Get Mystery Box with random crypto!

#ሩት የአህዛብ ሴት/ሞዓባዊት ሩት 1 (Ruth) 4፤ እነርሱም #ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት | Amna Tadesse Ministry

#ሩት

የአህዛብ ሴት/ሞዓባዊት

ሩት 1 (Ruth)
4፤ እነርሱም #ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስት አገቡ፤ የአንዲቱ ስም ዖርፋ የሁለተኛይቱም ስም #ሩት ነበረ። በዚያም አሥር ዓመት ያህል ተቀመጡ።

ሞዓብ ደግሞ ሎጥ ከመጀመሪያ ሴት ልጁ የወለደው

ዘፍጥረት 19 (Genesis)
36፤ የሎጥም ሁለቱ ሴቶች ልጆች ከአባታቸው ፀነሱ።
37፤ #ታላቂቱም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም #ሞዓብ ብላ ጠራችው፤ እርሱም እስከ ዛሬ #የሞዓባውያን አባት ነው።

ሞዓባዊያን የእስራኤልን መብዛትና ሰላማቸውን የማይፈልጉ ጠላቶች ናቸው ሰለዚህም #እርግማን ሊያደረጉባቸው ፈለጉ

ዘኍልቍ 22 (Numbers)
16-17፤ ወደ በለዓምም መጥተው፡— የሴፎር ልጅ ባላቅ፡— ክብርህን እጅግ ታላቅ አደርገዋለሁና፥ የተናገርኸውንም ሁሉ አደርግልሃለሁና እባክህ፥ ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ ምንም አይከልክልህ፤ እባክህ፥ ና፥ ይህን ሕዝብ #ርገምልኝ አለ፡ ብለው ነገሩት።

የተወዳዳችሁ ወንድሞቼ #ሩት አህዛብ ነች ይህ ብቻ አይደለም የምትኖረው በርግማን የሚታወቅ ንጉስ በሚገዛበት ከተማ ነው።

በአንድ አጋጣሚ ከይሁዳ ቤተልሔም ወጥተው ወደ ሞዓብ የሄዱ ቤተሰቦች ነበሩ

ሩት 1 (Ruth)
1፤ እንዲህም ሆነ፤ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር #በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ #ከቤተ ልሔም #ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።
2፤ የሰውዮውም ስም አቤሜሌክ፥ የሚስቱም ስም ኑኃሚን፥ የሁለቱም ልጆች ስም መሐሎንና ኬሌዎን ነበረ፤ #የቤተ ልሔም #ይሁዳም የኤፍራታ ሰዎች ነበሩ። ወደ #ሞዓብም ምድር መጡ በዚያም ተቀመጡ።

እነዚህ ቤተሰቦች ይኖሩበት የነበረው ከተማ የምስጋና/ይሁዳ እንዲሁም የእንጀራ ቤት/የሚበላ ያለበት/ቤቴልሔም ከተማ ውስጥ ነበር።

እንግዲህ ከምስጋናና ሁሉ ከሞላበት ከተማ ወጥተው ወደ እርግማን ከተማ ሞዓብ ሲሂዱ ያተረፉት ሞት ነበር።

ሩት 1 (Ruth)
3፤ የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ #ሞተ፤ እርስዋና ሁለቱ ልጆችዋ ቀሩ።
5፤ መሐሎንና ኬሌዎንም ሁለቱ #ሞቱ፤ ሴቲቱም ከሁለቱ ልጆችዋና ከባልዋ ተለይታ ቀረች።

የሩት መጽሐፍ ስናነብ ኑኃሚን እና ሩት ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሞዓብ ወደ ይሁዳ ቤተልሔም ለመምጣት ተነሱ ፤ ወዳጆቼ ወደ ቤቴልሔም ቢመጡ ኑኃሚን የቀድሞ ከተማዋ ነወ፣ቤተሰብ አላት፣ ረስት ነበራት ነገር ግን #ሩት ወገን አልነበረችም፣ ለእስራኤል ቤት የተሰጠው ተስፋ የላትም፣በእነርሱ ዘንድ ርስት የላትም ፣ለከተማው እንግዳ ነች/ባለገር አይደለችም

#ሩት በይሁዳ ርስትን ታገኝ ዘንድ ርስትን ሊሰጣት ፈቃደኛ የሚሆን ቤዛ/የሚቤዣት ያስፈልጋት ነበር ለዚህም ቦዔዝ ርስትን ይስጣት ዘንድ ሩት ሚስቱ አድርጎ ወሰዳት/ተቤⶳት።

አማኝ ልክ እንደ ሩት ነው።

ኤፌሶን 2 (Ephesians)
11፤ ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ #በሥጋ #አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤
12፤ በዚያ ዘመን #ከእስራኤል #መንግሥት #ርቃችሁ #ለተስፋውም #ቃል #ኪዳን #እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም #ተስፋን #አጥታችሁ #ከእግዚአብሔርም #ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።
13፤ #አሁን #ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።

ቆላስይስ 2 (Colossians)
13፤ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ።

ወንድሞች እኛ በክርስቶስ ቤዛነት ከእርግማን ወደ በረከት ከአንዳች ወደ ሙሉነት ከሞት ወደ ህይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን መለኮታው ልውውጥ ተደርጎልናል!!!

ጸጋ ይብዛላችሁ
ወንድማችው አምና ታደስ

https://t.me/joinchat/AAAAAE5Veg3GlEdndwaGyw