Get Mystery Box with random crypto!

2. ክርስቲያን በእግዚአብሔር የጸደቀ ነው:: ሮሜ 8 (Romans) 33፤ እግዚአብሔር የመረጣቸውን | Amna Tadesse Ministry

2. ክርስቲያን በእግዚአብሔር የጸደቀ ነው::
ሮሜ 8 (Romans)
33፤ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

መጽደቅ ይቅርታን ከመቀበል ይበልጣል::

ለአማኝ ጏጥያት የሚያሰከፈለወን መስዋት ሁሉ ኢየሱስ ከፍሏል::ኢየሱስ ሙሉን ክፈያ ስለከፈለ እግዚአብሔር የአማኙን ጏጢአት ይቅር ብሎታል ይህ ብቻ አይደለም አማኝ ሀጢአተኝነት እንዳይሰማው ጻድቅ አድርጎታል።

አማኝ የበደሉን ሰርየት አግኝቷል።
ኤፌሶን 1
7፤ በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።

የአማኙን የሀጢአት ደሞዝ ኢየሱስ በሞቱ ከፍሏል።
ሮሜ 6
23፤ የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።

አማኝ ስለ ጸደቀ ወደ ፍርድ በፍፁም አይመጣም።
ዮሐንስ 5
24፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።

አማኝ ወንድሜ ጻድቅ ነህ ማለት እግዚአብሔር ተቀብሎሀል ማለት ነው።እግዚአብሔር የተቀበለክ በልጁ ስራ ነው። አሁን እግዚአብሔር አንተን የሚያይ ልክ ከዚህ ቀደም ጏጢአት እንዳልሰራ አድርጎ ነው።


ጸጋ ይብዛላችሁ
ወንድማችሁ አምና

https://t.me/joinchat/AAAAAE5Veg3GlEdndwaGyw