Get Mystery Box with random crypto!

በእነ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ቤት ፍተሻ ተደርጓል፤ ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አ | አማራ ሚዲያ ማዕከል Amhara media center

በእነ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ቤት ፍተሻ ተደርጓል፤ ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አንድም ነገር አልተገኘም ተብሏል።

አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
መጋቢት 21 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ

ፌደራል ፖሊስ መጋቢት 20/2015 ረፋድ ላይ በእነ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና ጌትነት አሻግሬ ቤት ፍተሻ አድርጓል።

ነገር ግን ጋዜጠኞችን ተጠያቂ ሊያደርግ የሚችል አንድም ነገር አልተገኘም ተብሏል።

በጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ አራት የፌደራል ፖሊስ አባላት የዐይን እማኞችን ከጎረቤት በማካተት ፍተሻውን አድርገው ተመልሰዋል ተብሏል።

የሮሃ ኒውስ ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እና የአማራ ድምጽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ መጋቢት 17/2015 በፌደራል ፖሊስ ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው ወደ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸው ይታወሳል።