Get Mystery Box with random crypto!

#ከባርነት_ወደ_ልጅነት “ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእና | Amna Tadesse Ministry

#ከባርነት_ወደ_ልጅነት


“ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
— ኤፌሶን 1፥2

በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የተደረገልንን የማንነት ለወጥ አብረን እንመለከታለን።

ወደ አማኝ ሆይ በክርስቶስ ኢየሱስ ስታምን የተደረገልህንና አሁን በክርስቶስ ያለህን ማንነትህን መረዳትን የመሰለ መታደል አለ በዬ አላምንም።በክርስቶስ ኢየሱስ የተደረገለትን የማንነት ለውጥ ያልተረዳ አማኝ ማንነትን ባለማወቅ ቀውስ ውስጥ ያለ ምስኪን እርሱ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳችን በክርስቶስ ሰለተደረገልን አዲሱ መንነታችን እነደዚህ ይለናል

ገላትያ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
1“ነገር ግን እላለሁ፥ ወራሹ ሕፃን ሆኖ ባለበት ዘመን ሁሉ፥ ምንም የሁሉ ጌታ ቢሆን ከቶ ከባሪያ አይለይም፥”
² ነገር ግን አባቱ እስከ ቀጠረለት ቀን ድረስ ከጠባቂዎችና ከመጋቢዎች በታች ነው።
³ እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን #ከዓለም #መጀመሪያ #ትምህርት #በታች #ተገዝተን #ባሪያዎች #ነበርን፤
⁴ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤
⁵ #እንደ #ልጆች #እንሆን #ዘንድ፥ #ከሕግ #በታች #ያሉትን #ይዋጅ #ዘንድ።
⁶ ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።
⁷ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

አማኝ ወንድሜ አሰቀደመህ አንተ ለመጀመሪያው ትምህርት (ለህግ) ባሪያ ሆነ ከእግዚአብሔር የአባትነት አቅርቦት እረቀ እግዚአብሔርን አባቴ ብለ የመጥራት ደፈረት የሌለ ነበረህ፤

አሁን ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከህግ በታች ሆኖ ከሴት ተወለደ ይህም የመሆኑ ምከንያት እንደ ባሪያ ሳይሆን እንደ ልጅ ትሆን ዘንድ ነው።


አሁን እግዚአብሔርን አባ ብለ የመጥረት ደፍረት ተሰቶሃል በፍጹም ልብህ እንዳይፈራ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ ይላልና

“አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት #የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና።”
— ሮሜ 8፥15

ይህ ቃል የታመነ ነው እግዚአብሔር አባታችን ነው እኛም ደግሞ ልጆቹ ነን በክርስቶስ ኢየሱስ መንፈስ ከሆነው አባታችን ተወልደናል፤በአባታችን ውስጥ ያለው የህይወት ስርዓት በእኛም ውስጥ አለ ።
ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤
¹³ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።

“ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።”
— ዮሐንስ 3፥6

ወንድሜ የእግዚአብሔር ልጅ መሆንህን በድፍረት ተናገረው ምክንያቱም እውነተኛ ማንነትህ ሰለሆነ።

የእግዚአብሔር ልጅ ሰለሆነህ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።

“ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ልጅ ነህ እንጂ ባሪያ አይደለህም፤ ልጅም ከሆንህ ደግሞ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ወራሽ ነህ።”
— ገላትያ 4፥7

“ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፥ አብረንም ደግሞ እንድንከበር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”
— ሮሜ 8፥17

ከእግዚአብሔር የተወለደ ወደ አለመወለድ አይመለስም እግዚአብሔር ዘለዓለማዊና የማይጠፋ ስለሆነ ከእግዚአብሔር የተወለደም አይጠፋም ።

“በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥6-7

“ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 1፥23

ጸጋ ይብዛላችሁ
ወንድማችሁ አምና

@amnatadesseministry

https://t.me/joinchat/AAAAAE5Veg3GlEdndwaGyw