Get Mystery Box with random crypto!

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ሆይ 'መግደል መሸነፍ ነው' ባሉን መሰረት በዝረራ ተሸንፈዋል!!! ብዙ ብ | አዲስ መረጃ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር ሆይ "መግደል መሸነፍ ነው" ባሉን መሰረት በዝረራ ተሸንፈዋል!!!

ብዙ ብዙ ተናግረዋል። የሚናገሩት እና የሚሰሩት ግን ለየቅል የመሆኑ ጉዳይ በአለም መድረክ ጭምር አፀያፊ ተቀፅላ ስም አሰጥቶዎታል። እርሶም እልህ የተጋቡ ይመስል "የተናገርኩትን ከምፈፅም ስልጣኔ ይፈፀም" በሚመስል መልኩ ከራሶት ጋር በተቃራኒ ቆመው ተገኝተዋል።

መቼም ፖለቲከኛ ነዎት እና ቃል አባይ መሆንዎ የሚጠበቅ ቢሆንም የእርሶ ግን አንገሸገሸ። ፖለቲከኛ ነዎት እና ህዝብን ማጭበርበር እና ማታለል የሚጠበቅ ነው። ከተነቃ ግን መንገድ መቀየር የብልህ ፖለቲከኛ መንገድ ነው።

እርሶ ግን ከተነቃቦት በኋላም የማታለል እና የማጭበርበር መንገዶን ለመቀጠል ቆርጠዋል። ይህ የብልህ ፖለቲከኛ መንገድ ሳይሆን የጅል ዲክታተር መንገድ ነው። ህዝቡ አልታለልም አልጭበረበርም ካለ በጉልበት እና በጥይት ለመግዛት ማሰብ አንድ ነገር ነው፣ በጉልበት እና በጥይት ለማታለል ማሰብ ግን ድንቁርና ነው።

ክቡርነቶ ሌላው ሁሉ ይቅርና አንዷን ቃልዎን ብቻ አክብረው "ተሸንፌያለው" ይበሉ እና ይመኑ። በራሱ ቃል መሰረት "መግደል መሸነፍ ነው"። እርሶ ግን መግደል ማሸነፍ ነው ያሉን ይመስል ያለ ብሄር እና ሀይማኖት ልዩነት ህዝቡ ላይ የጥይት ናዳ እያርከፈከፉ ይገኛሉ።

ዛሬ ላይ ደግሞ የግድያ መድረኩን ወደ መሃል አዲስ አበባ ወስደውታል። የፈጣሪያቸውን ቃል ሊፈፅሙ መስጂድ በተገኙ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በተቀደሰ የሀይማኖት ስፍራ ውስጥ የጥይት እሩምታ ከፍተው ብዙዎችን ለሞት ዳርገዋል። ይህም አልበቃ ብሎዎት መትረፍ የሚችሉት እንዳይተርፉ አንቡላንስ ላይ መንገድ አስዘግተዋል። እናም ጠሚ ሆይ መግደል መሸነፍ ነው ባሉን መሰረት በዝረራ ተሸንፈዋል።