Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ የአማራ ሚዲያ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በሱዳን ኦምዱርማን ከተማ የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ

የአማራ ሚዲያ ማእከል
ሚያዚያ10 2915 አ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

በጦርነቱ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ደርሷል

አራተኛ ቀኑን በያዘዉ የሱዳን የከተማ ዉስጥ ጦርነት የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል እና የሀገሪቱ ጦር ዉግያ ዉስጥ ይገኛሉ። በርካታ ኢትዮጵያዊያን መኖሪያ በሆነችዉ ሱዳን ኢትዮጵያዊንም ህይወታቸዉ እንዳለፈ ተሰምቷል።

በሱዳን 12 አመታትን የቆየዉና አስተያየቱን የብስራት ራዲዮ ምንጭና የጤና ባለሙያዉ አቶ ወንድወሰን ጌትነት ፤ ከትናንት በስቲያ 11 ሰዓት ከ 30 አካባቢ ኦምዱርማን በተሰኘዉ አካባቢ በጦርነቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ አራት ኢትዮጵያዊያን በጦር ጄት ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን ተናግሯል። እስካሁን ከ 10 በላይ ኢትዮጵያዊያን በጦርነቱ ሞተዋል ያለን አስተያየት ሰጪያችን ፤ በትናትናዉ እለት በካርቱም ( ጅሬፍ ) በደረሰ ሌላ ጥቃት ፤ ባለትዳሮች ህይወታቸውን ሲያጡ የሶስት አመት ህጻን ልጃቸዉ ከጥቃቱ ተርፏል ብሏል።

በተጨማሪም በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይም ጥቃት መድረሱን ገልጿል። የትኞቹ ታጣቂዎች እንደፈጸሙት ባያረጋግጥልንም የኤምባሲዉን ቅጥርግቢ ጥሰዉ በመግባት በግቢዉ በሱዳን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ባለቤት በሆነበት የመጠለያ ማዕከል ዉስጥ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ አጸያፊ ተግባራት ጭምር መፈጸማቸዉን ተናግሯል።

የኤምባሲዉ ጥበቃዎች በጦርነቱ ወቅት ከግዳጅ ቦታቸዉ በመነሳታቸዉ የተባለዉ ጥቃት ደርሷል። ታጣቂዎቹም ገንዘብን ጨምሮ ዘረፋ መፈጸማቸዉን ነዉ የተናገረዉ።

በሱዳን ያለዉ ሁኔታ አስከፊ መሆኑን የገለጸልን የመረጃ ምንጭ በዋና ከተማዋ ካርቱም ከፍተኛ ዝርፊ መስፈኑንም ጨምሮ ለብስራት ራዲዮ ተናግሯል። ብስራት ራዲዮ በካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲን ለማግኘት ሙከራ እያደረገ ነዉ።
ምንጭ
ዳጉ_ጆ