Get Mystery Box with random crypto!

አማራው ጀማል በአማራዊ ማንነቱ ምክንያት በግፍ ተገደለ የአማራ ሚዲያ ማዕከል ሚያዚያ 10 2015 | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

አማራው ጀማል በአማራዊ ማንነቱ ምክንያት በግፍ ተገደለ

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዚያ 10 2015 አ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ወጣት ጀማል አህመድ ተወልዶ ያደገው በዚሁ በወለጋ በአንገር ጉትን አርቁምቢ መንደር 2 ቀበሌ ሲሆን ተወልዶ ባደገበት አከባቢም የታወቀ የስራ ሰው፣ ሰው አክባሪ እና ታታሪ ነው።

ጀማል ገና በልጅነቱ በስራ፣ በማህበራዊ ህይወት የመቻቻልና የመግባባት ባህል ውስጥ የህዝብ ለህዝብ ግንኙትን በፍቅር ያስተሳሰረ የህዝብ ልጅ ነበር።

ጀማል ከግብርና ስራው በተጨማሪ ጎበዜ፣ ታማኝ ነጋዴም ነው። ፍልቅልቅ፣ሳቂታና ተጨዋችም ነው። በተፈጠረው ሐገራዊና አካባቢያዊ ቀውስ ለዘመናት ከኖረበት ቀዬው ተፈናቅሎ በአንገር ጉትን መኖር ከጀመረ አመታት ተቆጥረዋል።

ወጣት ጀማል አህመድ ወይም በቅጽል ስሙ ጀማል አባጥሩ እየተባለ የሚጠራ ሲሆን በአከባቢው ደግሞ ጀማል አርቁቢ እየተባለ የሚጠራ ሐገርና ሰው ወዳድ ጀግና ነበር።

ሆኖም ግን ወጣት ጀማል ሚያዚያ 06-2015ዓ.ም በእለተ አርብ ከመኖሪያ ቤቱ እንዳለ ከባለቤቱ እና ከልጆቹ ፊት በጨካኝ አረመኔ እኔ ቂመኛ አክራሪ ጽንፈኛ በሆኑ አብሮ በኖራቸው በየ #አዱኛ በሊና በተባለው ቀንደኛ የኦነግ ሸኔ ክንፍ በጉትን ከተማ እቤቱ ድረስ በመሔድ ተማሪ የመከላከያ ሠራዊት አጃቢ በመያዝ በግፈኞች በተተኮሰበት በግፍ ተገደለ።

ለጀግናው፣ ለወጣቱ ነጋዴና ቱሁቱ ጀማል መገደል ሬንጀር የለበሰ ይከተሉንጂ ገዳዩ ይሔው በዘረኝነት በሰከረው ግለሰብ መሆኑ ደግሞ እጅጉኑ አሳዛኝ አድርጎታል። ምንጭ አጉልዞ ጥያቄ