Get Mystery Box with random crypto!

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው። ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 | Amhara Media Corporation

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው።

ባሕር ዳር: ሰኔ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የማጠቃለያ ዝግጅት እየተካሄደ ነው።

"ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ" እያለ ዓመታትን የተሻገረው አንጋፋው ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ይገኛል።

ጥበብ፣ ስልጣኔ፣ ታላቅነት፣ ቀደምትነት እና ሩቅ ተጓዥነት ከሚቀዳበት፣ ለዘመናት እየተቀዳ ትውልድ ከጠጣበት፣ ጠጥቶም ከረካበት ከግዮን ጓዳ፣ የከበረ ታሪክ ከመላበት፣ ምስጢር ከበዛበት፣ ቅዱሳን ከሚኖሩበት፣ ገዳማት ከተገደሙበት፣ ከምሥጢራዊ ከጣና ሐይቅ ዳር ተመሥርቶ ጥበብን ከፍልቀቱ ሲቀዳ ኖሯል።

ለዓመታት ጥበብ እየቀዳ ሀገር የኮራችባቸውን፣ እንኳን ወለድኳቸው፣ እንኳንም አስተማርኳቸው ያለቻቸውን ተማሪዎችን፣ ትውልድ ያነፁ መምህራንን ሲያፈራ ኖሯል።

ከበዓይ ጓዳ ጥበብን እየቀዳ ለተጠሙት እያጠጣቸው፣ አጠጥቶም እያረካቸው ኖሯል።

ዛሬም ጥበብን ለተጠሙ ከግዮን እየቀዳ፣ ከጣና እየጨለፈ እያጠጣቸው ይገኛል።

ይህ ከግዮን ጓዳ ጥበብ የሚቀዳበት የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲም 60ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን የማጠቃለያ ዝግጅት እያከበረ ነው።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO