Get Mystery Box with random crypto!

#በደባርቅ_ከተማ_ተከስቶ_የነበረዉ_መጠነኛ_የጸጥታ_ችግር_ወደነበረበት_ሰላምና_መረጋጋት_ተመልሷል! | የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

#በደባርቅ_ከተማ_ተከስቶ_የነበረዉ_መጠነኛ_የጸጥታ_ችግር_ወደነበረበት_ሰላምና_መረጋጋት_ተመልሷል!

ረፋድ 2፡50 ገደማ በከተማዉ ቀበሌ 01 በምትገኘዉ የጎጢት ማርያም ቤተክርስቲያን የተከሰተዉን የእሳት ቃጠሎ ተከትሎ የተፈጠረዉ መጠነኛ የፀጥታ ችግር በአካባቢዉ ወጣቶች፣ በሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ በአማራ ልዩ ሃይል፣ በአካባቢዉ ሚሊሻና መላዉ የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረገዉ ብርቱ ጥረት ወደነበረበት ሰላምና መረጋጋት ተመልሷል፡፡ እሳቱም የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር ተችሏል፡፡

የመንግስት የጸጥታ መዋቅር ከአካባቢዉ ህዝብ ጋር በመቀናጀት አጥፊዎችን ለማሳዎቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ስምሪት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን፤ የጸጥታ ምክር ቤቱ የችግሩን ምንጭ፣ የደረሰበትን ዉጤት አስመልክቶ የሚሰጠዉን መግለጫ ተከታትለን የምናሳዉቅ ይሆናል፡፡

ይሁን እንጅ አካባቢዉ ጠላት በቅርብ ርቀት የሚገኝበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለጠላት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር በመሆኑ፤ ህዝባችን አብሮ የመኖር እሴቱን ለማጠናከር አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በመቀናጀት ለአካባቢዉ ሰላምና መረጋጋት የበኩሉን እንዲዎጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን
ሚያዚያ 20/2014 ዓ.ም
ደባርቅ፡