Get Mystery Box with random crypto!

የአስተሳሰብ ለውጥ✊

የቴሌግራም ቻናል አርማ amir_islamic_channel — የአስተሳሰብ ለውጥ✊
የቴሌግራም ቻናል አርማ amir_islamic_channel — የአስተሳሰብ ለውጥ✊
የሰርጥ አድራሻ: @amir_islamic_channel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.07K
የሰርጥ መግለጫ

وَلَنُذِيقَنَّهُم مِّنَ الْعَذَابِ الْأَدْنَىٰ دُونَ الْعَذَابِ الْأَكْبَرِ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

ይመለሱ ዘንድም ከትልቁ ቅጣት በፊት (በዚህ ዓለም) ከትንሹ ቅጣት በእርግጥ እናቀምሳቸዋለን፡፡
[ ሱረቱ አል-ሰጅዳህ 32:21 ]
ሃሳብ አስተያት ከላችሁ
@amir_islamic_Channel_bot

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-17 17:27:08 ይሰምራል ሃሳቡ ይሽራል ህመሙ
ያያቸው እንደሆን ነቢዩን በህልሙ
ሲባል የሰማው ሰው ነቢዩን የማየት ጉጉቱ ቢወርሰው ሼኽየው ጋር መጣ ምክርን ፈልጎ

ሃዘኔ ሚጠፋው ውጥኔም ሚሰምር
በሁለቱም ሃገር ተሽቆጥቁጬ ማምር
የሚፈካው ልቤ የሚሽር ህመሜ
ሳያቸው ነውና ነቢዩን በህልሜ
ይኼው በጠዋቱ መጣሁ አሰግስጌ
የልቤ እንዲሞላ ምክሮትን ፈልጌ

ሸኽየው ጠቢቡ ጥቂት አሰላስለው
ለርሱ ብቻ ሳይሆን ለትውልድ ደግሰው
ማለፊያ ምክርን ነገሩት ለዚህ ሰው

ከሼኹ አንደበት

ሦስት ቀን በሙሉ ውሃ ሳትጠጣ
ከቆየህ በኃላ ወደኔ እንድትመጣ
የሚል ትእዛዝ ወጣ

ነቢዩን ለማየት የከጀለው ያ ሰው
ከባዱን ጥም ፀንቶ እየታገሰው
ሁለተኛውን ቀን በጥማት ደረሰው
የመጨረሻይቱ ሶስተኛ ቀን ማታ የተኛው ይኸ ሰው እየተሰቃየ አንድ ህልምን አየ

ሲዋኝ ባህር ሰምጦ ሲራጭም ሲጠጣ
በውሃ ተከቦ ተውሃ እየገባ ተውሃ ሲወጣ
ታዲያ ሌት ነጋና ሼኽየው ጋር መጣ

ይኸው ሶስት ቀን ሙሉ ጥሙን ተቋቁሜ ከውሃ ሸሸሁም
ስቃዩን ታግሼ ጥማቴን ሸኘሁም
ታዲያ ግን ነቢየን በህልሜ አላየሁም
ሲል ቃሉን ሰበቀ

ታዲያ ምንድን አየህ ተብሎም ተጠየቀ
በውኃ ታጅቤ ስራጨው ስጠጣው ስገባው ስወጣው
ጥማቴን ስወጣው ሌቱን አደርኩና ወዳንቱ ጋር መጣው

ሼኹም ከተል አርገው አየህ አንተ ልጄ
ሶስት ቀኑን ሙሉ እጅግ የናፈቅከው
ስታስበው ውለህ ስታስብ ያደርከው
ውኃን ነበርና ልብህ ያሳረፍከው
ያው እንደናፈቅከው በህልምህ ጠጣኻው ጠገብከው
ታዲያ አንተ ልጄ ነቢም እንደ ውኃው ቢጠሙህ ቢናፍቁህ ብታስታውሳቸው
ቀን ሌቱን ተጠምተህ ጠንተህ ብትናፍቃቸው
እሳቸውን ሊያስብ ተከፍቶ ያንተ በር
ዘይንዬን ተጠምቶ ውስጥህ ቢንበረበር
እንደ ውኃው ሁላ ነቢዩንም በህልም ባየሃቸው ነበር
አየህ አንተ ልጄ ከሻትክ ልታያቸው የእውነት አፍቅራቸው
ናፍቅ አስታውሳቸው ተራብ ተጠማቸው
በማለት ተቋጨ ሸኽየው ምክራቸው

صلوات ربي وسلامه عليه
@hayuzizaa
218 viewsZizahayu, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 23:11:10
@Hayuzizaa
210 viewsZizahayu, 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:32:46 አላህ ሆይ
ሰዎች እንደኛው ተሰባሪ መሆናቸውን ረስተን ተደገፍናቸው.....
እንደኛው የሚዝል ትከሻ እንዳላቸው ዘንግተን አረፍ አልንባቸው......
እንደኛው ሚታመሙ መሆናችን ረስተን ከህመማችን እንዲያሽሩን ህመማችንን አወጋናቸው..........
የተሰበረች ልባቸውን ከኛ ቢሸሽጉ እንዲጠግኑን መሰበራችንን ነገርናቸው ..........
ሲያመን ወደነሱ ስንሰበር ወደነሱ ስንደክም ወደነሱ ሆነ ..........
ነገራችንን ሁሉ ወደእነሱ አስጠጋን.........
ከሚገባቸው በላይ አሸከምናቸው..........
ከሚችሉት በላይ እንዲያድርጉ ጠበቅን ..........
ብዙዎቹ
ከህመማቸው ላይ ህመማችን ሲጨመርባቸው ደክመው ሸሹ........
ስብራታቸውን ሳናዳምጥ ስብራታችንን ስንነግራቸው ከኛ ብሰው ተሰባብረው ሄዱ ...........
አደጋገፋችን ከትከሻቸው አቅም በላይ ሆኖ እየዛሉ ተለዩን.........
ጥቂቶቹ ግን አሉ።
በህመማቸው ውስጥ ህመማችን ያስታግሳሉ.........
በስብራታቸው ውስጥ ሊጠግኑን ይጣጣራሉ ..........
የዛለ ትከሻቸውን ለኛ ሲሉ ያበረታሉ .........

ጌትዬ ሆይ

የደከምነውንም የደከሙትንም ሁላችንንም አንተ ጠግነን.....
መጠጊያችን ሆይ ካንተ የበለጠ መጠጊያን መሸሸጊያን አናገኝምና በእዝነትህ ሸሽገን.....
የታመመን የሚያሽር የተሰበረን የሚጠግን ካንተ በላይ የትም የለምና ከህመማችን አሽረን..... ስብራታችንን በውዴታህ ጠግንልን.....
ውስጣችንን ከኛ በላይ አንተ ትረዳለህ
የሚያስፈልገንን ከኛ በላይ አንተ ታውቃለህ
አላህ ሆይ ደካማ ባሮችህ ነን ........
በወንጀል ተጨማልቀን ነፍሳችንን እንኳን ከዝንባሌዋ መግታት አቅቶናል..........
ለባሮችህ እዘንልን....... ደካሞች ነን አበርታን..... ወንጀላችን በዝቷል ማረን

@Hayuzizaa
241 viewsZizahayu, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:32:46 እምቢ በይ እታለም!
(ከካፊር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ብንንቃት?!!
እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬን ከመስመር ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡
ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡
ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስከሚወርድ ………. ከዱዓህ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡
በምታይው ብልጭልጭ ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. ለተኩላ አትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. በራስሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡
ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገልቱ አተላ
ዛሬ እጅሺን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከላይሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞች ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!!


@Hayuzizaa
214 viewsZizahayu, 17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:21:13 ፈጣሪውን አምልኩ እንጂ ፍጡር አይደለም
እስልምና የህይወት መንገድ ነው(አይዲዮሎጂ) ሞክሩት።
እስልምና ስጦታ ነው ተቀበሉት።
እስልምና ጉዞ ነው ሙላው።
እስልምና ግብ ነው ፣ አሳካው።
እስልምና ዕድል ነውና ውሰደው።
እስልምና ቃልኪዳን ነው አሟላው።
እስልምና ግዴታ ነው ተወጣ።
እስልምና ውድ ሀብት ነው (ሶላት) ጸልዩት።
እስልምና ውብ የህይወት መንገድ ነው እዩት::
ኢስላም ለናንተ መልእክት አለው ስሙት።
እስልምና ፍቅር ነው ውደዱ።

@Hayuziza
204 viewsZizahayu, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 13:30:52 ከአላህ የራቀ ልብ በህይወቱ ውስጥ
እርካታን በፍፁም አያገኝም ።
⇘ ህይወት አላህን በእውነት ከልቡ
ለወደደው ናት ።
•┈┈• ❀ ❀•┈┈•
ምድርን ጠባብ የሚያደርጓት
ወንጀሎች ሲሆኑ ሰፊ የሚያደርጓት ደግሞ
ኢስቲግፋሮች ናቸው ።
አስተግፊሩላህ ወአቱቡ ኢለይህ
•┈┈• ❀°• •°❀•┈┈•
ደስ የሚል የዱንያ ጥፍጥና
አርኪ የልብ ደስታ እና እረፍትን
መቅመስ ከፈለጋችሁ ‥
⇘ ግባችሁን ሁሉ የአላህን ፍቅር
ማግኘት አድርጉ ።
•┈┈• ❀°• •°❀•┈┈•
ከጭንቀቶች ሁሉ ትልቁና
አስጨናቂው የአኺራ ጭንቀት ነው
⇘ ልንሰራለትና ልንዘጋጅለት የሚገባውም
ለሱ ነው ። ከዛ የተረፈው ነገር ሁሉ
የፈለገ ያህል ቢገዝፍም ቀላል ነው ።
﴿ ﻓَﺈِﺫﺍ ﺟﺎﺀَﺕِ ﺍﻟﻄّﺎﻣَّﺔُ ﺍﻟﻜُﺒﺮﻯ ﴾
" ታላቂቱም መዐት በመጣች ጊዜ "
[አን-ናዚዓት 34]

@Hayuzizaa
221 viewsZizahayu, 10:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 17:55:18 ♡ ያ ሰው ላንተ ስለማይገባ
⇨ ላንተም ኸይር ስላልነበር
⇨ አላህ አራቀልህ ...
የምን ማዘን ነው ??
@Hayuzizaa
238 viewsZizahayu, 14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 16:52:46 መህሬ "ተውሒድ" ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ሳቢት ኢብኑ አነስ እንዲህ አሉ፡-
አቡ ጦልሓ የተባለ ሰው ኡሙ ሱለይምን የትዳር ጥያቄ ያቀርብላታል ፡

ከዚያ ኡሙ ሱለይም እንዲህ ብላ መለሰችለት ፡

☞ " አንተ አቡ ጦልሓ ሆይ ! (ወላሂ) በአላህ ስም ይሁንብኝ የአንተ አይነት ሰው ለትዳር ጠይቆ እምቢ የምትባልና የምትመለስ ሰው አልነበርክም " ነገር ግን አንተ ካፊር/ካሃዲ ነህ ፡ እኔ ደግሞ ሙስሊም ሴት ነኝ ፡ እኔ አንተን ማግባት አልተፈቀደልኝም ፡ ከሰለምክ እሱ ነው መህሬ ከዚያ ውጭ ምንም አይነትን መህር አልፈልግም ፡
ከዚያም አቡ ጦልሓ ሰለመና ተጋቡ መህሯም ይሄው ሆነ ። አላህ አክበር

በሌላም
የኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) መህሯ ምን ነበር?!
አነስ _ረዲየላሁ ዐንሁ _ እንዲህ ይላሉ፦
"አቡ ጠልሓ ኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) ለማግባት የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ።
ኡሙ ሱለይም፦ "አንተ የምትገዛው ጣኦት እነ እገሌ… የሚባሉ ጎሳዎች መንደር ሐበሻዊ ሰው ከእንጨት እንጠረበው አታውቅምን?"ስትል ጥያቄ አቀረበችለት።
አቡጠልሓም፦"አዎን።ጠንቅቄ አውቃለሁ።"ሲል ምላሹን ሰጣት ።
ኡሙ ሱለይም፦"ታዲያ ሐበሺያዊው ሰው ከእንጨት የጠረበውን ጣኦት ስታመልክ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን?!!"አለችው።
በመቀጠልም፦
"እስልምናን ከተቀበልክ ከሱ ውጭ ሌላ ሰዳቅ ፣ጥሎሽ የምጠይቅህ ነገር አይኖርም።"
አቡጠልሐ፦"እስኪ የማስተውለበትና ከራሴ ጋር የምነጋገርበት ጥቂት ቀናትን ስጪኝ።"ብሏት
ወደ ቤቱ አቀና ብዙም ሳይቆይ ወደርሷ ተመለሰና፦
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ፣ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉላህ"በማለት እስልምናን መቀበሉን ከፊትለፊቷ አበሰራት።
ከዚያም፦

ኡሙ ሱለይም፦"አንተ አነስ ሆይ! ወልይ(ሐላፊ)ሆነህ ከአቡ ጠልሐ ኒካሁን ተቀበል።"አለችኝ።"
ሣቢት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም የላቀ እና ውድ መህር የተሰጣት ሴት ሰምተን አናውቅም፣ምክንያቱም የርሷ መህር አቡ ጠልሐ ኢስላምን መቀበሉ ነበርና።"
@Hayuzizaa
292 viewsZizahayu, 13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 08:31:52
በጧት የመጀመሪያው ስራህ ፈገግ የሚያስብልህን ሰው ፈልግ ምክንያቱም የጧት ፈገግታ ምርጥ ቀን ይፈጥራል!
صباح الخير ..
@hayuzizaa
290 viewsZizahayu, 05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 10:13:51
عندما يخطيء قلبـك مـرّة .. سيُعاقبك عقلـك ألـف مـرّة ..

ልብህ አንድ ጊዜ ሲያጠፋ አእምሮህ አንድ ሺ ጊዜ ይቀጣዋል
@Hayuzizaa
276 viewsZizahayu, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ