Get Mystery Box with random crypto!

'ሰላም፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ሕጻናት' ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2015 ዓ.ም (አሚ | Amhara Media Corporation

"ሰላም፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ሕጻናት"

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ጊዜው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ1976 ነበር። በደቡብ አፍሪካ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር ተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በራሳቸው ቋንቋ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ጥቁር ተማሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ።

በወቅቱ የነበረው የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ መንግሥት ወታደሮች ወደ ሕጻናት ተማሪዎች ተኮሱ። በመቶዎች የሚቆጠሩት ሲያልፉ በሺዎች ቆሰሉ። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በዚህ ሰልፍ ላይ መስዋዕትነት የከፈሉ ሕጻናትን ለማሰብ ከሰኔ 9/1991 ጀምሮ የአፍሪካ ሕፃናት ቀን ኾኖ እንዲከበር ወሰነ።

የአፍሪካ ሕጻናት ቀን በአፍሪካ ለ33ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ32ኛ ጊዜ በባሕርዳር ከተማ ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። በመድረኩ ላይ ከክልሉ ሁሉም ዞኖች የተመረጡ ባለልዩ ፈጠራ ልጆች ሥራዎቻቸውን ያሳያሉ። "ሃምሳ ሎሚ" የተሰኘ በሕጻናት የተዘጋጀ ቲያትርም ይቀርባል።

ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck