Get Mystery Box with random crypto!

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ 'የሰዋች ለሰዋች የመሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ 'የሰዋች ለሰዋች የመሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት' የፊዚክስ መምህር የሆነው መምህር በላይ ነጮ በአነደድ ወረዳ ፖሊስና ሚኒሻ ተደብድቦ ራሱን ስቶ ሆስፒታል ገብቷል።

የአማራ ሚዲያ ማዕከል
ሚያዚያ 2 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የኢ-ሰብአዊ ድብደባው መንስኤ ብልፅግናን የሚቃወም መፈክር ይዘህ ወጣቱን አስተባብረህ አደባባይ ወጥተሀል የሚል ነው::

ብልፅግናን ለምን ትቃወማለህ በሚል ኢ- ሰብአዊ በሆነ የተደበደበው መምህር በላይ የቲቢ ታማሚ ነው። መምህር በላይ አሁን ላይ መራመድ አይችልም። ሁለቱም እግሮቹ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል።
ይህን ግፍ የፈፀሙት:-

1.አስራደ ታምሩ:- የአነደድ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ሀላፊ ሲሆን የኦሮሞና የአማራ ተወላጅ ነው። አማራውን አምርሮ የሚጠላ ሰው ነው።

2.ይሄነው ሙሉአዳም:- የአነደድ ወረዳ የሚሊሻ ፅ/ቤት ሀላፊ

3.ማማሩ ገድፍ:- የአነደድ ወረዳ የገቢዋች ሀላፊ።
እነዚህ ሰዋች ህግ ኖሮ በህግ እንዲጠየቁ ሳይሆን ማህበረሰቡ በተለይም ወጣቱ እንዲያውቃቸው ነው።

ምንጭ ምንአልባት ይታየው