Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ፤ “በከባድ መሳሪያ የታገዘ” የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በአማራ ክልል አጣዬ ከተማ፤ “በከባድ መሳሪያ የታገዘ” የተኩስ ልውውጥ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ገለጹ

የአማራ ሚዲያ ማእከል
ሚያዚያ 2 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ

በአማራ ክልል፤ ሰሜን ሸዋ ዞን፤ አጣዬ ከተማ ዛሬ ከንጋት ጀምሮ የተከፈተው በከባድ መሳሪያ የታገዘ ተኩስ እስከ አመሻሽ ድረስ መቀጠሉን ስድስት የከተማዋ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናገሩ። የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ በከተማዋ ተኩስ እንዳለ ቢያረጋግጡም፤ በየትኛው አካል የተፈጸመ እንደሆነ እስካሁን አለመታወቁን ገልጸዋል።

የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና ከተማ በሆነችው አጣዬ ከተማ ተኩስ የተከፈተው፤ ዛሬ ሰኞ ሚያዝያ 2፤ 2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆኑን የከተማይቱ ነዋሪዎች ተናግረዋል። የመጀመሪያው የተኩስ ድምጽ የተሰማው “አላላ” በተባለው የኤፍራታና ግድም ወረዳ ቀበሌ አካባቢ እንደሆነ ነዋሪዎቹ አስረድተዋል።

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች “በዲሽቃ እና ሌሎች ከባድ መሳሪያዎች የታገዘ” ሲሉ የጠሩት ተኩስ የተከፈተው፤ የከተማዋን ዙሪያ ከከበቡት ተራሮች ላይ “በሁሉም አቅጣጫ ነው” ይላሉ። የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አሳልፍ ደርቤ፤ “አጣዬ ዙሪያውን ጦርነት አለ” ሲሉ ተኩሱ በሁሉም አቅጣጫ የሚሰማ መሆኑን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” አረጋግጠዋል።

ምንጭ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር