Get Mystery Box with random crypto!

የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ ፡፡፡፡፡፡ | Amhara Education Bureau

የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና ከነገ ጀምሮ እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ሰኔ 27/2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቸ ከነገ ጀምሮ በክልል ደረጃ የተዘጋጀውን ሞዴል ፈተና እምደሚወስዱ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ እየሩስ መንግስቱ ተናግረዋል፡፡ ሞዴል ፈተናው ከሰኔ 28 እስከ 30/2015 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን በብሔራዊ ፈተና የሚፈተኗቸውን የትምህርት አይነቶች እንደሚፈተኑ ታውቋል፡፡
ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እያደረጉ ሲሆን በክልል ደረጃ የተዘጋጀው ሞዴል ፈተና በቀጣይ ለሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ዝግጅት ያግዛቸዋል ተብሏል፡፡
የተማሪዎች የዝግጅት ስራ እስከ ፈተናው ጊዜ እንደሚቀጥል የተናገሩት ወ/ሮ እየሩስ ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ለተማሪዎች ውጤታማነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
የትምህርት ዘመኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከሐምሌ 19-30/2015 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ በክልሉ በ574 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች ከ215ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ ተገልጿል፡፡
በዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ፈተና ውጤታማ ይሆን ዘንድ አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ም/ኃላፊዋ ከሐምሌ አጋማሽ ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚጓጓዙ አክለው ገልፀዋል፡፡
ባለፈው አመት የታዩትን አንዳንድ ችግሮች በዚህ አመት እንዳይደገሙ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እየሰራነው ብለዋል፡፡
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ የአካባቢያቸው አንባሳደር መሆናቸውን ተገንዝበው የአካባቢያቸውን ባህልና ወግ የሚያሳዩ ሊሆን ይገባል ፡፡የወላጆቻቸውንና የመምህራንን ውለታ የሚከፍሉበት እና ለሀገራቸው ኩራት የሚሆኑበት ጊዜ መሆኑን አስበው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሊመጡ ይገባል ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን