Get Mystery Box with random crypto!

#ክርስቲያናዊ_ኑሮ የተወደዳችሁ ወንድሞች ከጌታ ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን አንድ ዳ | Amna Tadesse Ministry

#ክርስቲያናዊ_ኑሮ

የተወደዳችሁ ወንድሞች ከጌታ ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን

አንድ ዳግም የተወለደ ሰው ማወቅ ያለበትንና ዳግም በመወለዱ ያገኛቸውን የዳግም ልደት ውጤቶች አብረን እናያለን፦

1. የእግዚአብሔር ልጅ መሆን

ዮሐንስ 1 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተቀበሉትና በስሙ ላመኑት ሁሉ ግን የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው።
¹³ እነዚህም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፣ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

አማኝ ኢየሱስን በማመኑ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን መወቅ አለበት የእግዚአብሔር ልጅነት በዳግም ልደት የሚገኝ መለኮታዊ በረከት ነው።

እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን በተቀበለበት ልክ አማኙን ተቀብሏል።

እግዚአብሔር ኢየሱስን ሊጠላ ሰለማይችል ኢየሱስን በማመን ለራሱ ልጅ የሆኑትን አማኞችን በፍጹም አይጠላቸውም።

በኢየሱስ ያመነን አማኝ እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅሩ ይወደዋል።

አማኝ ወንድሜ እንኳን ደስ ያለክ አሁን አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ከእግዚአብሔር ጋር በክርስቶስ ደም ቤተሰብነትን ፈጥረሀል ልጅ ወዳለመሆን በፍጹም አትመለስም።

“በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤”
— ኤፌሶን 1፥5 (አዲሱ መ.ት)

ይቀጥላል.....

ጸጋ ይብዛላችሁ
እኔ ወንድማችሁ አምና ነኝ

ለሌሎች ሼር አድርጉት

https://t.me/joinchat/AAAAAE5Veg3GlEdndwaGyw