም ተhተል ከ16 እስከ 33 ጫማ (ከ5-10 ሜትር) መጠን ያላቸውን ትናንሽ አስትሮይዶችን በተመሳሳይ ርቀት ምድር አቅራቢያ ሲበሩ ቢመለከቱም፣ የአፖፊስን መጠን ያላቸው አስቴሮይዶች በቁጥር ጅግ ያነሱ በመሆናቸው በእንደዚህ ያለ ርቀት ወደ ምድር ቀርበው ብዙ ጊዜ አያልፉምበናሳ ለመሬት ቅርብ አካላትን የሚያጠና ማዕከል | ይሬክተር የሆኑት ፖል ቾዳስ (Paul Chodas) እንደሚሉት፡ | ፖፊስ በአሁኑ ጊዜ ከሚታወቁት ወደ 2,000 ለሚጠጉ አደገኛ ሊባሉ ከሚችሉ አስትሮይዶች የሚመደብ ነው፡ ናሳ ስለጉዳዩ ሲገልጽ “ይህ አስትሮይድ በ2029 በቅርብ ርቀት በሚያልፍበት ወቅት ከምድር ሆነው ለሚመለከቱት ታዛቢዎች “እንደ ተንቀሳቃሽ ኮኮብ የብርሃን ዓይነት” ይመስላል በማለት ተናግሯል፡፡ ወደ ምድር የበለጠም ሲያብራራው በመጀመሪያ በደቡባዊው ንፍቀ ክበብ በምሽት ሰማይ ላይ ከአውስትራልያ ምሥራቅ ጠረፍ አንሥቶ እስከ ምዕራብ ዳርቻ ከምድር በላይ ሲበር ያለምንም የማሳያ ርዳታ በባዶ ዐይን የሚታይ ይሆናል፡ አፖፊስ ከአውስትራሊያ ሰማይ ሚታይበት ጊዜ በአሜሪካ ምሥራቃዊ ጠረፍ የንጋት አጋማሽ ሆናል፡፡

ከዚያ የህንድ ውቅያኖስን በማቋረጥ፣ ከስዓት በኋላ ላይ ለአሜሪካ ምሥራቃዊ በኩል የምድር ወገብን ያቋርጣልወደ ምዕራብ በመጓዝ በአፍሪካ ላይ ያታያል በምሥራቅ የዴይላይት ሰዓት አቆጣጠር (EDT) አመሻሽ ላይ 6:pm ከመሆኑ በፊት በጣም በመቅረብ ፣ አፖፊስ ከአትላንቲክ ውቅያኖስ በላይ ይሆንና በፍጥነት ስለሚንቀሳቀስ አትላንቲክን በአንድ ሰአት ያቋርጣል ። በምስራቅ ሰአት አቆጣጠር (ETD) ምሽት አካባቢ በ7:p.m ሰአት አስትሮይዱ አሜሪካን አቋርጦ ይሄዳል ።

ይቀጥላል ...
#ሼር
@astronomy21bk
@astronomy21bk
3.9K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-16 16:34:37
ቀለበት የሌለው ፕላኔት የቱ ነው?
Anonymous Quiz
14%
ሳተርን
13%
ጁፒተር
49%
ማርስ
11%
ኔፕቲውን
12%
ኡራነስ
636 voters3.3K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-15 18:17:06 አስር የእስፔስ እውነታዎች

1. ስፔስ ሙሉ በሙሉ ዝም ያለ ነው

በጠፈር ውስጥ ከባቢ አየር የለም ፣ ይህ ማለት ድምጽ መስማት የሚችልበት መካከለኛ ወይም መንገድ የለውም ማለት ነው።

2. በእኛ የፀሐይ ስርዓት ውስጥ በጣም ሞቃት ፕላኔት 450 ° ሴ ነው።

ቬነስ በሶላር ሲስተም ውስጥ በጣም ሞቃታማ ፕላኔት ናት እና በ 450 ዲግሪ ሴንቲግሬድ አካባቢ አማካይ የወለል ሙቀት አላት ቬነስ ለፀሐይ ቅርብ የሆነች ፕላኔት እንዳልሆነ ያውቃሉ? ያ ሜርኩሪ ነው። ከዚያ ሜርኩሪ በጣም ሞቃታማ ይሆናል ብለው ያስባሉ ፣ ግን ሜርኩሪ ከባቢ አየር የለውም (የሙቀት መጠንን ይቆጣጠራል) ፣ ይህም ትልቅ መለዋወጥን ያስከትላል።

3. ሙሉ የናሳ ስፔስ ሱት 12,000,000 ዶላር ያወጣል።

ጠቅላላው ልብስ አሪፍ $ 12m ዶላር ሲያስከፍል ፣ ከዚያ ወጪ 70% ለቦርሳ እና ለቁጥጥር ሞዱል ነው። ሆኖም ፣ ናሳ የሚጠቀምበት የጠፈር ተስማሚነት በ 1974 ተገንብቷል። እነዚህ በዛሬ ዋጋ ቢገዙ ኖሮ 150 ሚሊዮን ዶላር ይገመት ነበር!

4. የፀሐይ ግዝፈት የፀሐይ ሥርዓቱን 99.86% ይይዛል።

ፀሐይ በፀሐይ ሥርዓታችን ውስጥ ካለው የጅምላ መጠን 99.86% የሚሆነው ከምድር 330,000 እጥፍ ያህል ነው። ፀሐይ አብዛኛው ሃይድሮጂን (ሶስት አራተኛ ዋጋ ያለው) እንደሆነች ቀሪው ግዝፈቱ ለሂሊየም እንደተመሰረተ ያውቃሉ? ፀሐይ ድምጽ ቢኖራት ከዚያ ሁሉ ሂሊየም ከፍ ያለ እና የሚጮህ ነበር?

5. አንድ ሚሊዮን መሬቶች በፀሐይ ውስጥ ሊስማሙ ይችላሉ

ፀሀይ ትልቅ ናት ፣ በግምት 1.3 ሚሊዮን የሚሆኑት ምድሮች በውስጣቸው ሊስማሙ ይችላሉ ወይም መሬቶች ክብ ቅርፃቸውን ከያዙ 960,000 ይጣጣማሉ። ግን ያንን የምድር ብዛት በዓይነ ሕሊናዎ ማየት ይችላሉ?


6. በወተት መንገድ ውስጥ ከዋክብት ይልቅ በምድር ላይ ብዙ ዛፎች አሉ

በፕላኔቷ ምድር ላይ ሦስት ትሪሊዮን ገደማ ዛፎች አሉ ፣ እና ከ100-400 ቢሊዮን ከዋክብት መካከል ፣ በግምት ፣ በጋላክሲው ውስጥ።

7. በማርስ ላይ ያለው ፀሀይ ሰማያዊ ይመስላል
በምድር ላይ በፀሐይ መጥለቂያ ውስጥ ቀለሞች የበለጠ አስገራሚ እንደሆኑ ሁሉ ፣ ናሳ እንደሚለው በማርስ ላይ ፀሐይ ስትጠልቅ ከቀይ ፕላኔቷ ለሚመለከቱ የሰው ታዛቢዎች ሰማያዊ ይመስላል። ጥሩ አቧራ በሰማዩ የፀሐይ ክፍል አቅራቢያ ሰማያዊውን የበለጠ visibilke ያደርገዋል ፣ የተለመደው የቀን ብርሃን ደግሞ የቀይ ፕላኔት የታወቀ የዛገ አቧራ ቀለም ለሰው ዓይን በጣም አስተዋይ ያደርገዋል።

8. በምድር ላይ ካለው የአሸዋ ቅንጣቶች ይልቅ በዓለም ውስጥ ብዙ ኮከቦች አሉ።
አጽናፈ ሰማይ ከራሳችን ጋላክሲ “ሚልኪ ዌይ” በላይ ይዘልቃል ፣ ለዚህም ነው ሳይንቲስቶች በጠፈር ውስጥ ስንት ኮከቦችን ብቻ መገመት የሚችሉት። ሆኖም የሳይንስ ሊቃውንት አጽናፈ ሰማይ በግምት 1,000,000,000,000,000,000,000,000,000 ኮከቦችን ወይም ሴፕቲሊንን እንደያዘ ይገምታሉ። በምድር ላይ ያለውን እያንዳንዱን የአሸዋ ቅንጣት ማንም ሊቆጥረው የማይችል ቢሆንም ፣ በሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች የተገመተው አጠቃላይ ግምቱ ሰባት ኩንታል ፣ አምስት መቶ ኳድሪሊዮን እህል አካባቢ ነው። ያ በጣም ትልቅ የአሸዋ ግንብ ነው!

9. በቬኑስ ላይ አንድ ቀን ከአንድ ዓመት ይረዝማል።
ቬነስ ቀኑን ለማጠናቀቅ 243 የምድር ቀናት የሚወስድ ዘገምተኛ ዘንግ ማዞሪያ አለው። በፀሐይ ዙሪያ ያለው የቬኑስ ምህዋር 225 የምድር ቀናት ነው ፣ ይህም በቬኑስ አንድ ቀን በቬኑስ ከ 18 ቀናት ያነሰ ቀን ያደርገዋል።

10.
ከአልማዝ የተሠራች ፕላኔት ከምድር ሁለት እጥፍ ትበልጣለች “ሱፐር ምድር” የተባለው 55 Cancri e ፣ ምናልባትም በግራፋይት እና በአልማዝ ተሸፍኗል። ወደዚያች ፕላኔት ጉብኝት ማድረጉ ምናልባት እዚያ ለመድረስ ለሚያስፈልገው የ 12 ሚሊዮን ዶላር የጠፈር ልብስ ይከፍላል!
@astronomy21bk
3.9K views15:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:16:47
በጨረቃ ብዛት የምትበልጠው ፕላኔት ማን ናት ?
Anonymous Quiz
28%
ቬኑስ
43%
ማርስ
9%
መሬት
19%
ሜርኩሪ
660 voters3.1K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 18:01:24
ጋሊልዩ ጋላሊ

ለብዙ አመታት ፀሐይን በቴሌስኮፕ በማየተ እና ለማጥናት በመሞከሩ ምክንያት አይኑ የታወረ ሳይንቲስት ነበረ።

ምድር ናት ፀሐይን የምትዞረው በማለቱ ለ8 አመተ የታሰረ ለአልበረተ አንስታይን ምርጡ ሳይንቲስት የነበረው ጋሊልዮ ጋላሊ የተወለደው 1564 ነበረ።

ጋሊልዮ ጋላሊ ቤተሰቦቹ በእክምና ዘረፈ ማለትም ሜድስን እንዲማር ቢገፍፉትም ለፊዚክስ እና ለሒሳብ ካለው ፍቅር የተነሳ ብዙ ሳይገፍበተ ቀርቷል።

ጋሊልዮ መሬት ናት ፀሐይን የምትዞረው በማለቱ በወቅቱ እንግልት እና ለእስረ የበቃው በዛ ጊዜ ይታመነ የነበረውን ፀሐይ መሬትን እንደምትዞር ነበረ ይሄንን ሐሳብ በመቃረኑ ነበረ ለስር የበቃው።

እራሱ በሰራው ቴሌእስኮፕ ጨረቃ ተራራ እንዳላት ጁፒተር የተባለ ፕላኔት ልክ እንደ መሬት የራሱ የሆኑ ጨረቃወች እንዳሉት ቀድሞ ያወቀ እንዲውም ጁፒተርን በራሱ ቴሌስኮፕ ቀድሞ ማየተ የቻለ ሳይንቲስት ነበረ።

በ1990 ናሰ ወደ ጁፒተረ የላካትን እስፔስ ክራፍት በጋሊሎ ስም ሰይሟት ነበር

እጅግ የሚታወቅበተ ግኝቱ ደግሞ ..ሁለተ ነገሮች ወደ መሬት በእኩል ሰሀተ ቢለቀቁ በእኩል ሰሀተ መሬት ዬነካሉ የሚለው ነው። ይሄንን እሳቤ የሰው ልጆች ጨረቃ ላይ አንድ የዶሮ ላባ እና መዶሻ ሞክረውት ተሳክቷል።

ይሄንን እሳቤ መሬት ላይ ብንሞክር መዶሻው ቀድሞ ይወድቃል ለምን?

gravity=9.81m/s*s ወይም አንድ ድንጋይ,የማንጎ ፍሬ ወዘተ ወደ ምድር ስትወድቅ ፍጥነቷ በአንድ ሰከንድ ውስጥ 9.81 መጠነ እየጨመረ ይሄዳል እንደማለተ ነው ለዚህ ቋሚ ቁጥር መገኘት አስተዋፆ ያደረገ አሳብ ነበረ።

እንዲሁም ሌሎች ግኝቶች አሉት....

@astronomy21bk
3.5K views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 17:39:38 ኤለን መስክ ያስወነጨፋት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ልትጋጭ ነው


የኤለን መስክ ሕዋ ምርምር ተቋም ያስወነጨፋት አንዲት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ተጋጭታ ልትፈነዳ እንደምትችል ተሰምቷል።

ፋልከን 9 የተሰኘችው ሮኬት ወደ ሕዋ የተወነጨፈችው በፈረንጆቹ 2015 ሲሆን ነገር ግን የያዘችው ነዳጅ በመገባደዱ ምክንያት ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ ምድር ከመመለስ ይልቅ ሕዋ ላይ ስትዋልል ነበር።

ጠፈርተኛው ጆናታን ማክዶዌል፤ ከጨረቃ ጋር የተጋጨች የመጀመሪያዋ ከቁጥጥር ውጭ የሆነች ሮኬት ትሆናለች ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር መጋጨቷ ያለው ፋይዳ ይህን ያህል የሚባል አይደለም።

ከሰባት ዓመታት በፊት ሥራዋን ጨርሳ ሕዋ ላይ የተረሳችው ሮኬት ከ1.6 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት አዳርሳለች።

ስፔስኤክስ የተባለው የኤለን መስክ የሕዋ ምርምር ተቋም ወደፊት ሰዎች በሌሎች ፕላኔቶች ላይ እንዲኖሩ ማመቻቸት የሚል ዓላማ አለው።

ሮኬቷ ከ2015 ጀምሮ በተለያዩ የምድር፣ የጨረቃና የፀሐይ የስበት ኅይሎች አቅጣጫዋን እየቀያየረች ቆይታለች ይላሉ ጠፈርተኛው።

"የስበት ሕግን ተከትላ ከጥቅም ውጭ ሆና ነበር ማለት ይቻላል።"

ይህች ሮኬት ብቻ ሳትሆን ለተልዕኮ ተስወንጭፈው ዕቅዳቸውን ያሳኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሮኬቶች ሕዋ ላይ እየዋለሉ ይገኘሉ።

"ባለፈው አስር ዓመት ከቁጥጥራችን ውጭ የሆኑ ቢያንስ 50 ትላልቅ ሮኬቶች አሉ። ከዚህ በፊትም ሳናውቀው ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል። ይሄኛው የመጀመሪያው የታወቀ ክስተት ይሆናል ማለት ነው" ይላሉ ማክዶዌል።

የፋልከን 9 ወደ ጨረቃ መገስገስ ሊታወቅ የቻለው ጋዜጠኛ ኤሪክ በርገርና የዳታ ተንታኙ ቢል ጌሪ ባደረጉት ክትትል ነው።

ሮኬቷ፤ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወርሃ መጋቢት አራት ከጨረቃ ጋር እንደምትጋጭ ተገምቷል።

"4 ቶን የምትመዝን ከኋላ ሞተር ያዘለች ብረት ማለት ናት። ይህን ያህል ክብደት ይዛ በሰዓት ከ8 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር በላይ እየተጓዘች ስትጋጭ የሚፈጠረው ነገር አስደሳች አይሆንም" ሲሉ ያክላሉ።

ሮኬቷ ከተጋጨች በኋላ የጨረቃ መልክዓ ምድር ላይ አነስ ያለ ሰው ሰራሽ ጉደጓድ ትፈጥራለች።

ሶፍትዌር ተጠቅሞ ለምድር የቀረቡ ሕዋ ላይ ያሉ ቁሶችን የሚከታተለው ቢል ጌሪ ሮኬት መጋቢት 4 ከጨረቃ እንደምትጋጭ ገምቷል።

በፈረንጆቹ 2009 ፕሮፌሰር ማክዶዌልና ሌሎች ጠፈርተኞች መሰል ነገር ቢፈጠር ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን ሐሳብ በቤተ ሙከራ አዳብረውታል።

ይህ ማለት ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር ስትጋጭ ሳይንቲስቶች ብዙም የሚማሩት አዲስ ነገር የለም ማለት ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ።

አክለው አሁን ምንም እንኳ ሕዋ ላይ እየዋለሉ ያሉ ቁሶች እየሄዱ ሲጋጩ ችግር ባይፈጥሩም ወደፊት ግን አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ።

ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር እስክትጋጭ ባለው ጊዜ የስበት ህግን ተከትላ ሕዋ ላይ ትንሳፈፋለች። @astronomy21bk
@astronomy21bk
8.9K views14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ