Get Mystery Box with random crypto!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ ባሕርዳር : ግንቦት 1 | Amhara Media Corporation

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

ባሕርዳር : ግንቦት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት "ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ" በሚል መሪ መልእክት በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል፡፡

አባላቶቹ ለሀገሪቱ የጀርባ አጥንት የኾነውን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን እና የአርሶ አደሩን ሕይወት ለማሻሻል የግብርና ሚኒስቴር እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚበረታቱ መኾናቸውን ገልፀዋል፡፡

አውደ ርዕዩ እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚቆይ ሲሆን በግብርናው መስክ የተሰማሩ ከ70 በላይ የምርምርና ፈጠራ ሥራዎች፣ ዲጅታላይዜሽን ፣ ግብርና እና የግብርና ፋይናንስ ላይ ያተኮሩ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ለዕይታ መቅረባቸውን ፋናቢሲ ዘግቧል።

በሳይንስ ሙዚየም የተሰናዳውን አውደ ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም መክፈታቸው ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck