Get Mystery Box with random crypto!

አንድሮሜዳ🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ androethiop — አንድሮሜዳ🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ androethiop — አንድሮሜዳ🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @androethiop
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.25K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል ዘመናዊ ASTRONOMI ከ ጥንታዊ ስነ ፈለክ ጥበብ አጣምሮ የያዘ ፣ ስለ ሰማዩ ምስጢር የሚዳስሱ መጸሐፍትን ከአቡሻህር እስከ universe books እንዲሁም ከምድር እስከ ጠፈር ፣ከሜርኩሪ እስከ ዩራኖስ፣ከፕሮክሲማ ሴንታወሪ እስከ ቪዋይ ካኒስ ማጆሪስ ፣ከ ሰለጠኑ ፍጡራን አስከ UFO ፣ከብላክ ሆል እስከ ዋይት ሆል... ማወቅና ማግኘት ለሚሻ እንሆ..
#አንድሮሜዳ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 20:34:39 ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የቻናሌ ቤተሰቦች ኢንትራንስ ለይ የሚመጡ ትምህርቶችን የአፈታተን ስልት ለዛሬ እናቀርብላችዋለን የተዘጋጀው aptitude ነው!!!! SHARE ያደረጋችውት አየታየ እንቀጥላለን

እንዴት የAptitude ትምህርት ፈተና መዘጋጀት እንችላለን!

English Part

የ Synonyms &Antonyms ጥያቄዎችን በLogic መልስ የምናገኝበት ዘዴ ።

Synonymous ከ (2-4) ጥያቄ ይመጣል!መልሱን ለማግኘት መጠቀም ያለብን ዘዴዎች

ምርጫውን ከማየታችሁ በፊት ተራ ቀጥሩ ላይ ያለውን ፤ ቃል በሚገባ ተረዱ። ትርጉሙን ካወቃችሁት እሰየው።ካላወቃችሁት ግን ቢያንስ Negative ነው Positive ነው የሚለውን ለዩ።

ቃሉ Positive ከሆነ ምርጫ ውስጥ Positive የሆኑ ቃላትን ፈልጉ ፤ ቢበዛ ከሶስት አይበልጡም!
¤ሶስት ቃል ከሆኑ አንዱ ቃል Negative ቢሆን እንኳን በፍፁም ከዋና ቃሉ ጋር ካልተጣጣመ አስወግዱት።ከሁለቱ አንዱን ምረጡ!
¤ ቃሉ Positive ሆኖ ምርጫ ውስጥ Positive ቃል አንድ ብቻ ከሆነ ትርጉሙን ባታውቁ እራሱ መልሱ የቃል ነው።

Antonyms ከ (2-4) ጥያቄ ይመጣል!መልሱን ለማግኘት መጠቀም ያለብን ዘዴዎች


ምርጫውን ከማየታችሁ በፊት ተራ ቀጥሩ ላይ ያለውን ፤ ቃል በሚገባ ተረዱ። ትርጉሙን ካወቃችሁት እሰየው።ካላወቃችሁት ግን ቢያንስ Negative ነው Positive ነው የሚለውን ለዩ።

ቃሉ Positive ከሆነ ምርጫ ውስጥ Negative የሆኑ ቃላትን ፈልጉ ፤ ቢበዛ ከሁለት አይበልጡም!
አሁን ልዩነቱን በማጥበብ ከሁለቱ Negative ቃላት አንዱን መረጡ
ተራ ቁጥር ላይ ያለው ቃል Positive ሆኖ ምርጫው ላይ አንድ Negative ቃል የሚገኝበት አጋጣሚም አለ ።ያኔ ያንን ምርጫ አጥቁሩ

Analogy ጥያቄዎች ከ 5-10 ግያቄዎች ይመጣሉ። ትርጉማቸውን የማናውቃቸው ቃላቶች Aptitude ላይ አይጠፉም ፤ መልሳቸውን የምናቅበት ድንቅ ሚስጥር ፤

Analogy ጥያቄዎች ስትሰሩ ተረጋጉና የቃላቶቹን ግንኙነት ተገንዘቡ። ተራ ቁጥር ላይ ያሉት ሁለት ቃላት በመሃከላቸው በምን ግንኙነት አለ?

Positive : Negative
Negative : Negative
Positive : Positive
ሰሪ : የመስሪያ ዕቃ
ሴት ፆታ : ወንድ ፆታ
ብዙ : ነጠላ
ወዳጅ : ጠላት

ተማሪዎች ብዙ ጊዜ Analogy ጥያቄ ሲመልሱ የሚፈጥሩት ስህተት ፦

Now try This one.
Teacher : Chalk

A. Carpenter : Hammer
B. Dentist : Colgate
C. Singer : tone
D. Student : Pen

የቱን ሞላችሁ?
Answer : D

ኛ ስህተት : *Specific ልዩነቱን ባለመለየት ፤ መልስ ለመሙላት ይቸኩላሉ! ለምን ''A ''አልሆነም? ምክንያቱም ከትምረህርት ጋር ግንኙነት ስለሌለው ፤ Choice D ባይኖር ኖሮ ግን መልሱ 'A' ይሆን ነበር

Now try This one.

VERSE : POEM

A. SPEECH : PITCH
B. PARAGRAPH : SENTENCE
C. ATOM : MOLECULES
D. LEXI : LUXURY

የቱን ሞላችሁ?
ANSWER : C

ኛ ስህተት : *ቅድመ ተከተሉን በደምብ አያስተውሉም። ለምን መልሱ ''B ''አልሆነም?
ጥያቄው የሚለውን በደምብ እናስተውል ፤ ስንኞች ተደምረው ግጥም ተሰጡ ፤ እንዴት አንቀፅ ተደምሮ አረፍተ ነገር ይሰጣል( ውድቅ ሆነ ምክንያቱም Inverse relationship order ስላለው)

Analytical reasoning ፤ የምንረዳበት መንገዶች።

አንዳንድ Logic ጥያቄዎች ስንጠየቅ ምን ማድረግ አለብን ፦

የሰጠንን መረጃ በደምብ መረዳት ከዛን ጥያቄው ወደሚመራን Logicኩን መከተል።ለምሳሌ

Helen ,Who is my mere sister, has, is a nice of Kidist.

If the above logic is true .Which of the following is true .
i. I have two Children.
ii. I am a nephew of kidist.
iii. Kidist as an ant called Helen

A. i,ii
B, i
C.iii
D. i,ii, iii


Answer : C

Logical reasoning ለመረዳት ከባድ እና ለመረዳቴ ጊዜ ሚወስድ ከሆነ ! ፤ ስዕል ወይም ዲያግራም ማስራት የሚጠይቅ ከሆነ ማዘጋጀት።

ለምሳሌ የለኛው የዝምድና አይነት ጥያቄ ቢመጣ ፤ የቤተሰብ ዘር ቅርጫፍ በመስራት ወዲያው መረዳት ይቻላል


Maths Part (25)
Maths part ምንም ያክል ቀላል ቢመስልም ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል

SHARE ያደረጋችውት አየታየ ሌሎች ትምህርቶችን እንቀጥላለን እያንዳንዳችሁ ለምትወዱት ተማሪዎች SHARE አድርጉ!!!


join our exam chanel
@englishethiop
@englishethiop
CONTACT US
@androethiop
90 viewsAbel , 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:47:16
እንኳን ደስ አለዎት

ሳፋሪኮም ቦነስ በኢትዮጵያ ያለውን ተደራሽነት ለማስፋት ያዘጋጀውን 2,500 ብር የሚያሸልም ቀላል ውድድር እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል

እንዴት ነው #መሳተፍ የምችለው?


1/ በመጀመሪያ ይሄን ሊንክ ተጭነው ቡቱን start ብለው ያስጀምሩ
https://t.me/Safaricom_bonus_bot?start=r0237120528

2/ በመቀጠል ' ሰው ለመጋበዝ ' የሚለውን MENU ይጫኑ።

3/ ከዚያም ለእርሶ የሚላክሎትን የራሶ መለያ ሊንክ ለሌሎች #ሼር ( #Forward ) በማድረግ ይጋብዙ።

4/ ሰዎች የእርስዎን ሊንክ ተጭነው ቦቱን ሲቀላቀሉ መልዕክት ይደርስዎታል።

5/ በእርስዎ ግብዣ አማካኝነት የተቀላቀሉ ሰዎች ቁጥር 30 ሲደርስ የባንክ ሂሳብ ቁጥርና ስልክዎን ይላኩልን። ወዲያውኑ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ 1500ብር ከተሰጦት 1000ብር ቦነስ ጋር ገቢ ይደረግሎታል።


የአሸናፊ ተሸላሚዎችን ዝርዝር ለማየት ሊንኩን በመጫን በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ።
https://t.me/+4vLmhNqxznYwNDA0

መልካም እድል
239 viewsAbel , 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 14:47:16 እቺ ነገር የምር ትሰራለች ቤተሰቦች ተጠቀሙባት ቢያንስ ለካርድ ትሆናለች
180 viewsAbel , 11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:24:00 SOCIAL MEDIAን እንዴት ብንጠቀም ነው በትምህርታችን ውጤታማ የምንሆነው?

በዚህ አሁን ባለንበት በዲጂታል አለም ውስጥ ኑሯችን Social media እንድንጠቀም ያስገድደናል!

ጥያቄው

አሪፍ የትምህርት ብቃት ለማግኘት ''እንዴት Social mediaን ልተው?'' ሳይሆን ''እንዴት Social mediaን ልጠቀም '' የሚለው ተመራጭ ጥያቄ ነው ?መልካም ወደ መልሱ እንሂዳ ፦

ሊበልጥ ሊጠቅሟችሁ የሚችሉ ማህበራዊ mediaዎችን ውስጥ ሁለቱን ምረጡ!

ለምሳሌ እኔ ፦
Fb አልጠቀመም (Uninstalled )
ቅድም ባልኳችሁ ምክንያት

እናንተም አይጠቅማችሁም ....ዘመድ ምናምን ሊኖር ይችላል የምታወሩት...ግን ወደፊት ስራ ስትይዙ ትጠያየቃላችሁ...ወደፊት ስራ ስትይዙ...ታገባላችሁ ( ያኔ የትዳር አጋራችሁን መጀላጀል ...sorry መጀናጀን ማለቴ ነው!



SKYPE አልጠቀምም (Uninstalled )

ከየትኛው ሴናተሮች ጋር video conference ላረግ ነው?

imo አልጠቀምም (Uninstalled )

ከየትኛው ቤተሰቤ ጋር Video call ላወራ!እኔም እንደናንተ ውጪ ሃገር አጎቴ አለ ግን አያስፈልግም ዝም ብሎ መቀናጣት ነው!

Instagram አልጠቀምም (Uninstalled )
በወጣሁ በገባሁ ቁጥር follow ሳላረጋቸው የአመለሴት ሙጬን ፣ የዳናዊት መክበብን ፎቶዎች ነው የሚያሳየኝ እኔ IG ብጠቀም ምንም ምጠቀመው ነገር የለም የ celebrity ፎቶ ከማየት በቀር!

አናንተ ግን ሴቶች በተለይ አሪፍ አቋቁም እና ቁንጅና ካላችሁ ተጠቀሙ ከትምህርት ጎን ለጎን አሪፍ ስራ ትሰሩበታላችሁ
e.g - ለሞዴልነት ትመረጣላችሁ
- ማስታወቂያ ትሰራላችሁ ( ልክ ማስተዋል ወንድ ወሰን እንደምትሰራው አይነት የfashion ,የ Cosmetics ማስታወቂያዎች ማለት ነው!
- Celebrity ትሆናላችሁ

አስተውሉ * : ተከታይ ለማግኘት ትምሮሽን ብትረሺ እኔ የለሁበትም!...

Telegram እጠቀማለሁ (installed )
እኔ በቴሌግራም ብዙ የምሰራቸው ስራዎች አሉኝ

ቻናል ገዛለው ፤ ሸጣለው ደልላለው ፤ማስታወቂያ ሰራለሁ!

እንዲሁም ያለ ምንም እንጊሊዘኛ በቀላሉ እንማር ላይ therapy ሰጣለሁ! ከናንተው ከቤተሰቦቼ ጋር አብሬ እለወጣለሁ!
እናንተም Telegram ለመጠቀም ብዙ ምክንያቶች ይኖራችኋል መቼም ፦
ከሌሎቹ Social Media platform በተሻለ አስተማሪ ነገሮችን ታገኙበታላችሁ
ማየት እና ማውራት የምትፈልጉትን ነው የምታወሩት( እንደ Fb,IG ,Tiktok አንዳንድ አስጠሊታ post እየመጡ አየረብሿችሁም )


Tiktok እጠቀማለሁ (installed )
ይህን platform ደግሞ የመረጥኩት ለ Manyazewal Eshetu እና ለ Inspire Ethiopia ስል ነው
PRANK VIDEOS አላይም
MUSICAL.LY (i.e እንደነ Yuti_nas* ሃያት ናስር ) ያሉትንም አላይም!
ምክንያቱም እንዲህ አይነት vIDS ሳይ አቋርጥ አቋርጥ አይለኝም ...ሶ እንዳይደርስብኝ አልደርስበትም
INTERNATIONAL PUBLIC SPEAKER' አያለሁ
የራሴን Motivational Therapy እለቃለሁ

ይሄም Instagram ላይ እንዳልኩት ይበልጥ ጠቀሜታ አለው! በራስ መተማመናችሁን ታሳድጉታላችሁ ፣ celebrity ትሆናላችሁ ፤ ልክ እንደነ Manyazewal ሰዎችን ትረዳላችሁ ፤ ገንዘብ ከፈለጋችሁም ታትሙበታላችሁ

YOU TUBE አልጠቀምም(Installed cause its system app)
You tube ከሚጠቅመኝ የሚጎዳኝ ይበልጣል!

Motivational video ,ስብከት ስፈልግ በወር አንዴ ገብቼ አውርጄ ወጣለሁ!
በተረፈ Movie ,music ምናምን የጊዜ ጠር ናቸው

ሌላም ሊኖር ይችላል ምትጠቀሙት Google +, RapChat , Snapchat ,line, WhatsApp ,viber, ...ብዙ ብዙ ብቻ እናንተ ሁለቱን ምረጡ


anyways እኔ ሁለት Social media መረጥኩ (Telegram እና Tik tok ) እናንተስ?

ከሁለቱ Plat from አንዱን favorite አርጉናችሁ በየቀኑ፤ ሌላውን ደግሞ በሶስት ቀን interval መጠቀም!

ለምሳሌ ||እኔ Telegram በየቀኑ እጠቀማለሁ....Tik tok ደግሞ አልፎ አልፎ ...አሁን የምትጠቀሟቸውን ሁለት App ከለያችሁ እንዴት መጠቀም እንዳለብን እንመልከት

SOCIAL MEDIA እንዴት እንጠቀም?

ቀን ተጠቀሙ እንጂ ፣ ማታ ማታ መጠቀማችሁን አቁሙ!

ጥናቴች እንደሚያሳዩት ከሆነ ብዙዎች Screen ላይ ሲያፈጡ ያመሹና እንቅልፍ ቶሎ አይዛቸውም! ስለሆነም ይተው ስለሆነ የሚያሸልቡት ጠዋት አርፍደው ይነሳሉ!
አንድ ተማሪ ቢያንስ ለሊት 11:00 ሰዓት ተነስቶ ካላነበበ ምኑን ተማሪ ነው?

እስካሁን የገደልነው ጊዜ ይበቃል! ማታ ማታ Online መሆናችሁን አቁሙ!

ካነበባችሁ በኋላ Online ግቡ

ከንባብ በፊት ከጀመራችሁ ጊዜያችሁን ይጋፋባችኋል So ከንባብ በኋላ!

አስተወሉ* ከምሳ በኋላ ሆዳችሁ እስኪፍታታ ባለው ጊዜ ፤ አልያም ጥናት ጨርሳችሁ ራት እስክትበሉ ባለው ጊዜ ብትጠቀሙ ከልላው ጊዜ ይበልጥ ተመራጭ ነው!

ትምህርታዊ contentዎችን በተቻለ መነገድ ምረጡ እና ተከተሉ
E.g Educational Group ,Educational Channels , Religional channels

ተቃራኒ ፆታን አታሳድዱ ፤ ያላችሁ ጓደኞች ይበቃችኋል!....ይህ መንገድ ጊዜ በጣም ይወስድባችኋል

....በየጊዜው ጓደኛ የምትቀያይሩ ከሆነ እውነትም ሱስ ውስጥ ገብታችኋል...ሱስ ውስጥ ከገባችሁ ደግሞ በቃ ማንነታችሁን ይቀይረዋል..

ከዚች ጋር አንድ ሳምንት ታወራለህ ፤ ይሰለችኋል ፣ ሌላ ሴት ትቀይራለህ ፤ ሞቅ ያለ ሙድ ውስጥ ተገባላችሁ ቢሆንም ለአንድ ሳምንት ነው... ከዛን ታስጠላሃለች( Fb በምጠቀምበት ጊዜ እንደሆንኩት አይነት ነው ፣ ሲበዛ ጥቅም አልባ ነገር ሴት ሴት እየተከተሉ እራስን ማስረከስ ).... ለሴቶችም ነው ይሄን ያልኩት ወንድ ወንድ እየተከተሉ እራስን ማስረከስ )

የተቃራኒ ፆታ ፍላጎት አላችሁ ይገባኛል ግን በመጠኑ አርጉት ጓደኛ ቀንሱ!ቢያንስ ከአንድ ወንድ ጋር ተጀናጀኝ ብትችይ ለመተው ሞክሪ

ሴቶች አነፍንፈው እንዲያወሩህ ከፈለክ :-
''Dear boys don't follow girls .Follow your dreams ,then girls will follow you''

ድሮ አልዋሽም እንዳልኳችሁ ነው ሴቶችን አሳድድ ነበር ግን ተውኩት ዛሬ ቴሌግራም ላይ Data ሳበራ ያልተነበቡ ብዙ messages ከወንዶችም ከሴቶችም ይደርሱኛል!እኔ ደግሞ አያስችለኝም ሲጀነጅኑኝ ግፍ ይሆናል እያልኩ በቃ

ቋሚ የጥናት Program አዘጋጁ እና እንደመዝናኛ -Social ሚዲያዎችን አካቱ!
በዛች interval ብትጠቀሙ ታተርፋላችሁ!


ይቀጥላል ...

SHARE በማድረግ የነቃ ቤተሰብ እንፍጠር


@androethiop
@androethiop
▬▬▬▬▬▬▬▬
106 viewsAbel , edited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:00:36 ጅንጀና ስለ ፋርማሲ

በ Andromeda English Channel ( From AAU ) ተዘጋጅቶ የቀረበ።

ፋርማሲ ከ other health ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ የትምህርት ስርአት freshman course ጨምሮ የ5 አመት ትምህርት ነው ።

ፋርማሲ ስትገቡ የምትማሯቸው ኮርሶች mostly chemistry ነክ around [ 60%] ,biological around [25%] እና ሌሎችም አሉ ።ስለዚህ chemistry የሚወድና አንባቢ ተማሪ በብቃት ይወጣዋል።

ፋርማሲ ስትማሩ የሚያስደስቱ ነገሮች ፦

የመድሃኒት ቅመማ በላብላቶሪ ትሰራላችሁ ፤

ከባህላዊ ህክምናና ከእፅዋት እንዴት መድሃኒት ማግኘት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ ፤

በላብላቶሪ ውስጥ lotion, cream, gel, shampoo, sanitaizer....የመሳሰሉትን ኮስሞቲክስ ታመርታላችሁ ፤መድሃኒትን አይጥ ላይ በመውጋት ትመራመራላችሁ ወዘተ....

በፋርማሲ ስትመረቁ ምን ትሰራላችሁ? ገቢውስ እንዴት ነው ?

1, clinical pharmacy የሚባለው እ hospital ውስጥ ተቀጥራችሁ::

2, pharmaceutical company የመድሃኒት ፋብሪካና በተወሰነ መልኩ የኮስሞቲክስ ፋብሪካ ጋር::

3, የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ማለትም ወደ ሀገር የሚገቡና የሚወጡትን መፈተሽ::

4, በግላችሁ community pharmacy በመክፈት በተለይ ቤተሰቦቻችሁ በገንዘብ የሚያግዟችሁ ከሆነ በጣም አዋጭ ነው።

5, የማንኛውንም የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁስ በ pharmacist ቁጥጥር ስር ነው የሚገዛው (የሚቀርበው) ስለዚህ እዛ ላይም የናንተ ሙያ አለ።

6, የ fingerprint,forensics, food toxicity,drug toxicity,.....የመሳሰሉትን የወንጀል ምርመራ ላይ መስራት ይቻላል ።

7, እኛ ሀገር ብዙም ባይኖር የመድሃኒት ጥናትና ምርምር ላይም ትሰራላችሁ::

ስለ ገቢው፦ እውነቱን ለመናገር በፋርማሲ ትምህርት ከተመረቃችሁ በኋላ ስለ ገንዘብ አያሳስባችሁም ። እያጋነንኩ አይደለም ከቻላችሁበት በጣም ባለሀብት ትሆናላችሁ ። ስለ ፋርማሲ ብትጠይቁ ቀድመው የሚነግሯችሁ businesses ነውና እሱ አያሳስባችሁ ።

ስራ ላላገኝ እችላለሁ? እንደማንኛውም የጤና ተማሪ ከhospital,ጤና ጣቢያ ትሰራላችሁ plus ሌላ አማራጭ በግል ትሰራላችሁ ወይም ከላይ ከ ተራ ቁጥር 2-7 ያሉት አማራጮች አሉላችሁ ።

ትምህርቱ ከባድ ወይስ ቀላል? pharmacy ከ medicine በመቀጠል የሚመደብ ስለሆነ ከበድ ይላል ነገር ግን chemistry,biology and labolatory ነክ ትምህርቶች ለሚሰራና ለሚያነብ ተማሪ በቀላሉ ማለፍ ይችላል ። እንደዬ ዩንቨርስቲው ቀለል ባለ መልኩ የሚያስተምሩም አሉ ። ስለዚህ ጠንከር ያለ ተማሪ ቢሆን የተሻለ ውጤት ያመጣል።

በአጠቃላይ ፋርማሲ ከሌሎች የጤና ዘርፎች ለየት የሚያደርገው ብዙ የስራ መስኮች ያሉትና ጥሩ የሚባል ክፍያ የሚገኝበት መሆኑ ነው።

ስለ ፊልድ መረጣ በተመለከተ እንደ medicine ገና የመጀመሪያ ሴሜስተር ኮርስ እንደጨረሳችሁ ነው ። ሌሎች other health ግን 1ኛ አመት ከጨረሳችሁ በኋላ ነው።

Is it your dream ??
Yes
No



Everyone #Share to all friends
@androethiop
@androethiop
181 viewsAbel , 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:26:26 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።

ክፍል ሁለት

በ አንድሮሜዳ @andeoethiop ተፃፈ።

Worksheet

Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡ ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።

የአጠናን መንገድ(ስልት)

እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው ?

አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ

የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም ።

ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

የጊዜ አጠቃቀም

ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

አለመሰልቸት

ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

Google

ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ ።

The End

Join and share

@androethiop
@androethiop
223 viewsAbel , 14:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:23:12 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን ።

በ አንድሮሜዳ ተዘጋጅቶ የቀረበ።


1ኛ) ማንበብ + መረጃ

ግቢ የቱንም ያህል ብታነብ ፡ ላይብረሪ ውስጥ ብትውል ብታድር ፡ ሺህ መፅሀፎችን ብታነቢ መረጃ ከሌለሽ ልፋትሽ ከንቱ ነው ፡ በለፋህበት ልክ አትሰራም መረጃ ከሌለህ ። መረጃው ምን አይነት ይሆን ?

ለምሳሌ አንዳንድ ፈጣን ተማሪዎች በነሱ ዲፓርትመንት ውስጥ ያሉ ነባር ተማሪዎችን ( senior ) ይጠይቃሉ።

ለምሳሌ ነባር ተማሪዎች ያንን ኮርስ በሚወስዱበት ጊዜ ምን ምን መፅሀፍ ይጠቀሙ እንደነበር ፡ መምህራኖች ጥያቄ የሚያወጡበት መፅሀፍ ምን እንደነበር ይጠይቃሉ ፡ ከዛም መፅሀፋን ይቀበላሉ ። ስለዚህ እናንተ ተፍ ተፍ ማለት ፡ የ ክላሳችሁን መጠየቅ ፡ ምን መፅሀፍ እንደተቀበሉ ምን መፅሀፍ እንዳላቸው ፡ መጠየቅ ።

ሌላኛው ደግሞ መምህሩ ክላስ ውስጥ በሚያስተምርበት ሰአት ፡ ይኸን part በደምብ አንብቡ ፡ ይሄን ያዙ ምናምን እያለ ፈተና የሚወጣበትን part ሊጠቁም ይችላል። ክላስ ካልገባህ ወይ ደግሞ ክላስ ውስጥ የምንታቀላፊ ከሆነ ፡ ተበላሽ ። ስለዚህ ክላስ የገቡ ተማሪዎችን መምህሩ ምን ምን እንዳለ መጠየቅ ።

ሌላኛው ደግሞ Affirmative action ። ምን መሰላችሁ ፡ ለምሳሌ mid exam የሚወጣው chapter 1&2 ከሆነ ፡ መምህሩ 2 ቱን chapter አስተምሮ እንደጨረሰ ፡ ፈተናው 3 ወይም 4 ቀን ሲቀረው ለ ሴት ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ለፈተናው የሚጠቅም መምህሩ tutorial ይሰጣቸዋል። ፈተና የሚወጣበትን part ያስተምራቸዋል ፡ ከ ፈተናው ጋ ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ይሰራላቸዋል። ኸረ እንደውም አንዳንድ ጊዜ ፈተና ላይ የሚወጣውንም ጥያቄ ይሰራላቸዋል ። ስለዚህ የ ክላሳችሁን ሴት ተማሪዎች እንዳትፋቷቸው ። በ tutorial class መምህሩ ያፃፋቸውን ኖት ፡ ያሰራቸውን ጥያቄ በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ አንብቡ ።
አሁን ደግሞ

በ ግቢ ቆይታየ ከ መረጃ ጋ በተያያዘ ያጋጠመኝ አንድ ሁለት ገጠመኝ ላጫውታችሁ ።

" Mass and Heat transfer " የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና እኔ አንዳንድ ጊዜ ከነሸጠኝ ክላስ አልገባም ። ከዛ ክላስ ባልገባሁበት ሰአት ፡ መምህሩ አስተምሮ ፡ በ Cartesian and cylindrical የሚሰራ proof ነበር። በ Cartesian የሚሰራውን መምህሩ proof አደረገላቸው። በ cylindrical የሚሰራውን ደግሞ እናንተ proof አድርጉ አላቸው ። " አደራ አደራ እንዳትረሱት " አላቸው ። እኔ በወቅቱ ክላስ ስላልገባሁ መረጃው አልነበረኝም ። ይኸን የሰሙ ተማሪዎች ላይብረሪ ገብተው proof ፋን ሽምድድ።

ከዛ mid exam ስንፈተን በ cylindrical proof አድርጉ ያላቸውን 8 mark ይዞ መጣ ።
እኔ መረጃው ስላልነበረኝ ከ 8ቱ 0 አመጣሁ ። ከዛ ይኸን ኮርስ 77.5 (B+) አመጣሁ ከ 100%። ግን መረጃው ቢኖረኝ ወይም ክላስ ባልቀጣ proof ፋን እሰራው ነበር ።

77.5 + 8 = 85.5( A )

አያችሁ አይደል በዚች የመረጃ ክፍተት A የማመጣውን ኮርስ B+ አመጣሁ ።


ከመረጃ ጋር በተያያዘ ሌላ ገጠመኝ

"Probability and Statistics" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና በወቅቱ መምህሩ ፈተና የሚያወጣበት ፡ አሳይመንት የሚያወጣበት መፅሀፍ ነበር። እና እኔ ደግሞ በወቅቱ መረጃው አልነበረኝም መምህሩ ያን መፅሀፍ እንደሚጠቀም። ከዛ መምህሩ የሰጠንን handout ለ ፈተና አንብቤ ገባሁ። ግን መምህሩ ጥያቄውን ከዛ መፅሀፍ ስለነበር ያወጣው 5/10 አገኘሁ ። ያንን መፅሀፍ ያነበቡ ልጆች ግን ደፈኑት ። ከዛ ከፈተና በሗላ ስጠይቃቸው "እንትን" የሚባል አሪፍ መፅሀፍ አለ ከዛ ነው ያወጣው አሉኝ ። ከዛ ተቀበልኳቸው ። ከዛ ለ mid exam ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ሰራሁት ። ከዛ አሳይመንትም እንደዚሁ ከ መፅሀፉ ቁጥር እንኳን ሳይቀር አመጣው ፡ ከዛ እኛም ድፍን ። ምን ቀረ ? Final exam ። ለ final exam አሁንም ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ከዛ 'A' አመጣሁ ።

አያችሁ አይደል ያንን መፅሀፍ ባልቀበል ወይም ደግሞ መረጃው ባይኖረኝ ፡ handout ቱን ብቻ ነበር የማነበው ፡ A አላመጣም ነበር።

በ ነገራችን ላይ Chemical Engineering, Electrical and Computer engineering, civil engineering ምናምን የምትገቡ ልጆች " probability and statistics" ኮርስ ትወስዳላችሁ ። የ ግቢ መምህሮች አሁን ያልኳችሁን መፅሀፍ ፈተና ለማውጣት ፡የ አሳይመንት ጥያቄ ለማውጣት ፡ handout ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። ስለዚህ " probability and statistics" ኮርስ በምትወስዱበት ጊዜ ፡ በውስጥ መስመር አናግሩኝ እሰጣችሗለሁ።

የመጨረሻ ገጠመኝ ፡ አላብዛባችሁ ።

" Applied Electrochemistry" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና መምህሩ አሳይመንት አስቀድሞ ነበር የሰጠን። በቅፅል ስም " Smith " እያልን የምንጠራው ልጅ አለ ፡ መፅሀፍ በመጎርጎር 1ኛ ነው ። አመናችሁም አላመናችሁም መምህሮች የሚጠቀሙበትን እያንዳንዱን መፅሀፍ ያገኘዋል ። እንደውም ከመምህሮች በላይ መፅሀፍ የሚያውቅ ይመስለኛል ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Smith ያለኝን አድናቆት እና ምስጋና መግለፅ እወዳለሁ ። ብቻ ምን አለፋችሁ መምህሩ አሳይመንቱን ያወጣበትን መፅሀፍ አገኘው ። ከዛ መፅሀፋን ስናየው መምህሩ note የሚያወጣውም ከዛው መፅሀፍ ነው ፡ መረጃ ይልሀል ይኸ ነው ። እኛም አሳይመንቱን ድፍን ። ከዛ ለ mid exam ፈተና ያንን መፅሀፍ አንብበን ገባን። ከክላሱ ዝቅተኛ ውጤት የመጣው 24 ከ 30። መረጃ ይሉሻል ይኸ ነው ።

በዚሁ አጋጣሚ Chemistry ነክ የምትማሩ ልጆች ለምሳሌ Medicine, pharmacy, biomedical engineering, medical laboratory, Chemical engineering, biology, Chemistry.... የምትገቡ ልጆች Applied organic Chemistry, Analytical chemistry, inorganic chemistry, Applied Electrochemistry....ስለምትማሩ እንዲሁም የ natural science ተማሪዎች freshman course ላይ General Chemistry ስለምትማሩ አሁን የነገርኳችሁን መፅሀፍ ተጠቀሙ ። አሪፍ የሆኑ የ concept ኖቶችን ታገኛላችሁ ፡ አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ። በቃ Chemistry እንዲገባችሁ ከፈለጋችሁ መፅሀፋን ተጠቀሙበት።

የመፅሀፉ ስም
" University of Meinosota"

የመፅሀፋ መገኛ
Library ( natural library)

ሀሳቤን ስጠቀልለው ፡ ግቢ ላይ ማንበብ ብቻውን አይጠቅምም። መረጃ አነፍናፊ መሆን አለባችሁ። ስለ ፈተናው አወጣጥ ፡ ፈተናው ምን part ላይ አንደሚያተኩር ፡ ፈተናው ምን መፅሀፍ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ምናምን መረጃዎች ሾልከው ይወጣሉ ። ስለዚህ ከንባብ በተጨማሪ መረጃ ላይም አደራ ትኩረት አድርጉ።

ክፍል 1 አለቀ።
ክፍል 2 ይቀጥላል።

Join and share
@androethiop
195 viewsAbel , 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 17:19:23 #update

ሁለተኛ ዙር ውድድር


ከዛሬ ጀምሮ የ ግሩፑ member ብዛት 2000 እስከሚሆን ድረስ ሰዎችን add ያደረጉ 10 ሰዎችን እንሸልማለን
ሰዎችን አድድ ያደረጉ 10 ሰዎች አድድ ያደረጉትን ሰው ብዛት እየቆጠርን የምናሳውቅ ይሆናል ውድድሩ ተጀምሯል


.1only me... 87+28=115
2.Me D...90
3.Humood...86
4.eyob...6
5.Yonas.. 5
6.m.e.r.y....1
7.
8.
9.
10




2k አልገባንም ውድድሩ የሚያበቃው የmembers ብዛት 2k ሲሆን ነው።በርቱና add አድርጉ እኛም ከ 1-10 የወጡትን የምንሸልም ይሆናል ትምህርቱንም ማስተማራችንን እንቀጥላለን።
180 viewsAbel , 14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 21:29:41 ሰበር መረጃ

ሽራሮ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብታለች

ሠላምን ምረጥ ሲባል ውጊያን የመረጠው ህውሃት እየጨለመበት፣የትግራይ ህዝብ እየነጋለት ነው። ሽራሮ በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብታለች
በራያ ግንባር ለማመን የሚከብድ ጀብድ ተፈፅሟል።

@androethiop
@androethiop
272 viewsAbel , 18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:40:55 ወልድያ ላለ ጓደኛየ ደውየ ነበር ....

ሰኞ ፈተና ነበራቸው.... ዩኒቨርስቲው ምንም ነገር አላላቸውም ነበር ድንገት ዛሬ ነው ውጡ ያላቸው....12ስሀት እንደወጣ ቁርስ ሳይበላ አሁንም እየተጓዘ እንደሆነ ነገሮኛል...መኪና ሚባል ነገር እንደለለና ህውሃት ቆርጦ እንዳይገባ ስለተፈራ መንገዶች ላይ የ ፈዴራል ፖሊስ እንዳለ አድርሶኛል ።

ፈጣሪ ይጠብቃቸው ሌላ ምን ይባላል።

@androethiop
275 viewsAbel , 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ