Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና በማጀቴ፣በሸዋ ሮቢት፣በአጣየ በአጠቃላይ በይፋት ሸዋ የኦህዴድ/ኦነግ ሠራዊት ዛሬ ማለዳ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

ሰበር ዜና

በማጀቴ፣በሸዋ ሮቢት፣በአጣየ በአጠቃላይ በይፋት ሸዋ የኦህዴድ/ኦነግ ሠራዊት ዛሬ ማለዳ በቡድን የታገዘ ጦርነት ከፈተ

የአማራ፣የደቡብ እና የሌሎች አካባቢ ተወላጅ የመከላከያ አባላት ለሽመልስ አብዲሳ ስልጣን ሲባል ወደ ህዝብ አልተኩስም፣አል በማለት እየከዳችሁ ውጡ ሲል ህዝቡ ጥሪ አቅርቧል።

ሼር በማድረግ ጥሪ እናቅርብ!

የኦነጉ ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ዛሬ ከነጋ በሰሜን ሸዋ በማጀቴ፣በአጣዬ፣በሸዋ ሮቢት እና በተለያዩ የሸዋ አካባቢዎች በቡድን የታገዘ ጦርነት በንፁሃን አማሮች ላይ መክፈቱን ህዝቡ ከስፍራው ገለፀ።

ከሚሴ መኮይ አካባቢ እና ማጀቴ ንፁሃን አማሮች የኦህዴድ/ኦነግ ሠራዊት በከፈተው ጦርነት አየተገደሉ መሆኑን ገልፀዋል።

የኦህዴድ ሠራዊት በኦሮሞ ልዩ ዞን ከሚገኙ የኦነግ እና የሸኔ አባላት ጋር በመሆን ነው ጦርነት የከፈተው።

መላው የአማራ ህዝብ የዐብይ አህመድ ሠራዊት በጎንደር እና በሽዋ በቀጥታ በንፁሃን አማሮች ላይ የከፈተውን ግልፅ ጭፍጨፋ ተረድቶ በየቦታ መንገድ በመዝጋት፣መረጃ እና ውሃ በማቀበል ራሱን ከጥፋት ሊከላከል ይገበል ብለዋል።

በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ የሚገኙ ሚዲያዎች፣የሲቪክ ማህበራት፣የዲፕሎማሲ አካላት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ሁሉ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው ግልፅ ጦርነት እንዲቆም ጥሪ እንዲያቀርቡ እና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንዲያሳውቁ ጥሪ ቀርቧል።

#ሼር በማድረግ መረጃውን እናድርስ!!