2022-07-05 10:06:29
GOLDEN RATIO
በተለያዩ ድንቅና ልዩ የጥንት ቦታወች ላይ የምናስተዉላቸዉ እና የምንመለከታቸው በጣም ብዙ የስነ ምልክት አርማና ወክልና ያያዙ ቅርሶች ይገኛሉ
አንዳንዶቹ ከሺ አመታት ቀደም ብለውም ቢሆኑም የታነጹት የእያንዳንዱን የቅርስ ውክልና እንዲሁም የህንጻ አሰራር ልዩ ጥበባዊ ሂሳብን እንደተጠቀሙ አይቶ ለመረዳት አያዳግትም።
አንዳንድ ልኬቶች ውስብስብ ቢመስሉም በተፈጥሮ ውስጥ ያላቸው መሰረታዊ ሚና ስናይ እውነትም መለኮታዊ ምጣኔ ነው የሚያስብሉ እውነቶች አሉ።
በእያንዳንዱ የተፈጥሮ ስሪት ውስጥ ይህ አስገራሚ ኮድ ይገኛል። ከተክሎች እስከ ነፍሳት ፣ ከፀሐይ እስከ ጨረቃ፣በስነ ህንጻ መዋቅራዊ ስሪት እንዲሁም የሰው ልጅ የሰወነት ክፍሎች ልኬታ ጭምር የዚህ ሂሳባዊ ቀመር ውጤት ናቸው ። ይህ የዩኒቨርስ ቀመር ምንድነዉ?
ወርቃማው ቁጥር በሚያስደንቁ ሁኔታ በየትኛውም ተፍጥሮአዊ ሆነ ሰው ሰራች ነገሮች ሁሉ መገኘቱ አጋጣሚ አይደለም ።
እያንዳንዷ የተፈጥሮ አካል በዘፈቀደ የተደረደሩ ሳይሆን እጂግ በሚያስገርም መለኮታዊ ምጣኔ የተለኩ መሆናቸው ነው።
አንዳንዶቹ ይህ ወርቃማ ቁጥር አለም በሙሉ ከ ግዑዝ አካላት እስከ ታላላቅ ፕላኔቶች ጭምር ቁጥራዊ ውክልናን ይይዛል ይላሉ።
ወርቃማዉ ንፅፅር ወይም Golden ratio የሚወክለው በ 1.618 ሲሆን እንጂግ በሚደንቅ ሁኔታ ይህ ቁጥር በእኛ በቀደምት አባቶቻችን ስራወቻቸው ላይ ሁሉ መጠቀማቸው ነው። ይህ ቁጥር መሰረት አድርገው የተቀመሩ በርካታ የጥንት ቅርሶቻችንን ስንመለከት እጂግ ያስደንቃል።
ይህ ቁጥር ከሁሉም የስነ ተፈጥሮ ክስተቶቻችን ጋር እጂግ በሚገርም ቅንጂት ተሳስሮ ይገኛል።
ለምሳሌ በስነ ህይወት ወይንም በbiology ዘርፍ በአንድ የንብ መንጋ ውስጥ ስላለው ግንኙነት ብንመለከት እጂግ ይደንቃል። በየትኛውም ዓለም የንብ ቀፎወች ውስጥ የሚገኝ የአንስት ንቦች ቁጥርን ለተባታይ ብናካፍል ተመሳሳይ ቁጥር እናገኛለን ይህም 1.618 ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን በእጽዋቶች ካለው ቀጥተኛ ግኑኙነት አንጻር ይህን ቀመር እናገኛለን።
ለምሳሌ የአንድ የሱፍ አበባ ዘሮች በተቃራኒ አቅጣጫ ነው የሚበቅሉት ቀለበት እየሰራ የሚወጣው አካላቸው የእያንዳንዱን ዙር ዲያሜትር ቀጥሎ ካለው ጋር ሲካፈል ውጤቱ 1.618 ይሆናል።
ጽጌረዳወች አበባወች ሰብሎች ጠመዝማዛ ጥዶች የነፍሳት አጹቆች ሁሉ ከዚህ ቁጥር ካር ግኑኙነት አላቸው።
ይህ አጀብ የሚያስብል ጉድ ነዉ!
ከሰው ልጅ ተክለ ሰውነት ጋርም እጂግ በሚገርም ሁኔታ ይህንን ምጣኔ እናገኘዋለን።
ከራስ ጸጉረችን እስከ እግር ጠፍራችን ያለውን ቁመት እንለካ እና ከዚያም ከወገባችን እስከ እግር ጠፍራችን ባላው ቁመት እናካፍለው የሁሉም የሰው ዘሮች የሚሰጠን ቁጥር 1.618 የተባለውን አስደናቁ ቁጥር ነው።
ይህ ብቻ አይደለም ከትክሻችን እስከ እጂ እጣታችን ጫፍ ያለውን ርዝመት ከክርናችን እስከ ጣቶቻችን ጫፍ ብናካፍለው የሁላችንም የሚሰጠን 1.618 ን ነው።
ሌላው ከወገባችን ዘቅ ብሎ ካለው መገታጠሚያ እስከ ከ ራስ ቅሎቻችን እግር ጫፍ ያሉ መገጣጠሚያወች በሙሉ የእጂ እና የእግር ጣት መገጣጠሚያወቻችን ጭምሮ በርካታ ውስጣዊ ስርአቶቻችን በዚሁ ሚስጥራዊ ቀመር የተቀመሩ ድንቅ ተፍጥሮ ናቸው።
የጥንት የሜሶፖታምያ አሻራወች ፣የታላቋ ባቢሎን ግንብ እንዲሁም የተለያዩ ዘመን ላይ የታነጹ ድንቅ አርማና ምልክቶች የያዙ ህንጻወች መካነ መቃብሮች የግብፅና የተሰወሩ የኢትዮጵያ ፒራሚዶች እንዲሁም አለም ላይ አሉ የተባሉ ንድፎች የዚህው ታምራዊ ቁጥር አሻራወች ናቸው። የዜማ ልኬቶች ቅንብሮች ጭምር የሞናሊሳ ስዕል ሳይቀር የዚሁ ውጤት ናቸው።
ይህ ወርቃማ ቁጥር ያልሰፈረበት ቦታ የለም።
መለኮታዊ ምጣኔ ወርቃማው አማካኝ በሁሉም ቦታ ይገኛል ከዛፍ ላይ ካሉ ቅጠሎች እስከ ባህር ውስጥ ቅሪቶች ድረስ ማለት ነው።
ሚስጥሩ ያልተፈታው ታላቁ የ ላሊበላ ህንፃም እጂግ በሚደንቅ ሁኔታ ቤተ መቅደሶቹ በዚሁ ታምራዊ የቁጥር ቀመር መገንባታቸዉን ስንመለከት እጂግ አስደናቂ ነው።
ሀሳባችዉን ግሩፓችን ላይ ፃፉልኝ ! እረ ደግሞ like እያደረጋቹ አትሰስቱ በዩቲዩብ እና ቲክቶክ ይከተሉኝ
ዩቲዩብ
https://www.youtube.com/channel/UCrMFcUoB8vPhFfmd_XH-ehg?sub_confirmation=1
ቲክቶክ
https://www.tiktok.com/@sirnhatty
creator
@sirnhatty
652 viewsIt's Me, 07:06