Get Mystery Box with random crypto!

በህንድ ሀሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ወንጀለኞች ተያዙ፤ ከትክክለኛው ፖሊስ ጣቢያ በ5 | አማራ ባንክ Amhara Bank √

በህንድ ሀሰተኛ ፖሊስ ጣቢያ ከፍተው ሲሰሩ የነበሩ ወንጀለኞች ተያዙ፤ ከትክክለኛው ፖሊስ ጣቢያ በ500 ሜትር ብቻ ርቀት ነበረው


በህንድ ቢሃር ግዛት ውስጥ ያለ የወሮበሎች ቡድን ለስምንት ወራት ያህል ሀሰተኛ ፖሊስ ጣቢያን ከፍቶ ሲሰራ እንደነበረ ተደርሶበታል። በቢሃር ግዛት ባንካ ከተማ ውስጥ ይህ ቡድን የመሰረተው ፖሊስ ጣቢያ ከእውነተኛው ፖሊስ ጣቢያ 500 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነበር።

አጭበርባሪዎቹ የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው፣ የጦር መሳሪያ ታጥቀው በመዘዋወር በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በማጭበርበር፣ ቅሬታ ለመመዝገብ ጉቦ በመጠየቅ፣ፖሊስ በመምሰል አስገድደው ጣቢያቸው ድረስ በመውሰድ ዝርፊያ ሲፈፅሙ ነበር።አንድ ትክክለኛ የፖሊስ መኮንን እንቅስቃሴያቸውን ሲያጤን ቆይቶ ወደ ሀሰተኛው ጣቢያ ሲገቡ በመመልከቱ ከ8 ወራት ማጭበርበር በኃላ ተይዘዋል።