Get Mystery Box with random crypto!

ደስ የሚለው ነገር የፍርዱ ቀን ዳኛ አላህ መሆኑ ነው =========================== | አዲስ መረጃ

ደስ የሚለው ነገር የፍርዱ ቀን ዳኛ አላህ መሆኑ ነው
========================================
ያ አሒባኢ ሰውማ ቢሆን አልቆልን ነበር
*
سأل أعرابي ابن عباس رضي الله عنهما..
አንድ የገጠር ሰው (በደዊ) ወደ ኢብኑ ዐባስ ዘንድ አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና መጣና እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፦
(من يحاسب الناس يوم القيامة؟)
«ሰዎችን የፍርዱ ቀን የሚመረምረው ማነው »

قال :الله
ኢብኑ ዐባስም «አላህ ነው!» ብለው መለሱለት።
.قال الأعرابي :نجونا ورب الكعبة
ገጠሬውም እንዲህ አለ፦ «በከዕባ ጌታ ይሁንብኝ፤ ነጻ ወጣን » አላቸው።
..قال ابن عباس :كيف؟
ኢብኑ ዐባስም «እንደት?» አሉት።
قال: إن الكريم إذا قدر غفر. ...
ገጠሬውም እንዲህ አለ፦ "አላህ እኮ (ቸሩ ጌታ) በቻለ ጊዜ ይቅር ይላል!" አላቸው።
لا إله إلا الله. .ما أعظم حسن الظن في الله!!

የሚገርም በአላህ መመካትና መልካም ጥርጣሬ
*
[በይሀቂይ ዘግበውታል።]
||
እውነትም "ነጀውና!" ወላሂ
እርሱ ጌታችን እኮ አንዳችንንም የማይበድል ነው።
( وَلَا يَظْلِمُ رَبُّكَ أَحَدًا !)
«ጌታህም አንድንም አይበድልም።»
[አል-ከህፍ፡ 49]
*
እንዳውም በመጥፎ ሥራችን ምትክ ወደ መልካም መቀየር የሚችል አዛኝ ጌታ
እናት ለልጇ ከምታዝነው በላይ፤ ለባሮቹ የሚያዝን ረሒም
||
አላህ ሆይ!
በአንተ ላይ ጥሩ ጥርጣሬና ጠንካራ ተስፋ ካላቸው ባሮችህ አድርገን።
||