Get Mystery Box with random crypto!

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ26__27/2015 ባሉት ቀናት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው | Amhara Education Bureau

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ26__27/2015 ባሉት ቀናት ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁ ተገለፀ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ከሰኔ26_27/2015 ባሉት ቀናት መስጠት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል(ሰኔ 25/2015-ትምህርት ቢሮ) ። ለፈተናው አገልግሎት የሚውሉ  ቁሳቁሶች ወደ ትምህርት ቤቶች  የማጓጓዝ ስራው ያለምንም ችግር የተጠናቀቁ ሲሆን በአስፈታኝ ትምህርት ቤቶች ለፈተና አስፈፃሚዎች እና ተፈታኝ ተማሪዎች  ኦሬንቴሽን የመስጠት ስራው ከሰኔ 24/2015 ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል።
በአማራ ክልል 347,966 ተማሪዎች በ5752 ትምህርት ቤቶች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ፈተናው ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በሁሉም አካባቢዎች የትምህርት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው  እየሰሩ ይገኛሉ።
መልካም ዕድል ለተፈታኝ ተማሪዎቻችን!!