Get Mystery Box with random crypto!

Artios Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ artios_media — Artios Media A
የቴሌግራም ቻናል አርማ artios_media — Artios Media
የሰርጥ አድራሻ: @artios_media
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.50K
የሰርጥ መግለጫ

We Are Artios! We are complete!
Maturity matters growth doesn't alone!
#Artios spiritual journey towards #maturity.
"So that the man of God may be complete and equipped for every good work." 2 Tim 3:17
Join the complete journey @artios_media

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 11:58:20 ይህንን ፖስተር ( ሦስተኛውን) ፕሮፋይል ፒክቼርና ሼር እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃችኋለሁ !!

ተባረኩ!!!
372 viewsBayissa Gamachu, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:58:20
653 viewsBayissa Gamachu, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:58:20
413 viewsBayissa Gamachu, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 11:58:19
364 viewsBayissa Gamachu, 08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 10:30:58
@artios_media
@artios_media
@artios_media
1.9K viewsBayissa Gamachu, edited  07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 10:53:33 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ARTIOS DEVOTION
ⓟⓗⓘⓛⓔⓜⓞⓝ
ቀን #7

ማረፊያ አዘጋጁልኝ

ፊል 22 - 25
--------------------------------------------------------------
²² ከዚህም ሌላ፣ ጸሎታችሁ መልስ አግኝቶ ወደ እናንተ ለመምጣት ተስፋ ስለማደርግ ማረፊያ አዘጋጁልኝ።
²³ ከእኔ ጋር የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆነው ኤጳፍራ ሰላምታ ያቀርብልሃል፤
²⁴ እንዲሁም አብረውኝ የሚሠሩት ማርቆስ፣ አርስጥሮኮስ፣ ዴማስና ሉቃስ ሰላምታ ያቀርቡልሃል።
²⁵ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።
--------------------------------------------------------------

ሐዋርያው ጳውሎስ ባለፉት ቀናት ባየናቸው ክፍሎች ውስጥ የመልዕክቱን አንኳር ነጥብ በማያሻማ መልኩ አስቀምጧል።

በሥነ ምግባር ጉድለት ምክንያት ከጌታው የኮበለለው አናሲሞስ በእስር ቤት ውስጥ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ በክርስቶስ በማመኑ ምክንያት ሕይወቱ ሙሉ በሙሉ የመለወጡን ብስራት ለፊልሞና ከነገረው በኋላ የማረሚያ ቤት ቆይታው ሲያበቃ ወደ እርሱ ተመልሶ አገልጋዩ እንዲሆን ፊልሞና እንዲቀበለው በትህትና ልመናን ያቀርባል።

ጳውሎስ ይህንን ጥያቄ ሲያቀርብ ፊልሞና እንደሚታዘዘው በመተማመን ነው። በመሆኑም አናሲሞስን ሲቀበለው ልቡ እንደሚያር ይናገራል። በመቀጠል ሌላ ትዕዛዝ በመስጠት ልቡን ብቻ ሳይሆን ሁለንተናውን የሚያሳርፍበትን የእንግዳ ቤት እንዲያዘጋጀለት ይጠይቃል።

በመጨረሻም ከእርሱ ጋር የወንጌል እስረኞች የሆነው ኤጳፍራ እንዲሁም የአገልግሎቱ አጋሮች ከሆኑት ማርቆር፣ አርስጥሮኮስ፣ ሉቃስና ዴማስ ሰላምታ እየቀረበለት መሆኑን በመግለፅ፤ የጌታ ፀጋ ከመንፈሳቸው ጋር እንዲሆን በመመኘት መልዕክቱን ይቋጫል።

በመጨረሻም የፊልሞና መልዕክት የወንጌል፣ የእርቅ፣ የሥራ ባልደረባነት፣ የትህትና፣ የመቀባበልና የመስዋዕትነትን ሕይወት በሚገባ የተስተዋለበት ድንቅ ደብዳቤ ነው።

ይህንን የፊልሞናን ጥናት እዚህ ላይ ቋጨን። ጌታ ቢፈቅድና በምድር ላይ ብንቆይ የቆላስያስን መልዕክት በማዘጋጀት ላይ ስለሆንን በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደምንመለስ ተስፋ እናደርጋለን።

የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ ቅዱሳንንና አገልጋዮቹን የማሳረፍ አስፈላጊነት።

የዛሬው ፀሎት፦ ጌታ ሆይ የቅዱሳንን ልብና ሁለንተና የማሳርፍ ሰው አድርገኝ


ባይሣ ገመቹ
ሐምሌ 29 , 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን
@artios_media
@artios_media
@artios_media
ይ ላ ሉን
2.2K viewsBayissa Gamachu, 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 08:33:23 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ARTIOS DEVOTION
ⓟⓗⓘⓛⓔⓜⓞⓝ
ቀን #6

ተቀበለው

ፊል 17 - 21
--------------------------------------------------------------
¹⁷ እንግዲህ እንደ ባልንጀራ ከቈጠርኸኝ እኔን እንደምትቀበለኝ አድርገህ ተቀበለው።
¹⁸ አንተን የበደለህ ነገር ቢኖር ወይም የአንተ ብድር ቢኖርበት በእኔ ላይ ቊጠረው።
¹⁹ እኔ ጳውሎስ ይህን በእጄ ጽፌልሃለሁ፤ ያለበትን እኔው እከፍልሃለሁ። አንተም ራስህ የእኔ ስለ መሆንህ ምንም አልናገርም።
²⁰ ወንድሜ ሆይ፤ በጌታ እንድትጠቅመኝ እፈልጋለሁ፤ በክርስቶስ ልቤን አሳርፍልኝ።
²¹ ታዛዥ መሆንህን በመተማመን፣ ከምጠይቀውም በላይ እንደምታደርግ በማወቅ እጽፍልሃለሁ።
--------------------------------------------------------------

ባለፊት ጥናቶች ውስጥ አስፈላጊ መንደርደርያዎችን አይተን ነበር። ዛሬ ደግሞ የፊልሞና ደብዳቤ ማዕከላዊ መልዕክት ያለበትን ክፍል እናያለን። የእነዚህ አምስቱ ቁጥሮች ማጠንጠኛና ቁልፍ ቃል "ተቀበለው" የሚል ሲሆን የቀሩት አረፍተ ነገሮች የዚህ ዋና ሃሳብ አጃቢዎች ናቸው።

ጳውሎስ ከፊልሞና ጋር ጥሩ ወዳጅነት በመገንባት ለዘመናት አብሮ ያገለግላሉ የሥራ ባልደረባ ናቸው። ፊልሞና ጳውሎስን ቢያገኘው እንዴት ባለ ደስታ ተቀብሎት እንደሚያስተናግደው ከደብዳቤው ላይ መረዳት ይቻላል።

ፊልሞና በድሎት የኮበለለው የቀድሞ ባሪያው የነበረ ሰው ወደ እርሱ ሲመለስ በወንጌል በማመኑ ሙሉ በሙሉ ሕይወቱ የተለወጠ፣ ከጳውሎስ ጋር የነበረ፣ ያለበትን ዕዳ የሚከፍልለት አስተማማኝ ሰው እንዳገኘ የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ይዞ ስለ መጣ ለመቀበል የሚያንገራግር የሚሆን አይመስልም።

ምናልባትም በደስታ አቅፎ የሚስመው ሁሉ ይመስለኛል። የአናሲሞስ ክርስቶስን አግኝቶ መዳን፣ ከጳውሎስ ጋር መገናኘት፣ ተመልሶ ደግሞ እርሱን ለማገልገል ፍቃደኛ በመሆን መምጣቱ ለፊልሞናና ለመላው ቤተሰቡና አልፎም በቤቱ ላለችው ቤተክርስቲያን ትልቅ ደስታ ነው። ማን ያውቃል የፀሎታቸው መልስ ቢሆንስ? ጳውሎስም አናሲሞስን መልሶ ስልከው ፊልሞና በደስታ እንደሚበቀለው በመተማመን ነው።

ጳውሎስ በሁለቱ ወዳጆቹ መካከል ያለውን ሸካራ የግንኙነት መስመር ለመጠገን የተጠቀመባቸውን የምልጃ ቃላት ሳስብ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን በደል በሙሉ ከፍሎ ከአባቱ ጋር ሊያቀራርበን ከተጠቀመባቸው የምልጃ ቃላት ጋር በእጅጉ ይመሳሰላሉ።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለብንን ዕዳ ሁሉ ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ በሰራልን የመስቀል ሥራ ከፍሎ ለዘላለም የሚሆን የምልጃ አገልግሎት ተክሎ ከአባቱ ጋር አስታረቀን።

ዉድ ወንድሞቼና እህቶቼ !! እኛም እኮ የማስታረቅ አገልግሎት የተሰጠውን (❝ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋር አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤❞ 2ቆሮ 5: 18) የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን። ደግሞ (❝የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።❞ ማቴ 5: 9) ተብሎ ተነግሮናል።

በእኔ ምልከታ እንደ አማኝ ማህበረሰብ በበዙ ጥላቻና ጦርነት ውስጥ ባለች አገርና ምድር ላይ የምንኖር ሰዎች እንደ መሆናችን መጠን የእርቅና የሰላም ምክንያት ልንሆን ይገባናል።

እግዚአብሔር የልጁን የኢየሱስ ክርስቶስን ልብ፣ የሐዋርያት የመስዋዕትነትን ሕይወት በሙላት እንድኖር ይርዳን!

የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ አብ በልጁ ሥራ ምክንያት የተቀበለኝ ሰው ነኝ!

የዛሬው ፀሎት፦ እግዚአብሔር ሰው ሰውን ከሰው፤ ሰውን ከእግዚአብሔርን ጋር ለማስታረቅ የምኖር ሰው አድርገኝ።

ጌታ ቢፈቅድ ከነገ ወዲያ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!!

ባይሣ ገመቹ
ሐምሌ 25 , 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን
@artios_media
@artios_media
@artios_media
ይ ላ ሉን
2.5K viewsBayissa Gamachu, 05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 00:01:21 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ARTIOS DEVOTION
ⓟⓗⓘⓛⓔⓜⓞⓝ
ቀን #5

የልቤ ሰው - ተወዳጅ ወንድም

ፊል 12 - 16
---------------------------------
¹² የልቤ ሰው የሆነውን እርሱን መልሼ ወደ አንተ ልኬዋለሁ።
¹³ ስለ ወንጌል በታሰርሁበት ጊዜ በአንተ ፈንታ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ለራሴ ላስቀረው ፈልጌ ነበር፤
¹⁴ ነገር ግን አንተ የምታደርገውን መልካም ነገር ሁሉ በውዴታ እንጂ በግዴታ እንዳይሆን ሳላማክርህ ምንም ማድረግ አልፈልግም።
¹⁵ ምናልባት ለጥቂት ጊዜ ከአንተ የተለየው፣ ተቀብለህ ለዘለቄታው አንተ ዘንድ እንድታቈየው ነው፤
¹⁶ ከእንግዲህ ወዲህ ግን እንደ ባሪያ ሳይሆን ከባሪያ በላይ የሆነ ተወዳጅ ወንድም ነው። ለእኔ ተወዳጅ ነው፤ ለአንተ ግን በሥጋም በጌታም ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
---------------------------------

ባለፉት ሦስት ጥናቶች ውስጥ ሐዋርያው ጳውሎስ በአናሲሞስና በፊልሞና መካከል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ለመፍታት እንደ መንደርደርያ ያስቀመጣቸውን ሀሳቦች አይተናል።

በዛሬው ጥናታችን ደግሞ ወደ ዋናው ሃሳብ ይበልጥ የተጠጋበትን መልዕክት እንመለከታለን። የደብዳቤው ማዕከላዊ ሃሳብ ያለው "ተቀበለው" የሚለው በቁ. 17 ላይ የተጠቀሰው ቃል ሲሆን እርሱን በሚቀጥለው ጥናታችን እንደምንዳስስ ተስፋ አደርጋለሁ።

የዛሬው ጥናታችን የመክፈቻ ቃል "የልቤ ሰው" (ቀ.12) የሚል ሲሆን፤ የማይጠቅም የነበረ ሰው (ቁ.11) ወደ ጳውሎስ መጥቶ ምን ቢደረግ? ወይም ምን ቢደረግለት? አልያም በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ተለውጦ ነው የጳውሎስ የልብ ወዳጅ ሊሆን የቻለው? ለሚለውን ጥያቄ መልስ ለመፈለግ ሳስብ በመደነቅ እሞላለሁ።

የልቡ ሰው መሆን ብቻ ሳይሆን ከእርሱ ጋር ሆኖ የጳውሎስ አገልጋይ እስከመሆን የሕይወቱን ሙሉ ለሙሉ መለወጥ ስናይ የወንጌል መልዕክት ምን ያህል ኃይለኛ እንደሆነ መገንዘብ እንችላለን።

ጳውሎስ ለፊልሞና የአናሲሞስን መለወጥ ካበሰረው በኋላ አሁንም ቢሆን ሕጋዊ ባሪያው በሆነው አናሲሞስ ላይ ያለ አሳዳሪው(ፊልሞና) ፈቃድ አንዳች ነገር እንደማያደርግ መናገሩን ስናይ የጳውሎስን ሰው አክባሪነት፣ ጨዋነትና የአገልግሎት ሹመቱን በአግባብ የሚጠቀም በሳል ሰው መሆኑን እንረዳለን።

ጳውሎስ አናሲሞስን ከዚህ "ተቀበለው" ከሚል ትንሽዬ ደብዳቤ ጋር ወደ ፊልሞና ሲልከው በመካከላቸው ሊኖር ስለሚገባው ቤተሰባዊና የሥራ ግንኙነት ግልጽ መመርያ ይሰጣል። እነዚህም፦

1. ለዘለቄታው ፦ ዘለቄታዊ የሚለው አባባል ምናልባት አናሲሞስ የፊልሞና የእድሜ ልክ ባሪያ (በዚያን ዘመን በነበረው የማህበረሰብ አኗኗር መሠረት) ሊሆን እንደሚችል ይጠቁማል። በሌላ በኩል ደግሞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት የነበራቸው የሥራ ውል እንዳይፈርስ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነታቸውን እንዲቀጥል መፈለጉን የሚያመለክት ይመስላል።

2. ተወዳጅ ወንድም፦ ጳውሎስ በአናሲሞስና በፊልሞና መካከል ያለውን የባሪያና የጌታ ግንኙነት በቀጥታ በመቃወም መለወጥ አልፈለገም። ይልቁንም ግንኙታቸውን ከወንጌል ባገኙት ወንድማማችነት ላይ እንዲገነቡት ያሳስባቸዋል እንጂ። ይህ በተዘዋዋሪ ሰው ወንድሙን እንደ ባሪያ መቁጠር የለበትም የሚል አንድምታ አለው። ቁ.16 ላይ "በሥጋም" ሲል አብረው ከመኖራቸው የተነሳ ያላቸውን ቤተሰባዊነት ሲያመለክት በጌታም ሲል በዳግም ልደት ያገኙትን ዘላለማዊ ሕብረት ያሳያል።

በአጠቃላይ ጳውሎስ ትልቅ የምስራች የያዘችውን ደብዳቤ አስይዞ አናሲሞስን ወደ ፊልሞና ሲልከው በመካከላቸው ተፈጥሮ የነበረው ግጭት በሰላም ተፈቶ ሕብረታቸው ታድሶ እንደገና አብረው የመኖር ተስፋ ሰንቆ ስናይ የወንጌልን መልዕክት የመለወጥ አቅም በሚገባ እንገነዘባለን።

የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ ወንጌል በደለኛውን ለውጦ የልብ ሰውና ተወዳጅ ወንድም ያደርጋል።

የዛሬው ፀሎት፦ ጌታ ሆይ በምኖርበት ማሕበረሰብ ውስጥ የእርቅና የሰላም ሰው አርገኝ።

ጌታ ቢፈቅድ ከነገ ወዲያ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!!

ባይሣ ገመቹ
ሐምሌ 23 , 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን
@artios_media
@artios_media
@artios_media
ይ ላ ሉን
2.4K viewsFeyisa Megersa, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 00:01:55 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ARTIOS DEVOTION
ⓟⓗⓘⓛⓔⓜⓞⓝ
ቀን #4

በፍቅር እለምንሃለሁ

ፊል 8 - 11
---------------------------------
⁸ ስለዚህ ማድረግ የሚገባህን እንድታደርግ አዝህ ዘንድ በክርስቶስ ድፍረት ቢኖረኝም
⁹ በፍቅር እለምንሃለሁ፤ እንግዲህ ሽማግሌና አሁን ደግሞ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆንሁት እኔ ጳውሎስ፣
¹⁰ በእስር እያለሁ ስለ ወለድሁት ልጄ ስለ አናሲሞስ እለምንሃለሁ።
¹¹ አስቀድሞ የሚጠቅምህ አልነበረም፤ አሁን ግን ለአንተም ሆነ ለእኔ የሚጠቅም ሰው ሆኖአል።
---------------------------------

ከመጀመሪያው ቀን አንስተን በተመለከትናቸው ክፍሎች ውስጥ የጳውሎስና የፊልሞና ወዳጅነት ጠንካራ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ጳውሎስ በክርስቶስ እንደ ተሾመ አገልጋይ፣ በመንፈሳዊ ልጆቹ ላይ ስልጣኑን ተጠቅሞ ማዘዝ ሲችል ያንን ማድረግ ግን አልመረጠም። የተሻለ ጉልበትና ተጽዕኖ ማሳረፍ ይችላሉ ብሎ ያሰበውን በፍቅርና በትህትና መለመንን ፈለገ።

በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ ጳውሎስ የደብዳቤው አንኳር መልዕክት ወደ ሆነው የአናሲሞስ ጉዳይ እየተንደረደረ ነው። ለፊልሞናም ልመናውን ሲያቀርብ ሁለት ዋና ነጥቦችን ያስቀምጣል፦

የራሱን ሁኔታ፦ ጳውሎስ በዚህ ቦታ ላይ እራሱን ሽማግሌና የክርስቶስ እስረኛ ብሎ ይጠራል። ሽማግሌ ሲል በእድሜ የገፋ ትልቅ ሰው፤ እንዲሁም የአስታራቂነትን ሚና እየተወጣ ያለ አባት መሆኑን ለማመልከት የተናገረ ይመስል።

በመቀጠልም ይህንን ልመና የሚያቀርበው በተመቻቸ ሁኔታ ውስጥ በድሎት ተቀምጦ ሳይሆን በእስር ቤት ሆኖ መከራን እየተቀበለ መሆኑን ይነግረዋል።

በእርቅ ስነ ሥርዓት ውስጥ የአስታራቂዎች ማንነትና ተዓማኒነት ከፍተኛ ሚና ስላለው ጳውሎስ ስለ ሽምግልናውና ስላለበት እስራት መናገሩ ሁለቱን ለማቀራረብ መንገድ እየጠረገ ስለ መሆኑ ጥሩ ማሳያ ናቸው።

የአናሲሞስ ማንነት፦ አናሲሞስ የፊልሞናን ልብ አሳዝኖት ንብረቱን ዘርፎ የኮበለለ ወንጀለኛ ነው። ከዚህ የተነሣ የማይጠቅም ሰው እንደሆነ አሳይቷል። ይህ አይረቤነት ግን አስቀድሞ በሚባል ያለፈ የታሪክ ማህደር ውስጥ ያለ ጉዳይ እንጂ አሁን ግን የሚጠቅም ሰው መሆኑን ጳውሎስ በልበ ሙሉነት ይናገራል።

ፊልሞና እንዲቀበለው የሚለምነው ሰው አሁንም የሚጎዳውን ወንበዴ ሳይሆን በወንጌል እውነት ተለውጦ የሚጠቅመውን አናሲሞስን ነው።

በዛሬው ጥናታችን የጳውሎስን የትህትና፣ የፍቅር ጎዳና ምርጫ ደግሞም ጥልቅ በሆነ የማስታረቅ ጥበብ ሁለት የተጣሉና የተጎዳዱ ሰዎችን እንዴት እያቀረበ እንዳለ አይተናል።

ወንድሞቼ! ያለንበት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሁኔታ የተኮራረፉ፣ የተራራቁ፣ የተጎዳዱ አማኞች ያሉበት ሕብረት እንደሆነች መገመት አያዳግትም። የምንኖርበት ሀገርና ማህበረሰብም ቀላል በማይባል ደረጃ በጠላትነት፣ በጥላቻ እየኖረ እንዳለ ግልጽ ነው።

ስለዚህ ከላይ ያየናቸውን የእግዚአብሔርን ቃል መርህ በመከተል በቤተክርስቲያንና በማህበረሰቡ ውስጥ የእርቅና የሰላም ሰዎች ሆነን እንድንኖር ጌታ ይርዳን።

የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ የፍቅርና የትህትና ልመና ጉልበት!

የዛሬው ፀሎት፦ እግዚአብሔር ሆይ የእርቅ ሰው ሆኜ የሰላምና የፍቅርን ድልድይ እየገነባሁ እንድኖር እርዳኝ።

ጌታ ቢፈቅድ ከነገ ወዲያ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!!

ባይሣ ገመቹ
ሐምሌ 21 , 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን
@artios_media
@artios_media
@artios_media
ይ ላ ሉን
2.1K viewsFeyisa Megersa, 21:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 00:00:03 ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ARTIOS DEVOTION
ⓟⓗⓘⓛⓔⓜⓞⓝ
ቀን #3

ከፍቅር ተራራ ሥር የሚፈልቀው ደስታና መጽናናት

ፊል 4 - 7
--------------------------------------------------------------
⁴ አንተን በጸሎቴ በማስብህ ጊዜ ዘወትር አምላኬን አመሰግናለሁ፤
⁵ ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ያለህን እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ያለህን ፍቅር ሰምቻለሁ።
⁶ በክርስቶስ ስላለን መልካም ነገር ሁሉ በሚገባ ትረዳ ዘንድ፣ እምነትህን ለሌሎች በማካፈል እንድትተጋ እጸልያለሁ።
⁷ ወንድሜ ሆይ፤ የቅዱሳንን ልብ ስላሳረፍህ ከፍቅርህ ታላቅ ደስታና መጽናናት አግኝቻለሁ።
--------------------------------------------------------------

ከትናንተ በስቲያ ፊልሞና በቤቱ ውስጥ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ተቀብሎ፣ ቅዱሳንን በንብረቱ የሚያገለግል ቸር ወንድም መሆኑን አይተን ነበር። ጳውሎስ ይህን መልካም ሰው በፀሎት መሠዊያው ላይ ይዞት በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ በተጨባጭ በሕይወቱ የተገለጠውን የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ እያሰበ በምስጋና እንደሚሞላ ይናገራል።

ስለ እርሱ የሚያመሰግንበትን ጉዳይ በምክንያት ስገልጽ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው እምነቱ ጠንካራ በመሆኑና ማንንም ሳያበላልጥ ቅዱሳንን ሁሉ የሚወድድ ልብ በወዳጁ ውስጥ በማግኘቱ ነው።

በፊልሞና ሕይወት ውስጥ የጎመራው የእምነትና የፍቅር ፍሬ ጥቅሙና ተጽዕኖው በጭራሽ እንደ ቀላል ነገር የሚታይ አይደለም። ጥላቻ፣ ክፋትና አሉባልታ የብዙ ቅዱሳንን ልብ መርዞ ቅን ልቦናን የማበላሸት አቅም እንዳላቸው ሁሉ ፍቅርና ለጋስነት በብዙ እጥፍ የወንድሞችን ሕይወት በደስታና በማጽናናት ሊሞላ እንደሚችል ከጳውሎስና ከፊልሞና ወዳጅነት መረዳት ይቻላል።

በተጨማሪም ጳውሎስ ለየፊልሞና አእምሮው አማኞች በሙሉ በክርስቶስ ውስጥ ስላላቸው መልካም ነገር በሚገባ እንዲረዳ እንዲሁም እምነቱም ታቁሮ እርሱ ጋር ብቻ የሚቀር ሳይሆን ለሌሎች (ያመኑትን ወደ ተሻለ የእምነት ሕይወት፤ ያላመኑትን ደግሞ በክርስቶስ ወደ ማመን በማምጣት) በማካፈል እንዲኖር እጸልይልሃለሁ ይለዋል።

ወገኖቼ! አጠገባችን ያሉት ቅዱሳን፣ የምናገለግላቸው ወዳጆች እንዲሁም የምንኖርበት ማህበረሰብ ልባቸውን የሚያደማ መርዶ በየእለቱ እየሰሙ በቡዙ ጭንቀት ውስጥ እንደሚያልፉ እያየን ነው።

አለማችን ከምን ጊዜውም በላይ አሳዛኝ ዜና የሚሰማባት አኬልዳማ እየሆነች ነው። በዚህ ክፉ ዘመን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ስር የሰደደ እምነት ያለውና በፍቅሩ የቅዱሳንን ልብ እንደ መስኖ ውሃ የሚያረሰርስ ሰው ብፁዕ ነው።

ለሐዋርያው ጳውሎስ ከፊልሞና ልብ ላይ በቅሎ በሁለንተናው ላይ የተገለጠው የመንፈስ ፍሬ ደስታና መጽናናትን የሚያጭድበት ማሳ እንደሆነለት ሁሉ እኛም ለቅዱሳን ሁሉ የመጽናናት፣ የብርታት፣ የደስታ ምክንያት እንድንሆን ጌታ ይርዳን።

የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!!

ዛሬ የማሰላስለው የቃሉ እውነት፦ እምነትና ፍቅር ተጽዕኖ ፈጣሪ ባህርያት ናቸው።

የዛሬው ፀሎት፦ ጌታ ሆይ ልቤን የፍቅርና የእምነት መፍለቂያ ምንጭ አድርግልኝ!

ጌታ ቢፈቅድ ከነገ ወዲያ እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ!!

ባይሣ ገመቹ
ሐምሌ 19 , 2014

ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ
ⒶⓇⓉⒾⓄⓈ

ይ ላ ሉን
@artios_media
@artios_media
@artios_media
ይ ላ ሉን
2.1K viewsBayissa Gamachu, 21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ