Get Mystery Box with random crypto!

አቶ በረከት ስምዖን የረሃብ አድማ አደረጉ . የማስታወቂያ ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የ | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

አቶ በረከት ስምዖን የረሃብ አድማ አደረጉ
.
የማስታወቂያ ሚኒስትርነትን ጨምሮ በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ የቆዩት እና በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖን የረሃብ አድማ መቱ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖን የረሃብ አድማ መምታታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ትላንት ሚያዚያ 7/2014 ዓ.ም. የጀመረው ይህ የረሃብ አድማቸው መነሻው ለወራት ወደ አዲስ አበባ ለመዘዋወር ለማረሚያ ቤቱ ሲያቀርቡት የቆየው ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ እንደሆነም ምንጮቹ አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በበኩሉ አቶ በረከት የረሃብ አድማ ስለማድረጋቸው መረጃው የለኝም ብሏል።
via- bbc amharic