Get Mystery Box with random crypto!

Amleset Muchie

የቴሌግራም ቻናል አርማ amlesetmuchie — Amleset Muchie A
የቴሌግራም ቻናል አርማ amlesetmuchie — Amleset Muchie
የሰርጥ አድራሻ: @amlesetmuchie
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.49K
የሰርጥ መግለጫ

She is the winner of titles Miss University 2004, Miss World Ethiopia 2006, she is an actress, a model, film director and writer. she Studied film making at New York Film Academy and Journalisme at uuc.

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-12-31 17:07:52
ክቡር ዶክተር አርቲስት Teddy Afro በአንድ ወቅት ለፈረሳዩ ዓለም አቀፍ ሚድያ ጣቢያ (AFP News Agency) ከሰጠው ቃለምልልስ የተወሰደ..!!

"... ሁሉም ሰው ኢትዮጵያዊነት ውስጡ ያለ ፣ የነበረ ነው! ኢትዮጵያዊነት ሊጠፋ የሚችል አይደለም። እንደሃይማኖት የጠለቀ ነው። ኢትዮጵያዊነት ረቂቅ ሚስጥር አለው። ኢትዮጵያዊነት በጣም ትልቅ መሠረት ያለው ነው። ይህን ባለመረዳት አብረን ባደረግናቸው ብዙ መልካም ነገሮች ላይ መስማማት ስንችል ፣ አብረን ባጎደልናቸው ላይ ዝም ብለን ግዜ ማጥፋት ጠቃሚ አይደለም። ምንግዜም.. .. እኔ ትላንት አዲስ ልጅ ወልጃለሁ። አሁን 4 ዓመት ሆኖታል። ይህ ልጅ ከፍቅርና ከጥላቻ የቱ እንደሚሻል ብጠይቀው የሚነግረኝ ሰለፍቅር ነው። ከአንድነትና ከልዩነት የቱ እንደሚሻል ብጠይቀው ያንተም ልጅ ሊነግረኝ የሚችለው አንድነት ነው። ይሄ ልጆች ሊመልሱት የሚችሉትን ጥያቄዎች በዕድሜ በልጽገን እንኳን ለመግባባት የማንችልባቸው ነጥቦች ላይ በማተኮር ነው ብዙ ወጣቶች ጉዞ ሊደናቀፍ የሆነው። ይሄ ደግሞ ከታላላቆቻችን ግፊያ ነው። የቀድሞ አያቶቻችን ግን ከዚህ የላቀ ቅርጽ የነበራቸው ናቸው። ለዚህም ነው እነሱ ላይ ያተኮረ ሰራ የምሰራው። ስለዚህ ሁሉም የራሱን አመለካከት መግለጽ ደግሞ የተፈጥሮአዊ መብት ነው። ሁሉንም ማስደሰት ባይቻልም ፣ በተቻለ መጠን ሁሉንም የሚያግባባ ቅርጽ ይዞ ለመቅረብ ነው የምሞክረው..."

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ፍቅር ያሸንፋል!!

https://youtube.com/channel/UCQKyrC0xnEk1KhSQqrv2JBg
1.6K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-26 19:11:56 https://vm.tiktok.com/ZM8wRUGfp

#ጥቁር_ሰው

ለአገር ክብር ለተዋደቁ የዘመናችን ጀግኖች ምስጋና ይሆን ዘንድና በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖቻችን የገንዘብ ድጋፍና የተለያዩ ቁሶችን ማሰባሰቢያ እንዲሆን ያለመ እንደዚህ አይነት ግዙፍ ኮንሰርት በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች እንዲዘጋጅ እመኛለሁ! እንደሚደረግም ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ምክኒያቱም እንዲህ አይነት ዝግጅት ሲያዘጋጅ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የመጀመሪያው አይደለም! ይልቁንም የኖረበት ነው።

በኮንሰርቱ ላይ የሶስቱ ነገስታት ስም ይጠራል። /የዳግማዊ አጤ ቴዎድሮስ፣ የዳግማዊ አጤ ምኒልክ እና የቀዳማዊ አጤ ኃይለ ሥላሴ/ እነዚህ ነገስታቶች የኢትዮጵያ ታላቅነት ምንጭ ናቸውና ዳግም በዘመናችን ይታወሳሉ። ይሄ መሆኑ ደግሞ ዛሬም ድረስ የአባቶቻችን ስም ለወገኖቻችን የድጋፍና የጥንካሬ ብሎም የጀግንነት፣ የአንድነትና የአሸናፊነትን መንፈስ በፅኑ የሚያጎናጽፈን መሆኑን ለዓለም የምንመሰክርበት አጋጣሚ ሆኖ ያልፋል። የተጠቀሱት ታላላቅ መንፈሶች በኢትዮጵያ ታላቅነት ለሚኮሩ የድል ዜና ሲሆን ይህችን አገር ለሚጠሏት ደግሞ መራር መርዶ ይሆንባቸዋል።

ኢትዮጵያ የአባቶቻችን አገር ነች እኛም የአባቶችን ልጆች ነንና ተደጋግፈን ማለፍ ያለብንን ሁሉ እናልፋለን። የኛ ኢትዮጵያ ሁሉን አሸንፋ ዳግም በኩራት ትቆማለች።

✎ #ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/

https://vm.tiktok.com/ZM8wRUGfp
1.7K viewsedited  16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-25 20:08:55 የዕልፍ ብዕረኞች ሙገሳ ያልገለፃቸው የኛ አጤ ምኒልክ ዓለም አቀፍ ጀግና ናቸው። የሀሰት ትርክት ፈፅሞ ገናና ስማቸውን ሊያደበዝዘው አይችልም። ምክኒያቱም የተራሮች ግዝፈት የፀሐይን ብርኃን ፍፅሞ ማጥፋት አይችልም።

ትላንት፣ ዛሬም፣ ነገም፣ ለዘለዓለሙም የሚኖር ጀብድ የፈጸሙ ጥቂት ሰዎች በምድራችን አሉ! ከሁሉ ታላቅ ሰው የምንላቸው ግን አጤ ምኒልክ ናቸው! ዘለዓለማዊ ክብርና ሞገስ ለጥቁሩ አጤ ምኒልክ ይሁን!!!


"አባቴ ወኔውን ተኮሰው
ምኒልክ ጥቁር ሰው..."



1.5K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-17 20:30:05
1.6K views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-17 16:20:21 @
1.6K views13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ