Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ፋኖ በጎንደር የናደው ሻለቃ መሪዎች አርበኛ ደረጀ በላይ እና ሻለቃ አይሸሽም ዮሐንስ ከደም | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

የአማራ ፋኖ በጎንደር የናደው ሻለቃ መሪዎች አርበኛ ደረጀ በላይ እና ሻለቃ አይሸሽም ዮሐንስ ከደምቢያ ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ተለቀዋል፤ የፋኖዎች የምክክር መድረክ ግን ተከልክሏል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

የአማራ ፋኖ በጎንደር የናደው ሻለቃ መሪዎች አርበኛ ደረጀ በላይ እና ሻለቃ አይሸሽም ዮሐንስ ስብሰባ አታደርጉም የሚል ክልከላ ከደምቢያ ወረዳ አመራሮች የገጠማቸው መሆኑ ታውቋል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) መጋቢት 21/2015 ረፋድ ላይ እንዳጣራው
1) ከሰቀልት አይምባ፣
2) ከቆላድባ እና
3) ከጯሂት ተጓጉዘው ከመጡ ፋኖዎች ጋር ሊደረግ የነበረው የምክክር መድረክ ከመስተጓጎሉ አልፎ ከበላይ በመጣ ትዕዛዝ በሚል ተከልክሏል።

አሚማ ስብሰባውን ለማካሄድ በዝግጅት ላይ እያሉ ወደ እስር ተወስደዋል የተባሉትን የአማራ ፋኖ በጎንደር የናደው ሻለቃ መሪዎች አርበኛ ደረጀ በላይ እና ሻለቃ አይሸሽም ዮሐንስን ለማግኘት ጥረት አድርጓል።

ወደ ቢሮ ተወስደን ከደምቢያ ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ተለቀናል፤ ስብሰባውም እንዳይካሄድ ተከልክሏል ያለው ሻለቃ አይሸሽም ዮሃንስ ነው።

ወቅቱ የበለጠ አንድነታችን ማጠናከር ያለብን ጊዜ ላይ መሆናችንን ታሳቢ በማድረግ ከአባላት ጋር የሚደረገውን ምክክር ለሌላ ጊዜ ለማራዘም ተገደናል ብሏል።

መሰብሰብ መብት እንጅ ወንጀል አለመሆኑን የጠቀሰው ሻለቃ አይሸሽም "ያለንበት ሁኔታ ካልገባቸው እስኪገባቸው ድረስ ተነጋግረን በሌላ ጊዜ ስብሰባችን እናስኬዳለን" የሚል አቋም መያዛቸውን ተከትሎ ተሰብሳቢዎች ወደየመጡበት እንዲመለሱ ማደረጋቸውንም ተናግሯል።