Get Mystery Box with random crypto!

Amleset Muchie

የቴሌግራም ቻናል አርማ amlesetmuchie — Amleset Muchie A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amlesetmuchie — Amleset Muchie
የሰርጥ አድራሻ: @amlesetmuchie
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.49K
የሰርጥ መግለጫ

She is the winner of titles Miss University 2004, Miss World Ethiopia 2006, she is an actress, a model, film director and writer. she Studied film making at New York Film Academy and Journalisme at uuc.

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-14 13:20:15 በቅድሚያ ጀግናው ልጃችን ቴዲ አፍሮ፦ እንኳን ለኢትዮጵያ ልጇ፥ ለልጆቿም ወንድሞቿ ሆነህ ተወለድክልን። ብዙዎች በዚህ ዓለም ላይ "ከከባድ ነገሮች ውስጥ አንዱ ከባድ ነገር የሚወዱትን ሰው በሚመጥኑ ቃላቶች ለመግለጽ መሞከር ነው" ሲሉ አውቃለሁ። በዚህ ጉዳይ በተወሰነ መልኩ ብስማማም ልቤ ግን አንደበት ከሚገልጸው በላይ ተግባር የሚገልጸው ፍቅር ይልቃል ብሎ ስለሚያምን ይኼን ሰው ለመግለጽ ቸገረኝ ብሎ ከማውራቱ ይልቅ እሱን በእውነተኛ የመውደድ ስሜት መውደዴ ብቻ በቂ ሆኖ ይሰማኛል። እንደ ቴዲ አፍሮ በጀግንነት እና በእርሱ ጽናት ልክ ባይሆንም ጥቂት ነገሮቹን በመውረስ ለአንዲትም ሰከንድ ቢሆን ሀሳቡን ሳልቋወም ከ20 አመታቶች በላይ ከርሱ ጋ ተጉዣለሁ። ይኼ እና ያልገለጽኳቸው እውነታዎች በተግባር የተገለጸውን ፍቅሬን በመጠኑም ቢሆን ይልጻሉ ብዬ አምናለሁ።

ሰውን ለመውደድ ሰው ከመሆን የላቀ ምክኒያት ባያስፈልግም የሰዎች አፍ ግን ስለምን ወደድከው ሲል ዕልፍ ጊዜ ጠይቆኛል። በመጀመሪያ ሰው በመሆኑ እንደ ሁሉ ሰው እንደወደድኩህ በኩራት ተናገርኩ። በመቀጠልም የእርሱን ስብዕናዎች እንዲ እያልኩ መጥቀስ ጀመርኩ። ቴዲ አፍሮን በጣም የወደድኩት ከሌሎቹ በተለየ መልኩ በሙዚቃዎቹ ስለ ፍቅር በጽኑ መንፈስ ስለሚያቀነቅን ነው። እኔ ደግሞ የፍቅርን ኃያልነት የማምን ሰው ነኝ። ፍቅር በእግዚአብሔር ከመወደድ እና እግዚአብሔርን ከመውደድ ይጀምራል። እግዚአብሔርን የሚወድ ሁሉ ሌሎችን ይወዳል። ይኼ የፍቅር ሉዓላዊ /ነጻ/ ህግ ነው።

ታዲያ ስለፍቅር ሌልች አላዜሙም እንዴ ብሉኝ ነጥቤ እሱ አይደለምና ሃሳቤን እንዲህ ስል እቀጥላሉ። ፍቅር ማለት መውደድ ብቻ አይደለም። መፍራት እና ማክበርም ጭምር ነው። በመፍራት የሆነ ማክበር እና አምልኮ ለእግዚአብሔር፥ በማክበር የሆነ መፍራት ደግሞ ለሰው ልጆች እና ለፍጥረት ሁሉ ይገባል። ይኼን መንፈስ የተጎናጸፈ ሰው ደግሞ ታላቁንም ታናሹንም ያከብራል፣ ይወዳል ይፈራልም። መፍራት በሃይለ ቃል ላላመናገር ነው። መፍራት ከላይም ከታችም በማሃከልም ለቆመው ለመታዘዝ መፍቀድን እንደ ሆነ ልብ ይሏል። ከዚህ አንጻር በኪነጥበቡ ዘርፍ እንዲህ ሆኖ ያገኘሁት ይኼንን ሰው ነው። ይኼንን ሰው መውደድ፣ ማክበር፣ መታዘዝ እንዲሁም እንደ ታላቅ ወንድም ማየት ፍጹም ጤናማ ከሆነ ልብ እና አዕምሮ የሚመነጭ ነው። በእግዚአብሔርም ዘንድ መውደድ ለሰው ልጆች ሁሉ የቀረበ የክርስቶስ አዋጅ ነውና ይኼን ሰው በመውደዴ ደስተኛ ነኝ እላለሁ በኩራት።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ አገራችን እና ለወገኖቻችን ላበረከተው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ። የኪነጥበብ ሙያው እንዲከበርና እንዲታፈር ጭምር የእርሱ በዚህ ደረጃ መግዘፍ ዋናውን ሚና ተጫውቷል ለዚህም ትልቅ ክብርን እሰጠዋለሁ። ቴዲ አፍሮ በሚወዱት፣ በሚጠሉት፣ በሚተቹት /በሚቀኑበት/ ባለሙያዎች ልብ ውስጥ ሳይቀር ትልቅነቱ ሊገዝፍ የቻለው እግዚአብሔርን ይዞ በመቆሙ ስለሆነ እግዚአብሔር እስከ ፍጻሜው ድረስ አብሮት ይሆን ዘንድ መልካም ምኞቴ ነው።

ትንሽ ልከትብ ፈልጌ ብዕሬን አነሳሁት ግን ትልቅ ሰው ሆነብኝ እና በትንሽ አንቀጽ ልቋጨው ተሳነኝ። አሁንም ብዙ ጠልቄ መውጫው እንዳይጠፋኝ የልቤን ሀሳብ ገትቼ ምኞቴን ገልጬ ልተው። በእውነተኛ መውደድ የምወድህ የክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ መልካም ልደት ይሁንልህ። የሚወድህ ልቤ የጸነሰውን ሀሳብ በሚያከብርህ ብዕሬ እንዲህ ከተብኩት።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
279 views10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 19:46:36
በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የህይወት ጉዞ ላይ የሚያውጠነጥን "ቴዎድሮስ እስኪነግሥ" የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ከሀምሌ 20/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንባቢያን ይቀርባል።

ከመጽሐፉ...

"...ቴዲ በሥነ-ግጥሙ ዘርፍ የነበረው ሀሳብን በተመጠነ ቃል የመግለጽና ለሰዎች በድምጹ የማቅረብ ልምዱ አድጎና ጎልብቶ እዚህ ደረጃ መድረሱ እጅግ አስገርሞኛል፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ የመኖር ውበት የሚገልጽባቸው መንገዶች ልዩ ናቸው፡፡ አርቲስቱ ከፖለቲካ ነጻ መሆኑና ቀደምት ሀገሪቷን በከፍታ ላስጓዟት መሪዎች የሚሰጠው ክብር ከድምጻውያን መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚያሰልፈው ነው፡፡"

የቴዲ አፍሮ የቀድሞ አማርኛ መምህር ስለሺ ከበደ
350 views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 17:19:33 https://vm.tiktok.com/ZMNj2CAEa
969 views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 20:08:13
የክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ አንተ ጽኑ እና ጀግና አባት ነህ። ከአብራኮችህ ለወጡ ልጆችህ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ምርጥ አባት ሆነህ በመቆምህ ከልብ እናመሰግንኃለን።

የአገሬ ማህጸን እንዳንተ አይነት ቅን ሰዎችን ስለምታፈራ ክብር ሊሰማት ይገባል።

መልካም የአባቶች ቀን ይሁንልህ!

በጽኑ መውደድ እ...ን...ወ...ድ...ኃ...ለ...ን!
1.0K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-05 16:28:36
የመልካም ልደት መግለጫ!

ውዷ አምለሰት ሙጬ እንኳን ተወለድሽ! እንኳንም በሰላምና በጤና ለዚህች ዕለት አደረሰሽ! ኤሚዬ ብሩ እና መልካም ልደት ይሁንልሽ። ቀሪው ዘመንሽ በደስታና በብዙ በረከቶች የተሞላ ይሁን። የልጆችሽን ወግ ማዕረግ የባለቤትሽንም የስኬት ጥግ በዘመንሽ እንዲያሳይሽና የልብሽም መሻቶች በዘመንሽ የተፈጸሙ እንዲሆኑልሽ እመኛለሁ።

ከአክባሪ ወንድምሽ ✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
1.9K views13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 16:34:57
ስለ ቦብ ማርሊ በጥቂቱ

ሙሉ ስም ሮበርት ኔስታ ማርሊ ይባላል እ.ኤ.አ Feb 6/1945 ተወልዶ May 11/1981 በ36 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። ቦብ ማርሊ እናቱ ሴዴላ ቡከር የምትባል ጥቁር ጃማይካዊት ስትሆን አባቱ ደግሞ ኖርቫል ማርሊ የተባለ ነጭ እንግሊዛዊ ነበር። የሙዚቃ ሕይወቱንም የጀመረው በ1960ዎቹ ፒተር ቶሽ እና በኒ ዌይለር ከተባሉ ጓደኞቹ ጋር ዘ ዌይለርስ የተባለ ቡድን በመመስረት ነበር። ከዚያም ከደጋፊ ዘፋኞቹ አንዲቱ የነበረችውን ሪታ ማርሊን በማግበት 5 ልጆች አፍርቷል። ከቦብ ታላቁ የሙዚቃ ስራ "ኖ ውማን ኖ ክራይ" /ቃል በቃል ሲተረጎም/ "አንድም ሴት አታልቅስ" የሚለው ነበር።

ቦብ በአገሩ ጃማይካ እንደ ታላቅ ጀግና የሚቆጠር ሰው ነው። ብሎም ዘፈኖቹ ስለ ፍቅር ከመተረክ ይልቅ ወደ ፖለቲካና ወደ ሃይማኖት ያጋደሉ ስለነበር በዓለም ተቀባይነትን አግኝቷል። እንዲሁም የሬጌን ሙዚቃ ዘዴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ እንዲሆን ያደረገ ሙዚቀኛ ነው። እስካሁንም ድረስ ተፈቃሪነቱ የቀጠለ ሙዚቀኛ ነው። ዛሬ ከተወለደ በህይወት ቢቆይ 77ኛ የልደት በዓሉን ያከብር ነበር።

ቦብ ከመሞቱ ጥቂት ሴኮንዶች በፊት ለልጁ ለዚጊ የተናገረዉ የመጨረሻ ቃል «ገንዘብ ህይወትን አይገዛም» የሚል ነበር።

ቦብ ባንድ ወቅት በህይወት እያለ ስለሚያቀነቅነው የሙዚቃ ስልት ሲጠየቅ ከተናገረው....
ጋዜጠኛ>> «የሬጌ ሙዚቃ ስልት እንዴት ተፈጠረ? የማንስ ነው?»
ቦብ>> «ሬጌ እኮ በጃማይካውያን ሳይንቲስቶች አማካኝነት ከኦርቶዶክስ ቤ/ክርስትያን መንፈሳዊ የከበሮ ምት ዜማ (bit of z drum in z orthodox church's spiritual ceremony) በመጠቀም ተቀናብሮ እና ጣፍጦ የተፈለሰፈ ወይም derived የሆነ የንጉሱ (z king's) ሙዚቃ ነው!» ሲል ቃሉን ሰቷል።
2.3K views13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 14:54:59

2.1K views11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-19 13:23:42
2.0K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 22:02:08 የእውነት ቃል!

ዐይንህን ለማየት፥ ደምጽህን ለመስማት የሚጓጉ ዕልፍ ወዳጆች ያሉህ አንተ ትከሻዬ ላይ እጅህ አረፈ። ዕልፍ አዕላፍ አገር ወዳድና እውነተኛ የሙዚቃ አፍቃሪያን፦ ያዜምከውን የጥበብ ዜማ ብቻ ሳይሆን የተነፈስካትን አንዳች ቃል ለማዳመጥ የሚመኙልህ አንተን፤ ፊት ለፊትህ ቆሜ ሞገስ ያለውን ድምጽህን ሰማሁ። የምስጋና እና የአክብሮት ቃሎችህን አደመጥኩ። ሩቅ የሚመስል የልጅነት ምኞቴ በተደጋጋሚ ተሳክቷል። ሳታውቀኝ ወድጄህ ስሜን እንድትጠራ መልኬን እንድትለይ ያስቻለኸ ከልቤ ውስጥ ያለው እውነተኛ ፍቅር በመሆኑ እደሰታለሁ። ይኼንንም ሳስብ "መውደድ እንዴት ያለ መታደል ነው?" እላለሁ በልቤ።

ብዙዎች ባንተ ሊያከብሩኝና ሊቀርቡኝ ችለዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎች ሳይቀሩ ላንተ ባለኝ ፍቅር ለኔ ዋጋ መስጠት ችለዋል። አሁን ላለሁበት የህይወት ደረጃና ላለኝ ስብዕና አንተን መከተሌ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። ብዙ ቁምነገረኛ ሰዎችን ባንተ ማትረፍ ችያለሁ። ሰው መውደድ ዋጋ ሊያስከፍል ባይገባም እኔ ግን ብዙ አይቻለሁ። ተሰድቤ፣ ተተችቼ፣ ተገላምጬ እንዲሁም ሊፈጸሙልኝ የሚገባቸው ብዙ ጉዳዮችን እስከማጣት ደርሻለሁ። በስልክ እየደወሉና በውስጥ መስመር ባገኙት አጋጣሚ የዛቻ መልዕክቶችን የሚያደርሱኝ ጥቂቶች አይደሉም። የእነዚህ ነገሮች መደጋገም ግን ላንተ ያለኝን ፍቅር እንድተው አልያም እንድቀንስ ጉልበት አላገኙም። እኔም ብሆን በገጠሙኝ ነገሮች የምቆጭና የምጨነቅ ሳልሆን ይልቁንም ፍቅሬን እየጨመርኩ ባንተ ላይ ያለኝን አቋም እያጠበኩኝ መቀጠል ችያለሁ።

"አይሰለችህም? አይደክምህም? ያንተስ በዛ..." ወዘተ ተብዬ አውቃለሁ። ሰዎች ግን ምን ያህል ሞኞች ናቸው? እንዴት መውደድ ይሰለቻል? እንዴት ፍቅር ያደክማል? እግዚአብሔር የማያልቅ፣ የማይደበዝዝ አድርጎ ካጸናቸው መንፈሶች ዋነኛው ፍቅር መሆኑን እንዴት ልብ ማለት አቃታቸው? ዳሩ ሰው ለመውደድ ካልኩኝ ደከመኝ ያኔ ገና ውስጤን /ነፍሴን/ አመመኝ ነው ቁም ነገሩ። የሰውን ልጅ ለመፍጠር ካሳበበት ጊዜ አንስቶ ሰውን በጽኑ መውደድ ሲወድ የኖረ ቅዱስ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው። አምላካችን የመዋደድ መንፈስን በልባችን ያሳደረ፣ የፍቅርንም ዋጋ በመስቀል ላይ ከፍ አድርጎ የሰቀለ ነውና ክብሩ አይጉደልበት። የከበረ ምስጋና ዘውትር ይድረሰው።

ለዘመናት በገጠሙህ መልካምም ሆነ ፈታኝ ነገሮች ላይ ያንተን ያህል ተደስቼም አዝኜም አውቃለሁ። የኔና ያንተ ነገር አፍንጫ ሲነካ ዐይን እንደሚያለቅስ አይነት ነው። ጤንነትህ ያሳስበኛል። ያሰብከው እንዲሳካ የዘራኸው እንዲያፈራ ካንተ እኩል እመኛለሁ። እንደ አንድ የኪነጥበብ ሰው ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቼ አንዱ የሆንክ ያህል ነፍሴ አጥብቃ ትወድሃለች። ለአጤ ቴዎድሮስ ገብርዬ በጽናት እንደቆመለት ሁሉ እኔም ላንተ እጸናለሁ። ለአገር የከፈልከው በዋጋ የማይተመነው መስዋዕትነትህ ነው ይኼንን ፍቅር በልቤ ውስጥ የፈጠረው። በብዙ የቃላት ክምር ስላንተ የሚሰማኝን /የውስጤን/ የመግለጽ ጥበቡ ቢኖረኝ ያንን እወነት እየከተብኩ ለዘመናት በተቀመጥኩበት እቆይ ነበር። ግን የማይገለጹ ብዙ ነገሮች አሉ። ልቤ ውስጥ ካሉት ያነሱ ቢሆኑም የጻፍኳቸው ሁሉ የልቤ ውስጥ የእውነት ቃላቶች ናቸው። ብቻ ግን በእውነተኛ መውደድ ሁሌም እ...ወ...ድ...ኃ...ለ...ው...!

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
2.1K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-01 22:02:08
የእውነት ቃል...

#ቴዲአፍሮ እና #ታታአፍሮ
1.6K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ