Get Mystery Box with random crypto!

በጣም አስቸኳይ የበረከት ስራ የሰማእቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች የሆናችሁ ይህ በረከት እንዳያመ | #የግጥም_ዓለም

በጣም አስቸኳይ የበረከት ስራ

የሰማእቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ወዳጆች የሆናችሁ ይህ በረከት እንዳያመልጠን... የ5 ብር ካርድ ከ5 ደቂቃ በላይ አያዋራም ለጊዮርጊስ የምናወጣት 5 ብር ግን እስከ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ድረስ ታነጋግረናለች ምህረት እና ይቅርታን ታስገኝልናለች....

ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ይህችን መልእክት የምታነቡ ሁላችሁም የበኩላችሁን ተባበሩኝ መልእክቱ የኔ ሳይሆን የሊቀ ሰማእታት የቅዱስ ጊዮርጊስ ነው ...

ወደ ጉዳያችን ልግባና በቡሬ ወረዳ ሽማጎ በተባለች ትንሽየ ሰፈር ውስጥ የሰማእቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በሚገርም ሁኔታ ተጠናቆ ...ግን አንዳንድ ያልተሟሉ ነገሮች አሉ።

ለምሳሌ ብነግራችሁ 2 ካህናት እና 3 ዲያቆናት ብቻ ናቸው ያሉት... እነዚህም ያለምንም ክፍያ ነው የሚያገለግሉት። በዚያ ላይ ደግሞ የክብረ በዓል ጊዜ ሊቃውንቱ ማኅሌቱን ሲቆሙ ጸናጽል የለም። መቋሚያ የለም። ...እነዚህ እና መሰል ችግሮች ስላሉ የእኛን ኪስ ይመለከታሉ። አስቡት እኛ አቅም ላይኖረን ይችላል። ግን እመኑኝ ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ ብትተባበሩኝ ግን ልዑል እግዚአብሔር መፍትሄ አያሳጣንም። እኛም ደግሞ ከ5 ሳንቲም ጀምሮ እስከ ≥10 ብር ለእግዚአብሔር ዓሥራት በኩራት ብናወጣ ምን ያክል ጽድቅ ይሆንልን??

እውነት እላችኋለው ሰው በሌለበት ሰው ሆኖ መገኘት እንዴት አይነት መመረጥ መሰላችሁ?? እርግጠኛ ነኝ ሁሉን የሚያውቅ እግዚአብሔር ነው። ያላችሁ በብራችሁ የሌላችሁ በጸሎታችሁ እና ሼር በማድረግ ታሪክ እንስራ! ብናውቀው ኖሮ የእግዚአብሔርን ቤት ለመስራትም ሆነ ለመርዳትም እኮ መመረጥ ያስፈልጋል። አስታውሱ የኢየሩሳሌምን ቤተ መቅደስ ሊሰራ የፈለገው ዳዊት ነበር። ግን አልተፈቀደለትም። ለሰሎሞን ነበር የተፈቀደለት።

"ስጡ ይሰጣችኋል በምድር ያላበደረ በሰማይ የሚያበድረው የለም ፣ በምድር ርኅራኄ ያላደረገ በሰማይ የሚራራለት አያገኝም ፣ በዚህ ዓለም ማደሪያ ሰጥቶ እንግዳውን ያልተቀበለ በዚያች በፍርድ ቀን የሚያሳድረው አይኖርም ፣ በምድር ንስሐ ካልገባ በሰማይ ንስሐ የለም....(ድርሳነ ሚካኤል ዘመስከረም)

ስንቅ እንያዝ በማይታበል ቃሉ ይምረናልና " "ለዘጸውዓ ስመከ ወለዘገብረ ተዝካረከ ወለሐነጸ ቤትከ እምህር ለከ ፣ ስምህን የጠራውን መታሰቢያህን ያደረገውን ቤተ ክርስቲያንህን ያነጸውን ይቅር እልልሃለው" ...እንግዲህ ለጠቢብ አንዲት ቃል ትበቃዋለች ሰማእቱ 7 ዓመት ተሰቃይቶ ያገኛትን ክብር እግዚአብሔር ስለሚወደን እንኩ ለእናንተም ይለናል....

=> እኔ ያሰብኩት የባንክ አካውንት በሰማእቱ ስም ይከፈት ከዚያ በኋላ ሁሉም ሰው የሚችለውን ያበርክት ምናልባት ይህንን መልእክት አይቶ ሙሉውን የሚሸፍን ሰው እንዳለ ማን ያውቃል? ወይም ሌላ የተሻለ አማራጭ ካለ እንነጋገር "ተናገር ወኢታርምም ተናገር ዝም አትበል"... አደራ በሰማእቱ ስም በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም በኮከበ ፋርስ ስም ብላችሁ እዚህ ላይ አስተያየት አስቀምጡልኝ ምን ማድረግ እንዳለብን እንድንነጋገር እፈልጋለው እንዳያመልጠን ሌሎች እንዳይቀድሙን እንፍጠን!!!