Get Mystery Box with random crypto!

መስከረም አበራ “ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

መስከረም አበራ “ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ፖሊስ ወንጅሏል።

ከትላንት በስቲያ እሁድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዋ መስከረም አበራ፤ “ሁከት እና ብጥብጥ በማነሳሳት ወንጀል” ተጠርጥራ በፍርድ ቤት 13 የምርመራ ቀናት ተፈቀደባት። መስከረምን ፍርድ ቤት ያቀረባት የፌደራል ፖሊስ፤ “ተጠርጣሪዋ ለኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወታደራዊ ስልጠና እና የተኩስ ልምምድ ስትሰጥ ነበር” ሲል ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

ፖሊስ ዛሬ ማክሰኞ ሚያዚያ 3፤ 2015፤ በመስከረም ላይ ውንጀላውን ያቀረበው፤ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። በችሎቱ መስከረምን ወክለው የቀረቡት ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲጠብቅ ጠይቀዋል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።