Get Mystery Box with random crypto!

በአደባባይ ሊከበር የነበረው የላብ አደሮች ቀን ተሰረዘ። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሚ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በአደባባይ ሊከበር የነበረው የላብ አደሮች ቀን ተሰረዘ።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)
ሚያዚያ 23/2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የላብአደሮችን ቀን በማስመልከት ሚያዝያ 23 በአደባባይ ሊከበር የነበረው ክብረ በዓል መሰረዙ ተሰምቷል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ እንደተናገሩት ቀኑን በአደባባይ ማክበር እንደማንችል የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አሳውቁናል ብለዋል።

አቶ ካሳሁን እንዳሉት (ሜይዴይ) የላብ አደሮች ቀን ሚያዚያ 23/2015 ሠራተኛውን የተመለከተ መልእክቶችን በማስተላለፍ በአደባባይ ለማክበር ታስቦ እንደነበር አንስተዋል።

ነገር ግን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በአሉ በአደባባይ እንዳይከበር መከልከሉን ነግረውናል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን የአደባባይ ክብረ በዓሉ መሰረዙን ተከትሎ በቀጣይ ሊኖሩ የሚችሉ ሂደቶችን እንደሚያሳውቅም ገልጸዋል ያለው ለኢትዮ ኤፍ ኤም ነው።