2021-01-09 13:28:30
#ጌታችን #ኢየሱስ #ክርስቶስ #በታህሳሥ #ወር #አለመወለዱን #ያውቃሉ???
===============================
#መንፈሳዊ #ሰው #ግን #ሁሉን #ይመረምራል
1ቆሮ 2፡15
ዮሐንስ 8
32፤ እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል፡ አላቸው።
ቆላስይስ 2
16፤ እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ።
17፤ እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።
ኢሳይያስ 34
16፤ በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ አፌ አዝዞአልና፥
1) በእውነት ኢየሱስ ክርስቶስ በታህሳስ ወር ተወልዷልን???
2) የሚደረገው ስርዓትስ ከክርስትና ጋር ግንኙነት አለው??
3) የገና ዛፉስ ከየት መጣ???
4) መብራቱ እና አፉፋውስ ከየት መጣ???
5) ቅዱስ ኒቆላዎስ ( የገና አባት ) የተባሉትስ ከየት መጡ???
መንፈሳዊ ሰው ግን ሁሉን ይመረምራል 1ቆሮ 2:15
መፅሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደው በታህሳስ ወር እንዳልሆነ ይናገራል።
መፅሐፍ ቅዱስ ምን ይላል !!!
1ዜና 24፡7-19 ንጉሥ ዳዊት ካህናትን በተራቸው ወደ እግዚአብሔር መቅደስ ገብተው ያጥኑ ዘንድ መደባቸው 24 ካህናት ነበሩና በወር 2 ካህን ማለትም( ከ 1-15 እና ከ 16-30) በ 12 ወር 24 ካህናትን አደረገ ።
በእስራኤላዊያን ቀን አቆጣጠር መሰረት ደግሞ የመጀመሪያ ወራቸው ኒሳን (Nisan) ይባላል።
ዘፀ 12:1- አስቴር 3፡7 , 8፡9
የእስራኤል የመጀመሪያ ወር ኒሳን በኢትዮጵያውያን ቀን አቆጣጠር ሚያዚያ መሆኑ ነው።
፨ በምድቡም መሰረት
በአንደኛው ወር (ኒሳን)
ከ 1-15 ቀን== ዮአሪም
ከ 16-30 ቀን== ዮዳኤ
በሁለተኛው ወር (እያር)
ከ 1-15 ቀን==ካሪም
ከ 16-30 ቀን==ሥዖሪም
በሶስተኛው ወር (ሲቫን)
ከ 1-15 ቀን==መልክያ
ከ 16-30 ቀን==ሚያሚን
በአራተኛው ወር ( ታሙዝ)
ከ 1-15 ቀን== አቆስ
ከ 16-30 ቀን== አብያ
በሉቃስ ወንጌል 1፡5- 13 ከአብያ ቤተሰብ የሆነ በ 4ኛው ወር (ታሙዝ) የወሩ ሁለተኛ አጋማሽ ማለት ከ 16-30 ቀን በክፍሉ ተራ ለማጠን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ የገባ ስሙ ዘካርያስ የሚባል ሰው እናገኛለን ።
መቅደስ ውስጥ እያጠነ መልአኩ ገብርኤል ተገልጦ ልጅ እንደሚወልድ ይነግረዋል ከዚያም ዩሐንስ መጥምቁ ይፀነሳል ማርያም ደግሞ ከ 6 ወር በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን ትፀንሳለች።
መጥምቁ ዩሐንስ ኢየሱስን በ6 ወር ስለሚቀድመው በ 10ኛው ወር (#ቴቬት) ኢየሱስ ይፀነሳል
ቴቬት 10ኛ ወራቸው በኢትዮጵያ በታህሳሥ ወር ኢየሱስ ይፀነሳል ከታህሳሥ ጀምሮ 9 ወር ስንቆጥር መስከረም (ቴስር) መጨረሻ ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ ይወለዳል ።
ሉቃ 22:14-23, 1ቆሮ 11:23-25
ኢየሱስ ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ ተወዳጅ እና የከበረ የጌታ እራት ስነስርዓት እስክመጣ ሞቴን አስቡ በማለት ለቤተክርስቲያን ሰጥቷል ። እንጂ የትኛውም ቦታ ላይ ልደቴን በታህሳስ ወር መጨረሻ አስቡልኝ አላለም
መፅሐፍ ቅዱስ እንደዚህ የሚናገር ከሆነ የገና በዓል እየተባለ በታህሳስ ወር የሚከበረው ከየት መጣ ??
የገና በዓል በቅርብ የጀመረ ሳይሆን ክርስቶስ ከመወለዱ በፊትም በአህዛቦች ይከበር የነበረ ነው ከታህሣሥ 25 አስከ ጥር 1 ድረስ ይከበር ነበር ይህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌለው የአህዛብ በዓል
ክርስትና ከተጀመረ ከ 313 በኃላ ቤተክርስቲያን ነፃነቷን ስታገኝ አህዛብን ተከትሎ የገባ የአህዛብ በዓል ነው። አህዛቦች የብርሃን አምላካችን(በዐል የተባለው ጣኦት) የተወለደበት ብለው ጨለማው አለፈ የበጋው ብርሃን መጣ በማለት እሳትን እያነደዱ የለመለመ ዛፍን እየቆረጡ ያከብሩ ነበር። ይህ አህዛባዊ በዓል በቤተክርስቲያን ውስጥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተብሎ ተቀየረ ። ቆይቶም የካቶሊክ ቅዱስ የተባሉት ኒቆላዎስ የገና አባት ተብለው በየቤተክርስቲያኑ ውስጥ ተቀባይነት ካገኙ ዘመናትን አስቆጥረዋል ።
ቀኑ ወሩ አመቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ይህ በዓል ክርስቶስን የማያከብር ብዙ ቤተሰብ የሚበጠበጥበት የጌታችን ስም የማያከብር አለም የዳንኪራ ምሽት አዘጋጅታ ወጣቱን እና ባለትዳሩንም ሁሉ የምትጋብዝበት አጋንንታዊ በዓል ነው።
ክርስቶስን የማያከብረው አለም በስሙ የሚያሳምጽበት እውነት ይሄ በዓል የክርስቲያኖች ነውን???
ምሳሌ 30
5፤ የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች፤ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።
6፤ እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።
የገና በዓል እንዲህ ስር የሰደደ እና በብዙኀን ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም እውነት ሊሆን ግን አይችልም እውነቱ የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ብቻ ነው።
1 ዮሐንስ 5 ፡21፤ ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።
ይሁዳ 1፡17
እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
237 viewsNathnael M. Gawo, 10:28