Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ ሚያዚያ 23 2015 አ/ም የኦሮሞ ብልፅግና ከህወሀት ጋር በአደረገው ስምምነት መሰረት ቀደ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

መረጃ
ሚያዚያ 23 2015 አ/ም

የኦሮሞ ብልፅግና ከህወሀት ጋር በአደረገው ስምምነት መሰረት ቀደም ሲል በህወሀት የስልጣን ዘመን ከፍተኛ ግፍ የፈፀሙ እና በተለይም በመከላከያ እና በደህንነት ተቋም ውስጥ የነበሩ ሰዎች ተመልሰው የሀገሪቱን የፀጥታ መዋቅር እንዲመሩ እና ወደ ቀደመው ጭፍጨፋ እንዲሰማሩ ተደርገዋል ።

ለዛሬው መረጃ በአዲስአበባ ተቀምጠው በተሳሳተ መረጃ በአማራው እና በሌሎች የሀገሪቱ ዜጎች ላይ ግፍ እንዲፈፀም አብይን እና ሌሎችን እያማከሩ የሚገኙ የሚከተሉት ናቸው ።

1፦ ገብረ ዲላ የተባለው ቀደም ሲል የመከላከያ መረጃ ሀላፊ የነበረ ከዚያም ለውጡን ተከትሎ ወደ ኬንያ በመሔድ ኦነግን እና አልሸባብን ሲያደራጅ የነበረ ነው በአጭሩ ይሄ ገብረ ዲላ በጦርነቱ ወቅት ኬንያ ሆኖ አልሽባብን ሲያደራጅ የነበረ ቀደም ሲልም ሶማሊያ ተመድቦ ሲሰራ የነበረ ከሶማሌዎች ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው ነው ። በዚህም የገሬ ጎሳ አባል ሆኖአል ።

ይህ ሰው በከፍተኛ ደረጃ በሶማሊያ ክልል እና በምስራቅ ኢትዮጵያ የተደረገውን ጭፍጨፋ የመራ ነው ፣ ይህን ሰው አብይ አህመድ በቅርቡ ቀን በክብር ሸልሞታል ።

2፦ ኮለኔል ተወልደ አብርሃተንሳ ፣ ይህ ሰው ቀደም ሲል የምዕራብ ዕዝ የመረጃ ሀላፊ የነበረ ሲሆን በጦርነቱ ወቅት ወደ ትግራይ በመሔድ የሰሜን ዕዝን ከማስጨፍጨፍ እስከ ማይካድራ እና ጭላ ጭፍጨፋዎችን የመራ ነው ፣ በቅርብ ከትግራይ ወደ አዲስአበባ በመግባት እነ አብይን እያገዘ ይገኛል::