Get Mystery Box with random crypto!

በአናሆሮ ወረዳ የኤርፈንቲ ገበር ቀበሌ አማራዎች አዋሳኝ ወደሆነው አቢደንጎሮ ወረዳ ለግብይት በሄዱ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በአናሆሮ ወረዳ የኤርፈንቲ ገበር ቀበሌ አማራዎች አዋሳኝ ወደሆነው አቢደንጎሮ ወረዳ ለግብይት በሄዱበት በመንግስት የጸጥታ አካላት እየታሰሩ በመሆኑ መቸገራቸውን ገለጹ።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

በሆሮ ጉድሩን ወለጋ ዞን አናሆሮ ወረዳ ኤርፈንቲ ገበር ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ አማራዎች ለህክምና፣ ለግብይትም ሆነ ለሌላ ስራ ጉዳይ ከርቀቱ እና ከአሸባሪ ኦነጋዊያን የመንገድ ላይ ጥቃት የተነሳ ወደ ወረዳው ማቅናት አይችሉም።

ያለፈው ቅዳሜ መጋቢት 16/2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ ከ100 በላይ የሚሆኑ አሸባሪ ኦነጋዊያን ወደ ኤርፈንቲ ገበር በማቅናት ተኩስ ከፍተው እንደነበር ተገልጧል።

ከሀሮ ሾጤ ቀበሌ ወደ ገርች ወንዝ በመምጣት ወደ ቢንኩ በመተኮስ ጥቃት ለመፈጸም ስለመሞከራቸው
የኤርፈንቲ ገበር ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል።

ከአናሆሮ ወረዳ ኤርፈንቲ ገበር ቀበሌ ለአቢደንጎሮ ወረዳ ጎረቤት
በመሆኑ የግብይት ልውውጥ እና ሌሎች የማህበራዊ አገልግሎቶችን የሚያገኙት ወደ አካባቢው በማቅናት መሆኑ ተገልጧል።

ይሁን እንጅ በተለይ ከሰሞኑ ከኤርፈንቲ ገበር ወደ አቢደንጎሮ ለግብይት የሄዱ አማራዎችን የአካባቢው ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ እየያዘ እያንገላታ ተቸግረናል
የሚሉት ምንጮች እንደአብነት በእለተ ሰኞ መጋቢት 18/2015 ሰባት የኤርፈንቲ ገበር አማራዎች ለወፍጮ በሄዱበት ታፍነው ስለመታሰራቸው ጠቁመዋል።

በአቢደንጎሮ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮችም:_

1) እንድሪስ ገ/ህይወት፣
2) ሰይድ መኮንን፣
3) መሀመድ እባቡ፣
4) እንድሪስ መኮንን፣
5) የሱፍ አራጌ፣
6) መሀመድ አስፌ እና
7) ሰይድ አስፌ መሆናቸው ተነግሯል።

አንዳንዶች እንደሚሉት በኤርፈንቲ አማራዎች ላይ የተደራጁ አሸባሪ ኦነጋዊያን ጥቃት ሊፈጽሙ በሄዱበት ወቅት ከቡድኑ የተጎዳ አለ በሚል ቁጣ ቢሮ ላይ ያለው ኦነግ እየተበቀለ ስለመሆኑ ይናገራሉ።

የኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትም በሚያገኙን አካባቢ ሁሉ እያሳደዱን በመሆኑ ለችግራችን መፍትሄ ሊፈለግልን ይገባል ሲሉ ጥሪ አድርገዋል።