Get Mystery Box with random crypto!

ቆላስይስ 3 (አዲሱ መ.ት) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በ | Amna Tadesse Ministry

ቆላስይስ 3 (አዲሱ መ.ት)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ በተቀመጠበት በላይ ያሉ ነገሮችን እሹ፤
² አሳባችሁም በላይ ባለው ላይ እንጂ በምድራዊ ነገር ላይ አይሁን።
³ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰውሮአልና፤
⁴ ሕይወታችሁ የሆነው ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም በዚያን ጊዜ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።(አ.መ.ት)